💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇
👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ

📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri






ኅዳር ፮ ቊስቋም ማርያም


እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ቊስቋም ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓሏ በሰላም አደረሳችሁ ።

በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው ።

ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤ እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው

"
ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ኢትዮጵያ ናት፤ በዚህች አገር ያሉ ሳይዩኝ ያመኑኛል፤ አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል፡፡
በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን ፤ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል፡፡

ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

©ልቦና ቲዩብ


╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯



ጥቅምት ፲፬ የአባታችን አቡነ አረጋዊ የተሰወሩበት መታሰቢያ በዓል ነው


እንኳን ለአባታችን ለአቡነ አረጋዊ ዓመታዊ በዓል በሠላም አደረሳችሁ

ከአባታችን ከአቡነ አረጋዊ በረከት ረድኤት ያሳትፈን ከቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ ከቅዱስ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ከቅዱስ ፊልጶስ በረከት ረድኤት ይክፈለን ምልጃቸው አይለየን ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውሩን አሜን በእውነት

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯


መስከረም 29 ሰማእቷ ቅድስት አርሴማ ሰማእትነትን የተቀበለችበት ዕለት ነው።

"
ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቁመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትሆን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው።"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ

ሰማእቷ ቅድስት አርሴማ እኛንም ከተጋረጠብን ችግር ፈተና የምንወጣበትን ብርታት ታድለን የቅድስት አርሴማ ምልጃ አይለየን ::
አሜን


╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯


💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛 dan repost
​​✞ዘመነ ጽጌ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል አንድ
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን  ሕግና ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን  እስከ ሕዳር 6 ቀን  ያለው40 ቀን  የእመቤታችንን እና የልጇን ስደትበማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች።ይህ 40ው ቀን የእመቤታችንና የጌታችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው።

ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታችን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡
 በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አምሥቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡

በዚሁ ዘመን ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል  ማኅሌተ ጽጌ  የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡
 
ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሄድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ሲሆን  ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ ወቅት ተለይቶለት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚውለው ግን   በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና በልጇ የስደት ዘመን  ማለትም  ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው  ዘመን ውስጥ ነው፡፡

በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊቱን በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ  ምድረ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እየታሰበ በሊቃውንቱ  የሚደርስ የምሥጋና ጸሎትም  ነው።
ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ  ሲሆን በአብዛኛው አምስት ስንኞች ሲኖሩት ብዛቱም 158 ያክል ነው፡፡እመቤታችን ጣዕሟንና ፍቅሯን እንዲሁም ምስጋናዋን ሲናፍቁ የነበሩትን ቅዱስ ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን እንደገለጸችላቸው  ሁሉ ለፍቅሯ ሲሳሳ ለነበረው ለአባ ጽጌ ድንግል ደግሞ ይህንን የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት  እንዲደርስ ምስጢርን ገልጻለታልች ።
 
በቅድስት ሐገር ሐገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ  የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት ወርኅ ጽጌ (ዘመነ ጽጌ) ናቸው።ይህም ወቅት ተራሮች በአበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡

በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ልብስ ስለምን ትጨነቃላችሁ ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡አይደክሙም፣ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡እግዚአብሔር፣ ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፣ እናንተንማ ይልቁን እንዴት፡፡ እንግዲህ ምን እንበላለን፣ ምንስ እንጠጣለን፣ ምንስ እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ።"ማቴ ፭÷፳፰-፴፫
በማለት የተናገረውን ቃል በማሰብ መጨነቅ የሚገባን መንግሥተ ሰማያት ለመግባት እንጂ በዚህ ዓለም ስላለው ነገር እንዳልሆነ ተራሮችን በአበባ ያለበሰ አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረንን እኛን ለኑሮ የሚያስፈልገንን ምግብና ልብስ እንደማይነሳን እያሰብን የምንዘክርበት ወቅት ነው።

የሊቁ  ድርሰትም ፍሬ ከአበባ÷ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘ ሁሉ ማኅሌተ ጽጌም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚ
ያስረዳ ድርሰት ነው።እርሷን በአበባ ሲመስል ልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል  ልጇን ደግሞ በአበባ እየመሰለ ይናገራል

ነቢዩ ኢሳይያስ "ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ ወየዓርግ ጽጌ እም ጕንዱ - ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፤ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል።"ኢሳ ፲፩÷፩ብሎ ከእሴይ ዘር የምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ፣ ከርሷ የሚገኘውን ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎ ትንቢቱን ተናግሯል፡፡

አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱን መልክዕ እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬ በመመሰል፣ ከዚያው በማያያዝ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በምሥጢር፣ በታሪክ፣ በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበ ሁኔታ አዋሕዶ ደርሶታል።

ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እመቤታችንን በአበባ እየመሰለ ከተናገረው   ድርሰቱ መሐከል አንዱ  "ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘዘመነ ጽጌ እንግዳ ወዘመነ ፍሬ  ጽጋብ  ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ  ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእምአውግሪሁ ለይሁዳ  ፀቃውዐ   መዓር  ቅድው (ጥዑም) ወሀሊብ ፀዓዳ" በመከር ጊዜ አበባ፣ በአበባ ጊዜ ደግሞ መከር አዝመራ ማጨድና መሰብሰብ የለም፡፡ምክንያቱም ጊዜያቸው የተለያየ ስለሆነ።

ለምሳሌ በመስከረም ወር የአበባ ጊዜ በመሆኑ አዝመራ መሰብሰብ የለም፡፡ የትንቢት መከር መካተቻ የሆንሽ እንደ ዘመነ ጽጌ የረሃብን ዘመን ያስወገድሽ ማርያም ሆይ፣ የኤልዳ ነቢይ ኢዩኤል ከይሁዳ ተራሮች ጣፋጭ ማርና ፀዐዳ ወተት ይፈሳል ብሎ የተናገረው ትንቢት በአንቺ ታወቀ፣ ተፈጸመ።
እመቤታችን ነቢያት የተናገሩት የትንቢት ዘር ተፈጸመባት ማለትም ነቢያት የአምላክን ሰው የመሆን ነገር በተለያየ ሁኔታ ተናግረዋል።

ጌታችን ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መፈጸሙንና ይህንን ፍጻሜ ለማየት የታደሉት ሐዋርያት መሆናቸውን "አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል"የሚለው ቃል እውነት ሆኗል፡፡
"እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ።ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ።"በማለት ተናግሮአልዮሐ.፬÷፴፯-፴፰)፡፡ 
ይህም ነቢያት የዘሩት ትንቢት በሐዋርያት ዘመን ለአጨዳ ለፍሬ መድረሱን መናገሩ ነው።ስለሆነም "ማዕረረ ትንቢት"የትንቢት መካተቻ ማርያም አላት።
በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ ክርስቶስን ያስገኘችና ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች እየተባለ የተነገረላት በመሆንዋ ድንግል ማርያም  በአበባ ትመሰላለች፡፡
ስለዚህ እመቤታችን በመከር ወራት የምትገኝ አበባ ናት።በመከር ጊዜ የአበባ መገኘት ያልተለመደ ስለሆነ "ወዘመነ ጽጌ እንግዳ "እንግዳ የሆነ አበባ አላት፡፡ ከዚህ በኋላ "ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፣ ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእምአውጋሪሁ ለይሁዳ፣ ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሀሊበ ፀዓዳ"በማለት ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረውን ትንቢት አፈጻጸም ይናገራል፡፡

ነቢዩ ኢዩኤል በዘመኑ ጽኑ ረኅብ ነበር፡፡እግዚአብሔር ሕዝቡን በምሕረት እንደሚጐበኛቸውና ረሃቡ እንደሚጠፋ ይነግራቸው ነበር፡፡ 
"ብዙ መብል ትበላላችሁ÷ ትጠግቡማላችሁ፣ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል፣ ተራሮች በተሃ ጠጅ ያንጠበጥባሉ÷ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ÷ በይሁዳም ያሉት ፏፏቴዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ"
ኢዩ ፫፥፲፰፣ ፪፥፳፮

ክፍል ሁለት ይቀጥላል....
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯


✞አርሴማ ቅድስት✞


አርሴማ ቅድስት እናታችን አርሴማ ቅድስት
የእውነት ምስክር ሰማዕት(፪) አርሴማ ቅድስት

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯


💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛 dan repost
"...እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሳ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው። እርሱም ተነስቶ ሕፃኑንና እናቱን በለሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ 'ልጄን ከግብፅ ጠራሁት'(ሆሴ፲፩፥፩) የተባለው አንዲፈፀም ወደ ግብፅ ሄደ።"

ማቴ ፪፥፲፫-፲፭
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱




✞በልዩ መንበሯ✞

ልዩ መንበሯ አገሯ ግሸን ማማሯ (፪)
ማማሯ ማማሯ - - አገሯ ግሸን ማማሯ(፪)
የክርስቶስ መስቀል - - አገሯ ግንሸን ማማሯ

የክርስቶስ መስቀል - - አገሯ ግሸን ማማሯ
ያረፈበት ስፍራ  - - አገሯ ግሸን ማማሯ
ሰላም ደብረ ከርቤ - - አገሯ ግሸን ማማሯ
የታቦር ተራራ - - አገሯ ግሸን ማማሯ
   
በልዩ መንበሩ ሚጣቅ አማኑኤል
ማማሩ ማማሩ - - ሚጣቅ አማኑኤል ማማሩ(፪)
የፍጥረታት ገዢ - - ሚጣቅ አማኑኤል ማማሩ
የሁሉ አባት - - ሚጣቅ አማኑኤል ማማሩ 
ተወልዶ አዳነን - - ሚጣቅ አማኑኤል ማማሩ
በገብርኤል ብሥራት - - ሚጣቅ አማኑኤል ማማሩ

በልዩ መንበሩ ቁልቢው ገብርኤል ማማሩ
ማማሩ ማማሩ - - ቁልቢው ገብርኤል ማማሩ(፪)
ሠለስቱ ደቂቅን - - ቁልቢው ገብርኤል ማማሩ   
ያዳነ ከእቶን - - ቁልቢው ገብርኤል ማማሩ  
ከክፉ ፈተና - - ቁልቢው ገብርኤል ማማሩ  
እኛንም ያውጣን - - ቁልቢው ገብርኤል ማማሩ

  
በልዩ መንበሩ ቅዱስ ሚካኤል ማማሩ
ማማሩ ማማሩ - - ቅዱስ ሚካኤል ማማሩ
ቅድስት አፎምያን - - ቅዱስ ሚካኤል ማማሩ
ከሰይጣን ያስጣላት - - ቅዱስ ሚካኤል ማማሩ
የጌታ ባለሟል - - ቅዱስ ሚካኤል ማማሩ
የባሕራን አባት - - ቅዱስ ሚካኤል ማማሩ  

በአሥራት አገሯ   እንጦጦ ማርያም ማማሯ
በአሥራት አገሯ - - አዳዲ ማርያም ማማሯ
በአሥራት አገሯ - - የአክሱም ጽዮን ማማሯ
ማማሯ ማማሯ - - የአክሱም ጽዮን ማማሯ(፪)
በጸሎትሽ እና - - የአክሱም ጽዮን ማማሯ
በአማላጅነትሽ - - የአክሱም ጽዮን ማማሯ
አስቢኝ ትላለች - - የአክሱም ጽዮን ማማሯ
ኢትዮጵያ ርስትሽ - - የአክሱም ጽዮን ማማሯ


          
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

   @yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯


💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛 dan repost
​​በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ጼዴንያ

በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን ከሚዘከሩ በዓላት መካከል የእመቤታችን በዓል አንደኛው ሲኾን ይኸውም ጼዴንያ በምትባል አገር ከሥዕሏ ተአምር የተደረገበት ዕለት ነው፡፡

በተአምረ ማርያምና በመጽሐፈ ስንክሳር እንደ ተመዘገበው ቅዱስ ሉቃስ ከሣላት ሥጋ የለበሰች ከምትመስል የእመቤታችን የሥዕል ሠሌዳ ቅባት ይንጠፈጠፍ ነበር።

እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምትወድና በሚቻላትም ኹሉ የምታገለግላት፣ ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን አባ ቴዎድሮስ የሚባሉ መነኵሴ ከእርሷ ዘንድ በእንግድነት አድረው በማግሥቱ ከቤቷ ሲወጡ ማርታ የሚሔዱበትን አገር በጠየቀቻቸው ጊዜ  እርሳቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው ቅዱሳት መካናትን እንደሚሳለሙ ነገሯት፡፡

ማርታም ከእርሷ ገንዘብ ወስደው የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተው ይዘውላት እንዲመጡ ለመነቻቸው፡፡

መነኵሴውም በራሳቸው ገንዘብ ሥዕሉን ገዝተው እንደሚያመጡላት ቃል ገቡላት፡፡

አባ ቴዎድሮስ ኢየሩሳሌም ደርሰው ቅዱሳት መካናትን ከተሳለሙ በኋላ ሥዕሏን ሳይገዙ ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡

ያን ጊዜም "ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ?" የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰምተው ወደ ገበያ ተመልሰው መልኳ ያማረና የተወደደ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ገዝተው በሐርና በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ይዘው እየተጓዙ ሳሉ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ሲደርሱ ወንበዴዎች ተነሡባቸው፡፡

ሊሸሹ ሲሉም "መንገድህን ሒድ" የሚል ቃል ከሥዕሏ ወጣ፤ መነኵሴውም መንገዳቸውን በሰላም ተጓዙ፡፡

ሁለተኛም አንበሳ ሊበላቸው በተነሣባቸው ጊዜ ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረላቸው፡፡

አባ ቴዎድሮስ ይህን ኹሉ ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜም ያቺን ሥዕል ለማርታ ከመስጠት ይልቅ ወደ አገራቸው ሊወስዷት ወደዱ፡፡

በመርከብ ተሳፍረው በሌላ አቅጣጫ ሲሔዱም ታላቅ ነፋስ ተነሥቶ ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያ ወሰዳቸው፡፡

ከመርከብም ወርደው ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ደረሱ፡፡ ነገር ግን ማንነታቸውን ለማርታ አልገለጡላትም፤ እርሷም አላወቀቻቸውም ነበር፡፡

በማግሥቱም ተሠውረው ወደ አገራቸው ሊሔዱ ሲሉ የቅፅሩ ደጃፍ ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ዋሉ፤ በመሸባቸው ጊዜም ወደ ማደሪያቸው ተመለሱ፡፡

ማታ ማታ በሩን ያዩታል፤ ነግቶ መሔድን ሲሹ ግን የበሩ መንገድ ይሠወርባቸዋል፡፡ እንዲህም ኾነው እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቆዩ፡፡

ማርታም "አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን? ስትቅበዘበዝ አይሃለሁና ምን ኾነህ ነው?" ሰትል ጠየቀቻችው፡፡

እርሳቸውም ከእመቤታችን ሥዕል የተደረገውን ተአምር ኹሉ ነገሯት፤ ራሳቸውንም ገለጡላትና ሥዕሏን ሰጧት፡፡

እርሷም የእመቤታችንን ሥዕል ተቀብላ የተጠቀለለችበትን ልብስ በፈታችው ጊዜ ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች፡፡

ከደስታዋ ብዛት የተነሣም የአባ ቴዎድሮስን እጃቸውንና እግራቸውን ሳመች፡፡ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር አኖረቻት፡፡

ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት፡፡ በቀንና በሌሊትም የሚያበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች፤ ከመቅረዞች ውጭም የሐር መጋረጃን ጋረደች፡፡

ከሥዕሊቱ በታችም እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች፡፡ እኒያ መነኰስም እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገሉ ኖሩ፡፡

የአገሩ ሊቀ ጳጳስም የእመቤታችን ሥዕል ሥጋ የለበሰች ኹና ባገኙና ተአምሯንም በተመለከቱ ጊዜ ከዚህ አምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ፡፡

ከሥዕሏ ከሚንጠባጠበው ቅባት ቀድተው ለበረከት ሲካፈሉም ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ መላ፡፡

ሥዕሊቱን ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜም ንውጽውጽታ ኾኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ፡፡

ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያች አገር (በጼዴንያ) ትገኛለች፡፡
"እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው።" ተብሎ እንደ ተጻፈ /መዝ.፷፯፥፴፭/ እግዚአብሔር አምላካችን በልዩ ልዩ መንገድ ለሰው ልጅ ተአምራቱን ይገልጣል።


በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ እንደምናገኘው እግዚአብሔር ከዓለት ላይ ውኃ እያፈለቀ ሕዝቡን ያጠጣል፡፡ ከግዑዝ ዓለት ውስጥ ውኃ የሚያፈልቅ አምላክ ከሥጋዋ ሥጋ፤ ከነፍሷ ነፍስ ተዋሕዶ ካከበራት ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ወዝ እንዲፈስ ቢያደርግ ምን ይሳነዋል? እንደዚሁም ቅዱሳን ሐዋርያት በቃላቸውም፣ በልብሳቸውም፣ በጥላቸውም ሙታንን በማስነሣት፤ ሕሙማንን በመፈወስ ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡

ለምሳሌ ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው፤ ቅዱስ ጳውሎስም በልብሱ ቅዳጅ ያደርጓቸው የነበሩ ተአምራትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሐዋርያት ከእግዚአብሔር ዘንድ በተሰጣቸው ጸጋ በልብሳቸውና በሰውነታቸው ጥላ ተአምራትን ማድረግ እንደ ተቻላቸው ኹሉ አምላክን በማኅፀኗ የተሸከመችው ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን መፈወስ ይቻላታል፡፡

ከቅዱሳን ልብስና ጥላ የእርሷ ሥዕል ይከብራልና፡፡ ስለዚህም ነው በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት የሚከበረው፡፡

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ የልጇ፣ የወዳጇ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት አይለየን፡፡

ምንጭ፦መስከረም ፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ዝግጅት ክፍል


ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯


#ምስለ_ራጉኤል



ምስለ ራጉኤል ስዑል በነበልባል ወዮሐንስ ድንግል ወበርተሎሜዎስ ሐዋርያ ሰባኬ ወንጌል ወኢዮብ ዓዲ ተወካፌ ቁስል
ዐውደ ዓመት ለባርኮ እም ጽርሐ አርያም ጌልጌል ማርያም ንዒ ለምህረት ወሳህል(ነግስ ዘመስከረም ዮሐንስ)
    
ትርጉም

በነበልባል ከተሳለ ከራጉኤል ድንግል ከሆነ ከዮሐንስ ከወንጌል ሰባኪ ሐዋርያ በርተሎሜዎስ ጋር ዳግመኛም መከራን(ቁስልን) ከተቀበለ ኢዮብ ጋር ማርያም ሆይ ዐውደ ዓመትን ለመባረክ ጌልጌል ከሚባል ከጽርሐ አርያም ለምሕረት እና ለይቅርታ ነዪ።


#ምስለ_ራጉኤል


ምስለ ራጉኤል ስዑል በነበልባል ወዮሐንስ ድንግል
ዐውደ ዓመት ለባርኮ ማርያም ንዒ ለምህረት ወሳህል

መዝሙር
በመምህር መልአኩ የማነ እና
በዲ/ን ይሁንሰላም
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯


​​በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

መስከረም አንድ ቀን

ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ


ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው። ማቴ ፲፥፫

ነገር ግን ዜና ሕይወቱ በስፋት ሲተረክ አንሰማም ቅዱሱ ሐዋርያ እንደ ሌሎቹ ወንድሞቹ ዓለምን በወንጌል ትምህርት አብርቷል በትውፊት ትምህርት መሠረት 'በርተሎሜዎስ' የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታችን ሲሆን ትርጉሙም 'ተክሎችን የሚያጠጣ' ማለት ነው።

ከሐዋርያትም ጌታ አስቀድሞ የስም ቅያሪ ያደረገለት ለእርሱ እንደ ሆነ ይታመናል። በርተሎሜዎስ የግብርና ሥራውን ትቶ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ከዋለበት እየዋለ ካደረበትም እያደረ ምሥጢረ ወንጌልን ተምሯል።

ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላም ከሐዋርያት ጋር ዓለምን በዕጣ ተካፍሏል።

ሃገረ ስብከቱም 'እልዋህ' እና 'አርማንያ' ናቸው። የአርማንያ መንበርም የእርሱ ነው። ቅዱሱ ገድሉ እንደሚለው አሕዛብን በስብከቱና በሚያስደነግጡ ተአምራቱ አሳምኗል::


ከቅዱስ ዼጥሮስ ከቅዱስ እንድርያስ ከክርስቶፎሮስና ከሌሎቹም ሰባክያን ጋር ዓለምን ዞሯል።

ሙታንን አስነስቶ ድውያንን ፈውሶ አጋንንትን አውጥቶ ብዙዎችን ወደ ሕይወት መልሷል። የደረቁ እንጨቶችም በእጁ ላይ እንዳሉ ለምልመው አብበው ያፈሩ ነበር ።

ቅዱስ በርተሎሜዎስ እያስተማረ ወደ ኢትዮዽያም ደርሶ እንደ ነበር ይነገራል። በመጨረሻም 'ለሚስቶቻችን ንጽሕናን አስተምረሃል' በሚል ተከሶ ንጉሥ አግሪዻ በሰቅ (ጸጉር) ጠቅልሎ አሸዋ ሞልቶ ባሕር ውስጥ ጥሎታል። በዚያውም ዐርፏል።


    የሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ በረከት በሁላችን ላይ አድሮ ይኑር ።አሜን።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯






🌼 #የእንቁጣጣሽ_መዝሙር
        🌼  🌼 🌼
       በማኅበረ ፊልጶስ
                  🌼 🌼 🌼 🌼
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
    @yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯


💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛 dan repost
​​🌼የእንቁጣጣሽ መዝሙር🌼
                  🌼🌼

እሰይ /ደስ ደስ ይበላችሁ/(፪)
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ

      ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)ጌቶች አሉ ብለን
      ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)እሜቴ አሉ ብለን

አበባዮሽ 🌼 ለምለም   አበባዮሽ 🌼  ለምለም
እንቆቅልሽ   - -  ንግሥት   ልትፈትል ሄዳ - - ንግሥት
ንግስተ አዜብ - -  ንግሥት   እናት ማክዳ - - ንግሥት
በልቧ ያለውን -  ንግሥት   አጫወታቸው - -   ንግሥት
አሰቀምጣ አበባ🌼  ንግሥት  እያሳየችው - -    ንግሥት
መአዛው የሚሸት  - - ከሁለቱ የቱ ነው አለቸው - -  ለንጉሥ 

          ንግስት ሆይ ለጥያቄሽ ጥበብ አለሽ(፪)
      🌼የአገር አምባር የሚሆነው ከልብ ሽተሽ

እንቆቅልሹ -  -  የሳባ    ከበድም ቢለው -  -🌼 የሳባ
ጥበብ ሰላለው - - ንጉሡ  ሚሥጥሩን ሊያውቀው - - ንጉሡ
ክፈት መስኮቱን - -  ሰለሞን   ቢለው ለሎሌው  - -ሰለሞን
ገቡ ንቦቹ  - -  ሊቀስሙ🌼 ከአባባው አርፈው - - ሊቀስሙ
ብልህ ጠቢቡ  - -   መለሠ     ለተጠየቀው - -  በእውነት
ንጉስ ሰለሞን - -   አለ     አልተሠወረው      🌼     በእውነት

🌼አደይ ቅድስት ሀገሬ እልል በይ (፪)
🌼 ኢትዩዮጲያ የዝና ስሟ በዓለም ተሠማ (፪)
🌼
ለፈጣሪዋ - - ንግሥት   ምስጋና አቅርባ - -   ንግሥት
ኢትዮጲያዊቷ - - ንግሥት   ንግስተ ሣባ   🌼   ንግሥት
ጥበቡን አይታ - -  ንግሥት   አደነቀችው  - -    ንግሥት
ወርቅ ሸቶውን - -  ንግሥት  ዕንቁ ሰጠችው - -   ንግሥት

      ንግስት ሆይ ምስክር ሆንሽ ለሀገርሽ (፪)🌼🌼
      የአምላክን የፈጣሪያችን ስሙን ጠርተሽ (፪)🌼🌼

የኢትዮጵያ ሠዎች  - -ለንግሥት   ቆሙ በተራ - -ለንግሥት
እደጅ ሆነው     🌼   ለንግሥት   ለዙፋን ክብሯ - - ለንግሥት
በመስከረም ወር - -  ለንግሥት   ሀገር ስትገባ - -  ለንግሥት
ይዘው ሥጦታ - -  ለንግሥት   የፈካ አበባ    🌼ለንግሥት

      🌼አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ (፪)🌼🌼
      🌼ኢትዮጲያ በታሪክሽ ጥንታዊት ነሽ (፪)🌼🌼

ኢየሩሳሌም - - ንግሥት   ደርሠሽ መጣሽ - -  ንግሥት
እንኳን በክብር - - ንግሥት   ለዚህ አበቃሽ - - ንግሥት
ከአምላክ በረከት - - ንግሥት  ፍሬ አግኝተሽ - - ንግሥት
የዘሽ ስጦታ - -  ንግሥት   ዕንቁ ለጣጣሽ - - ንግሥት

      🌼ንግስት ሆይ ለታሪክሽ ክብር አለሽ (፪)🌼🌼
      🌼ልጆችሽ አበባዮሽ እያልን እናስታውስሽ (፪)🌼🌼

🌼የአባቶች ተስፋ - -   ለፃድቃን   የነቢያት ትንቢት - - ለፅናት
የሙሴ ፅላት - -     ለፀሎት   የአሮን በትር  - -   ለፅናት
የዳዊት መንግስት - - ለፅናት    ይዘሸ የመጣሽ - -   ከጥንት
አምስቱን አውታር - - ለሠጠሽ   ለሀገር መሠረት -    በእውነት🌼🌼

🌼 አደይ ቅድስት ኢትዮጵያ እልል በይ (፪)🌼🌼
      🌼ኢትዮጵያ በልጆችሽ ደስ ይበልሽ (፪)🌼🌼

በህገ ልቦና  - -   ህጉን     ፈጣሪን አውቀሽ - -  ህጉን
ህገ ነቢያትን - -  ከዓለም  ፈጥነሽ ተቀበልሽ - - ከዓለም
በብሉይ ኪዳን   🌼ለጌታ    መስዋዕት አቅርበሽ - -  ለጌታ
ተስፋ ካረጉት - - ከአይሁድ ከአስራኤል - - ከአይሁድ
ህገ ወንጌልን-  -በፊት    ይዘሽ ተገኘሽ    🌼    በፊት

      🌼ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ፀጋ አለሽ(፪)🌼🌼
      🌼ስለፈፀምሽ ሦስቱን ህግጋት ለፈጣሪሽ (፪)🌼🌼


ካለፈው ሰህተት - -  ሁላችን    እንድንመለስ - - ሁላችን
አዲሱ ዓመት  - -  ለሁሉም   መጣ ማቴዎስ- -ለሁሉም
ይህም ያልፍና - - በጊዜው    ይመጣል ማርቆስ - - በጊዜው
ሌላው ይተካል - -  በጊዜው    ዘመነ ሉቃስ - - በጊዜው
ወልደነጓድጓድ  - -  በጊዜው  🌼 ሲደርስ ዮሐንስ - - በጊዜው
በየአራት ዓመት -  -  በጊዜው   ለሁሉም ሲደርስ - - በጊዜው
በየዓመቱ  - -  መጥምቁ      ቅዱስ ዩሐንስ - - በጊዜው🌼🌼

      🌼አደይ የብርሃን ጮራ በዮሐንስ በራ(፪)🌼🌼
🌼 ኢትዮጵያ ባሕል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ (፪)🌼🌼

ልጅ አበባ ልጅ አበባዬ    🌼     አዬ ውዲቷ እናቴ
ልጅ አበባ 🌼እያለች እማማ      አዬ ውዲቷ እናቴ
ምክሯን ሁሌ እኔ እንድሰማ    አዬ ውዲቷ እናቴ
እያሻሸች እንድሆን ጤናማ     አዬ ውዲቷ እማማ
አዬ ውዲቷ እናቴ (፪)🌼

🌼አበባ ለምለም 🌼 ቀጤማ ለምለም
    🌼ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም (፪)🌼

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ🌼
እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰዎት ብዬ (፪)
🌼
ይሸታል ዶሮ ዶሮ (፪) ከማምዬ ጓሮ (፪)
ይሸታል የወይን ጠጅ (፪) ከጋሽዬ ደጅ (፪)

      ከበረው ይቆዩ ከብረው 🌼
       አመት አወደ አመት ደርሰው
      ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው
      ትሁት ሰው አክባሪ ሆነው
      የፍቅር ሸማን ለብሰው🌼
      ንስሐ ገብተው ቆርበው
  🌼ከብረው ይቆዩ ከብረው
          
               መዝሙር
      🌼በማህበረ ፊልጶስ🌼

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
    @yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯


💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛 dan repost
​​በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🌼አዲስ ዓመት🌼

ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡

ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
 
🌼ዘመን መለወጫ🌼
ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡

ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ "ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፡፡ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡/ሄኖክ ፳፮፥፵፬/

"ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድሱ"/ሰቆኤር ፭፥፳፩/ እንዲል፡፡

በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ /ኩፋሌ፯፥፩/ በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየች"እንዲል፡፡
 
🌼ዕንቁጣጣሽ🌼
ዕንቁጣጣሽ የተባለበት ምክንያት

✝አንደኛ፦ "ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ" ብሎ የአበባውን መፈንዳት ያመለክታል፡፡

✝ሁለተኛ፦ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡

ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

✝ሦስተኛው፦ /፩ነገ፲፥፩-፲/ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ /አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ መንሻ በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም "እንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ" በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም ወርኀ መስከረም ነበር፡፡

ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡
 
🌼ቅዱስ ዮሐንስ🌼
ሦስተኛው የአዲስ ዘመን ስያሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡

/ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1-3/ መጽሐፈ ስንክሳር "የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል" እንዲል፡፡
 
በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኀጢአት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባል።

ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም
በዳዊት ደስታ
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯


መንፈሳዊ ግጥሞች እና ብሂሎች dan repost
🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼

"የምወዳችኹ ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችኁ ትሻላችሁን?

እንኪያስ ገና ከጅምሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኃጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኃጢአት አትጀምሩት፡፡

እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው።

የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡

አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡ በትግሃ ሌሊት፣ በቀዊም፣ በጾም በጸሎት እንድንበረታ ስንቅ ይኾነናል፡፡ በስካር፣ በዘፈን፣ በኀዘን የምንጀምረው ከኾነ ግን ዓመቱ ሙሉ እንዲኽ የተጐሳቈለ ዓመትን እናሳልፋለን፡፡ ሕይወታችንን በከንቱ እንገፋለን።

ዲያብሎስም ይኽን ጥንቅቅ አድረጐ ስለሚያውቅ ዓመቱን በገቢረ ኀጢአት እንድንጀምረው እየቀሰቀሰ ነው፡፡ ፈቃዳችንን አጥፍቶ፣ ዓይነ ልቡናችንን አሳውሮ በዘፈን፣ በስካር፣ በዋይታ እንድንጀምረው በተለያየ መንገድ እየለፈፈ ነው፡፡...."
💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥
  ✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥

●🔸 @Behila_Abew 🔸●
●🔸 @Behila_Abew 🔸●

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.