Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
♻️ታዋቂ ሳይሆን አዋቂ ሁን!
☞ሸሪዓዊ ርዕሶችን የሚመለከቱ ጭብጦች፣ ምልከታዎችና ትንታኔዎችን በብዕራችን ከመክተባችን፣ በአንደበታችን ከመናገራችንና በአእምሮኣችን ከማሰባችን በፊት በዚህ ርዕስ ላይ በቂ የሆነ የእውቀት ክምችት፣ ያልተዛባ የማስተላለፍ ብቃት እንዲሁም ሰናይ የሚባል እቅድ እንዳለን እናረጋግጥ። የኢስላም ሊቃውንቶች የተለያዩ ሸሪዓን የተመለከቱ ብይኖችንና ምልከታዎች ከመተንተናቸው በፊት አይኖቻቸው በሺዎች የሚገመቱ አያሌ ድርሳናትን ተመልክተው፣ መዳፎቻቸው ከአስር ሺዎች የሚልቁ ገፆችን አገላብጠውና ለዚህም መሰረታዊ ስንቅ የሚሆናቸውን ስር የሰደደ የፈጣሪ ፍራቻን አላብሰውት ነበር። በሸሪዓ ሚዛን ታዋቂነት በራሱ ተፈልጎ የሚለፋለት መሰረታዊ ግብ አይደለም። እንደውም በቀደምት አበዎች ዘንድ ታዋቂነትን መሻት ከመናፍቃን ተርታ የሚያስመድብ ሀጢያት ተደርጎ ተቆጥሯል።
አምሎኮኣዊ ድንበር የተበጀላቸው ነገሮች በአጠቃላይ ኢኽላስ የሚባል እጅግ ከባድ ድልድይ ተዘርግቶላቸዋል። ይህን ድልድይ ማለፍ የቻለ ብቻ ትክክለኛውን መቅሰድ ያሳካል። ይህን የተቀደሰ አላማ ባፈገፈገ መልኩ ዝናን መሻት የተቀላቀለበት ፅሁፍም ሆነ ድምፅ ብኩን መሆኑ እርግጥ ነው። የእውቀት ሽታን በወጉ ያላሸተቱ እጆችና ከእውቀት ነፃ አጃቢ የበዛላቸው ስብዕናዎች ይህን ትልቅ መርሆ በመሸሻቸው ሰበብ አስገራሚ ግትርነትና ማንነት ላይ ብቅ ይላሉ። ለጥቂት ግዜያት እጆች አፎች ላይ ተደራርበውና አይኖች ፈጠውላቸው የተደነቁ ፅሁፎች እንዲሁም ጆሮዎች የሚናፍቋቸው ድምፆች በእውነትም የአላህ ፊት ካልተፈለገባቸው ትቢያ ሆነው በአጭር ግዜያት ይበናሉ። በተቃራኒው እይታን የተነፈጉ የታፈኑ ፅሁፎችና ከማዳመጫ ታንቡር የሸሹ ድምፆች ሐቅ ተላብሰው የአላህ ፊት ከተሻባቸው በግዜ ሂደት ይጎመራሉ። በእውነትም ያብባሉ። ይህ ሁሉ በግዜ ሂደት የሚፈታ እንቆቅልሽ እንደሆነ እሙን ይሁንልኝ።
ለአላህ ተብለው የተሰሩ ተግባሮች ስራቸው ወደ ምድር እየሰደደ ፍሬያቸው እያበበ ሰዎችም ፈለጎቻቸውን እየቀጠፉና መአዛውን እየታወዱ ይዘወትራሉ። እውቀት ላይ ትእግስት የሌላቸው አካሎች በፍፁም መልካም ፍሬን ሊያፈሩ፣ ስብእናን ሊያንፁና የተንሻፈፈን ሊያቀኑ አይችሉም። ፅናትም አይኖራቸው። ተራ ዝና መሻት ይሰለቻል። ያደክማል። ከዝና ስር ተሰግስገው የተደበቁ እውነተኛ ማንነቶች ከእውቅና ማግስት ይፋ ሲሆኑ ግራ የሚያጋቡ አስገራሚ ስብዕናዎች ሆነው ብቅ ይላሉ።
እውቀት ከማንም በላይ ባለቤቱን ከቃላት ግድፈትና ከእሳቤ ብክነት እርምትን ይሰጣል። እውቀትና ኢኽላስ ያልጎተተው ዝና መኣዛው የጠነዛ፣ ቅምሻው የጎመዛና መጨረሻው መሳለቂያ ነው። ይህን ስል ሀቅ ተናጋሪ አፎችን ለመለጎምና ሀቅ ፀሀፊ እጆችን ለመጠምዘዝ አይደለም። በእውቀት ላይ ተቀምጠናል ብለው ለሚመፃደቁ ዝንጉዎች በፍፁም ብርታት አይሰጥም። ነገር ግን ሁሉም በልኩ እንዲራመድና ከደረጃው በላይ እንዳይንጠራራ ይሁን።
✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
https://t.me/abdurezaq27