🌹የሱና እህቶች የለውጥ ሚና🌹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


♡..አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ከመገላለጥ ተጠንቀቂ {{በአላህ ፍቃድ}} ከፈተናዎች ጠባቂሽ የሆነውን ሂጃብሽን አጥብቀሽ ያዢ!❥...
🍃═══ ¤❁✿❁¤ ═══🍃

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
🚫ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!

♻️እነዚህ ፊልሞችና ምስሎች የጀሀነም በሮች ናቸው!

📵እነዚህን የበከቱና የተግማሙ ዝሙተኞችን በማየት እስረኛ የሆንክ/ሽ ሁሉ በዚህ ሰበብ ምን እንደሚከተልህ/ሽ ተከታዩን እስተውለህ/ሽ አንብብ/ቢ!

☞ለላጤዎችና ለባለትዳሮች መጨረሻ ላይ የተቀመጠውን መፍትሄ በጥሞና አንብቡት!

☞የተራቆቱ ዝሞተኞችን ማየት እጅግ ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ እንደሚካተቱ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት ውርደትና ደካማነት እንደሚያወርስ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት በሰዎች አይን ያነስክና ወራዳ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞እነዚህን አፀያፊ ምስሎችና ቪድዮዎች በማየት የተለከፈ ወጣት በቀላሉ ካገኘው ተቃራኒ ፆታ ጋር ሁሉ ዝሙት ላይ የሚወድቅ ይሆናል። እንዲሁም ራስን ወደ ማርካት (masturbation) ሱስና የስንፈተ ወሲብ አደጋ ተጋላጭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።

☞እነዚህን የዝሙት ዌብሳይቶችና የቪድዮ ምስሎች መመልከት በአእምሮህና በአይንህ ላይ ድክመትን እንደሚከስት ታውቃለህ? ይህን በመመልከት ሱሰኛ የሆነ ሰው ቀለል ያሉ ጉዳዮችን በቀላሉ ይረሳል። ይህ አደጋ እያደገ ሲሄድ የአእምሮ ድክመት አስከትሎበት እንዴት መናገር እንዳለበት ሁሉ ላያውቅ ይችላል! ሌሎችም ብዙ የጤና እክሎች ያጋጥሙታል!

☞ይህ ወንጀል አላህ ዘንድ ወራዳ ሰው እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞የእነዚህ ዝሙተኞች ምስል አእምሮህ ላይ ተቀርፇል? (ይህ የአላህ ቁጣ ምልክት ነው!)

☞እነዚህን ነገሮች መመልከት ትንንሽ ነገሮችን ሁሉ የምትሰጋ ፈሪና ልፍስፍስ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞ይህን እርቃን ብልግና የምትመለከት ሆይ! የሸሪዓ እውቀትን ብርሃን በፍፁም ማግኘት እንደማትችል ታውቃለህ?

☞በዚህ ወንጀልህ ከምትወዳትና ከምትወድህ የህይወት አጋርህ ባለቤትህ ጋር የተረጋጋ ህይወት መኖር እንደምትነፈግ ታውቃለህ?

☞ይህን አስቀያሚ ተግባር የምትመለከት ከሆነ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች ይህን ቀፋፊ ተግባርህን ባትነግራቸውም እንኳን ሊጠሉህ እንደሚችሉ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞችን ማየት ግዴታ የሚሆንብህ በዝሙት ወንጀላቸው በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ?

☞ ከዚህ ከምትመለከተው ቀፋፊ ምልከታ እውነተኛ ተውበት አድርገህ ወደ አላህ ካልተመለስክ እጅግ ከባድ ዋጋ ለወደፊት እንደሚያስከፍልህ ታውቃለህ?

☞እጅግ የምትወደውና የምትቀርበው ሰው ሞት ዜና ይህን ነገር እየተመለከትክ ብትሰማ ትወዳለህ?

☞ ከዚህ ወንጀል አፀያፊነት የተነሳ አላህ መሬትን ደርምሶ ሊያስውጥህ እንደሚችል ታውቃለህ?

☞በዚህ ቀፋፊ ምልከታ ላይ ሆነህ ሞት ሊመጣህ እንደሚችል ታውቃለህ? አስከፊ ኻቲማ ሊያስደነግጥህ እንደማይችል እርግጠኛ ነህ?

☞ጌታህ ቻይ ነው! ለግዜው ይተውኃል፤ ነገር ግን በምትሰራው ወንጀል ደስተኛ ሆኖ እንዳይመስልህ! ከዚህ ወንጀልህ ተውበት ካላደረክ ለወደፊትም ቢሆን ከባድ መከራ ትጋረጣለህ!

☞ የዒባዳህን ጥፍጥና እንደሚያሳጣህ አምልኮ ላይ ደካማ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

ለዒባዳ በቆምክ ቁጥር የምታያቸው ምስሎች አዕምሮህን ተቆጣጥረው እንደሚፈታተኑህ ታውቃለህ? በዚህም ከአምልኮ መሸሽና ተስፋ ቢስነት ሊሰማህ ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ አደገኛው አዘቅት ክህደት የሚጎትት ጠንቅ ነው።

☞ ራስህን የምትጠላ የወንጀል ምርኮኛ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞ለአላህ ብሎ አንዳች ነገርን
የተወ ሰው አላህ የተሻለ መልካም ነገር እንደሚተካለት ታውቃለህ?

☞አላህ በባሪያው መመለስ የሚደሰት የተብቃቃና ምስጉን ጌታ መሆኑን ታውቃለህ?

☞ከወንጀል ጥብቅ ከሆንክ አላህ ከችሮታው እንደሚያብቃቃህ ታውቃለህ?

☞ለደቂቃዎች (ሻህዋ) ስሜት ተብለው የሚሰሩ ወንጀሎች የአመታት ቅጣት እንደሚያመጡ ታውቃለህ?

☞ዛሬ በዱንያ ላይ የምትሰራቸው ወንጀሎች፦ የተከለከለን ማየት፣ መስራትና ሌሎችንም በዱንያ ላይ ቅጣቱን በድህነት፣ በአደጋ፣ ሪዝቅህን በመከልከል በቤተሰብህ፣ በልጆችህና በቅርብ ሰዎች ላይ አደጋ ሊከስት እንደሚችል ታውቃለህ?

☞ይህ ወንጀል አእምሮህን ተቆጣጥሮ ከምትመለከታት ሴት ሁሉ ቀፋፊው ዝሙት ላይ ለመወደቅ እንደሚገፋፋህ ታውቃለህ?



✅✅✅✅✅

☞ለላጤዎች ምክር!

♻️ያላገባህ እንደሆነ በተቻለህ መጠን ለማግባት ሞክር!

♻️ስለ ትዳር በቂ እውቀት ይዘህ ወደ ትዳር ግባ!

♻️ ማግባት ካልቻልክ ትርፍ የምትለውን ግዜህን በመልካም ነገር አሳልፍ፦ በፆም፣ በንባብ፣ ስፖርት በመስራት፣ መልካም ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመማር፣ በመስማትና በማየት.......

♻️በብዛት ብቻህን ከመሆን ተቆጠብ

♻️አላህን ከዚህ ቀፋፊ ወንጀል ነፃ እንዲያደርግህ ተማፀን!

♻️መልካም ሰዎች ጋር ለመቀማመጥ ሞክር!

♻️ሸይጣን ይህን ወንጀል ባስታወሰህ ቁጥር ቆራጥ ሆነህ ላለመመለስ ሞክር! መጀመሪያው ቢከብድብም በሂደት አላህ ይረዳሃል!

☞ለባለ ትዳሮች ምክር

♻️አግብተህ ከሆነ ከትዳር አጋርህ ጋር ስለ ህይወታቹህ ያለ እፍረት በግልፅ በመነጋገር የምትፈልጉትን እርካታ ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እውቅ!

♻️ በኢስላም ጥላ ስር ያሉ ታማኝ ከትዳር ህይወት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ትምህርቶችንና ጥናታዊ ፅሁፎችን አንብብ!

♻️ በዚህ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን አላህን የሚፈሩ ብለህ የምታስባቸውን ወንድሞችህን አማክር!

♻️ ሚስትም የዘመኑን ክፋት ልትረዳና ነቃ ብላ ከትዳር አጓሯ ጎን ልትቆም ይገባል። በግልፅ ማውራትና ፍላጎቱን ማሟላት ብልግና ሳይሆን ብልጠት መሆኑን አውቃ በተቻለ መጠን ውበቷን በመጠበቅ የባሏ ልብ እንዳይሸፍትና እንዳይሰላች የበኩሏን ጥረት ሁሉ በማድረግ ባለቤቷን ማስደሰት አለባት!

✖️እነዚህ የተግማሙና የበከቱ ዝሙተኞች ይህችን አጭር ህይወትን እንዲያበላሹ አትፍቀድ! ጀግና ሁን/ሁኚ!

♻️በመጨረሻም የመልካም ሰዎችን ታሪክ አንብብ! እንዴት አላህን እንደሚጠነቀቁ አስተውል። አስተንትን! በዚህ ወንጀልህ የሰማያትና የምድር ጌታን እያመፅክ መሆኑ ይሰማህ!
ኮምፒዩተሮችህና ስማርት ስልኮችን የመዋረጃህ ሰበብ አታድርጋቸው!

ኢብኑ'ል ወርዲይ በግጥማቸው እንዲህ ብለዋል ፦
إنَّ أحلى عيشةٍ قضيتُها
ذهبتْ لذاتُها والإثمُ حلْ

ስሜቴን ያራገፍኩባቸው ጣፋጭ ግዜያቶች
ጥፍጥናቸው ሄዷል ወንጀሉ ቅን ቀርቷል/ተመዝግቧል


♻️ሁላችንንም አላህ ለሚወደው ይምራን!

✍Abdurazaq alhabeshiy

https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
አስገራሚ መልስ!

አንድ ሴኩላሪስት የሆነ ግለሰብ እንዲህ አለ "ሴት ልጅ ውበቷን ለመጠበቅ ስትል ልጅ መውለድ አልፈልግም ማለት መብቷ ነው።"

ይህን ንግግር እየሰሙ ካሉ ሰዎች መካከል አንደኛው እንዲህ አለው "ምነው እናትህ ውበቷን ለመጠበቅ ስትል ባልወለደችህ ኖሮ!"

https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
☞ለአስተዋዮች ብቻ!
―――――――――――
⇨አንዲት እጅግ በጣም ቆንጆ ሴት ሐጅና ዑምራ ለማረግ ወደ መካ አቀናች። ጀምረተ'ል ዐቀባ አካባቢ ሆና ጠጠሮችን ስትወረውር ገጣሚው ዑመር ኢብን አቢ ረቢዐ ተመለከታት። ይህ ሰው ፍቅር አዘል በሆኑ ግጥሞቹ ሴቶችን የሚያስቸግርና የሚያባብል በሴት ፍቅር የተለከፈ ዋልጌ ነበረ። ጠጋ ብሎ አናገራት መልስ አልሰጠችውም። በሁለተኛው ቀንም አናገራት። እሷም "ዞር በልልኝ! የተከበረው የአላህ ቤት ውስጥ እንዲሁም በተከበረ ቀን ውስጥ ነው ያለሁት! " ብላ ኮስተር አለችበት። ችክ ብሎ ይለማመጣትና ይገጣጥምላት ጀመረ። እሷም የጉዳዩን ሁኔታ መጋለጥ ሰግታ መወርወሯን ትታ ወደ ድንኳኗ ተመለሰች። በሶስተኛው ለሊት ወንድሟን "አብረን እንሂድና የሐጅ መናሲኮችን አሳየኝ" አለችው። ያ ገጣሚና ሴቶችን ለካፊ የሆነው ሰው ወንድሟን አብሯት ያየ ግዜ ከቦታው ሳይንቀሳቀስ እዛው ባለበት ተቀመጠ። ወደሷም አልተጠጋም። ይህን ስትመለከት ፈገግ ብላ ይህን ታዋቂ ግጥም ገጠመች።

*تعدو الكلاب على من لا أسود له*
*وتتقي صولة المستأسد الضاري*

☞የግጥሙ ግርድፍ ትርጉም

አንበሳ በሌለው ውሾች ይዘላሉ
ተናካሽ አንበሳን ጉዳት ግን ይሰጋሉ

☞ይህን ንግግሯን አቡ ጀዕፈር አል መንሱር የሰማ ግዜ "የቁርይሽ ወጣት ሴቶች ሁሉ ይህን ክስተት ሳይሰሙ እንዳይቀሩ ብዬ ወደድኩ" አለ።

☞በሆነ ከተማ ላይ አስተዋይና ሷሊሕ የሆነች እናት ነበረች። ሴት ልጇ ከቤት ስትወጣ ለወንድሟ "ተከተላት! ከእህትህ ጋር ሂድ። ሴት ልጅ መንገድ የሚያሰፋላትና የሚጠብቃት ወንድ ልጅ ከሌለ ልክ በተኩላዎች መሀል እንዳለች በግ ነች። ደካማው ተኩላም ይዳፈራታል!" ትለዋለች።

☞ገጣሚውም ይህን አለ!

📜 قال الشاعر:
*إنّ الرجال الناظرين إلى النساء*
*مثلُ الكلاب تطوفُ باللحمانِ*
*إن لم تصن تلك اللحوم أسودُها*
*أُكِلت بلا عِوضٍ ولا أثمانِ*

≈≈የግጥሙ ግርድፍ ትርጉም⇓

ሴቶች ላይ አፍጣጭ ወንዶች
ምሳሌያቸው በክትን ዟሪ ውሾች
ስጋዋን አንበሳዋ ካልጠበቀች
ያለ ልዋጭና ክፍያ ተበላች!

📚[ዑዩኑል አኽባር ሊብን ቁተይባህ 4/107)]

☞እኔም ይህን አልኩኝ⇩

በተከበረው ቤት- ካልጠፋ ለካፊ
በየመንደሩማـ ሞልቷል አነፍናፊ
ኒቃብ ተሰናብቶ ـ ተነስንሰው ሽቶ
ቀሚስ አጭር ሆኖـ ጅልባቡ ተረስቶ
ከቤትህ ሲወጡـ ሸይጣን አጅቦልህ
ቅናት ሳይሰማህ ـካየህ ዝም ብለህ
የሰው ውሻ ሲሆንـ የሴትህ አጃቢ
መሞት ይሻልሀልـ አፈር ተቀላቢ


https://t.me/abdurezaq27


بسم الله الرحمن الرحيم

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ አህቶች ላለፉት ጊዜያቶቾ ሲሰጡ የነበሩት(የሴቶች ብቻ) የኡሰታዝ ጣሀ አህመድ(ሐፊዘሁሏህ) ደርሦች ከዙም ወደ የኡስታዝ የቴሌግራም ቻናል መዘዋወራቸውን እየገለፅን ለዛሬ የሚኖረን፥

📣የረመዳን ሙሐደራ በቀጥታ❗

🌺ለሴቶች ብቻ

📆 ዛሬ እሑድ 17 April 2022

⏰ ሰዓት 2:30PM UK Time
4:30 Saudi
10:30 Ethio Time

🎙️በኡስታዝ ጣሀ አህመድ (ሐፊዘሁሏህ)

https://t.me/tahaahmed9




Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
የፆም አላማ ረሃብና ጥማትን እንዲሁም ጭንቅና መከራን መቋቋም መቻልን አካልን ማለማመድ አይደለም። ነገር ግን ለነፍሳችን ተወዳጅ የሆኑ ነገሮችን ይበልጥ ተወዳጅ ለሆነው ውዴታ ስንል መተውን ነፍሳችንን ማለማመድ ነው። የምንተዋቸው ተወዳጅ ነገሮች ምግብ፣ መጠጥና ወሲብ ሲሆኑ እነዚህን በመተው የሚፈለገው ውዴታ ደግሞ ልዕልናው ከፍ ያለው የአምላካችን አሏህ ውዴታ ነው።


📖(48سؤالا في الصيام ص10) ‎#ابن_عثيمين
‎#رمضان

https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
🌿ከፆመኞች ሁሉ በላጩ ማን ነው?

ኢብኑ-ል ቀይዪም ይህን ይላሉ ፦

"ከዒባዳ ባልተቤቶች ሁሉ የተሻለ የሚባለው በዒዳው ውስጥ እጅግ አላህን ማውሳትን (ዚክርን) የሚያባዛ የሆነ ሰው ነው። ልክ እንደዚሁ ከፆመኞች ሁሉ በላጭ የሚባለው ግለሰብ በፆሙ ውስጥ አላህን ማውሳትን (ዚክርን) በማብዛት የተሻለ የሆነው ሰው ነው።"

📚الوابل الصيب 152
https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
እናቴን ወይስ ሚስቴን?

☞ጥያቄ ፡ እናቴ ብቻዋን በጭርታ ውስጥ ነው የምትኖረው። በጣም እሰጋላታለሁ። ዘወትር አብራኝ ለመኖር፣ ጭርታዋን ለማስወገድና እንድንከባከባት አምርራ ትጠይቀኛለች። ሚስቴ ደግሞ ከእናቴ ጋር አብሮ መኖርን በፍፁም አትፈልግም። ይህን የእናቴን ሀሳብ በፅኑ ትቃወማለች። ሚስቴን ልታዘዝ ወይስ እናቴን?

☞መልስ ከሸይኽ ፈውዛን ፦ "ይህቺ ሚስትህ ከእናትህ ጋር የማትስማማ ከሆነ ለብቻዋ አኑራት። አንተ ከእናትህ ጋር ኑር። አልያም እናትህን እንድትንከባከብ የምትረዳህን ሌላ ሚስት ፈልግ። አለበለዚያ ሚስትህን ታዘህ እናትህን ችላ የምትልና ብቻዋን የምትተዋት ከሆነ ይህ ተግባር ወላጅን ከመበደል ውስጥ የሚመደብ ታላቅ ወንጀል ነው።"

📚المصدر / مجموعة رسائل دعوية ومنهجية ٢ / محاضرة الربا .ط. الامام احمد .ص١٨٩.ج
https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
♻️ታዋቂ ሳይሆን አዋቂ ሁን!

☞ሸሪዓዊ ርዕሶችን የሚመለከቱ ጭብጦች፣ ምልከታዎችና ትንታኔዎችን በብዕራችን ከመክተባችን፣ በአንደበታችን ከመናገራችንና በአእምሮኣችን ከማሰባችን በፊት በዚህ ርዕስ ላይ በቂ የሆነ የእውቀት ክምችት፣ ያልተዛባ የማስተላለፍ ብቃት እንዲሁም ሰናይ የሚባል እቅድ እንዳለን እናረጋግጥ። የኢስላም ሊቃውንቶች የተለያዩ ሸሪዓን የተመለከቱ ብይኖችንና ምልከታዎች ከመተንተናቸው በፊት አይኖቻቸው በሺዎች የሚገመቱ አያሌ ድርሳናትን ተመልክተው፣ መዳፎቻቸው ከአስር ሺዎች የሚልቁ ገፆችን አገላብጠውና ለዚህም መሰረታዊ ስንቅ የሚሆናቸውን ስር የሰደደ የፈጣሪ ፍራቻን አላብሰውት ነበር። በሸሪዓ ሚዛን ታዋቂነት በራሱ ተፈልጎ የሚለፋለት መሰረታዊ ግብ አይደለም። እንደውም በቀደምት አበዎች ዘንድ ታዋቂነትን መሻት ከመናፍቃን ተርታ የሚያስመድብ ሀጢያት ተደርጎ ተቆጥሯል።

አምሎኮኣዊ ድንበር የተበጀላቸው ነገሮች በአጠቃላይ ኢኽላስ የሚባል እጅግ ከባድ ድልድይ ተዘርግቶላቸዋል። ይህን ድልድይ ማለፍ የቻለ ብቻ ትክክለኛውን መቅሰድ ያሳካል። ይህን የተቀደሰ አላማ ባፈገፈገ መልኩ ዝናን መሻት የተቀላቀለበት ፅሁፍም ሆነ ድምፅ ብኩን መሆኑ እርግጥ ነው። የእውቀት ሽታን በወጉ ያላሸተቱ እጆችና ከእውቀት ነፃ አጃቢ የበዛላቸው ስብዕናዎች ይህን ትልቅ መርሆ በመሸሻቸው ሰበብ አስገራሚ ግትርነትና ማንነት ላይ ብቅ ይላሉ። ለጥቂት ግዜያት እጆች አፎች ላይ ተደራርበውና አይኖች ፈጠውላቸው የተደነቁ ፅሁፎች እንዲሁም ጆሮዎች የሚናፍቋቸው ድምፆች በእውነትም የአላህ ፊት ካልተፈለገባቸው ትቢያ ሆነው በአጭር ግዜያት ይበናሉ። በተቃራኒው እይታን የተነፈጉ የታፈኑ ፅሁፎችና ከማዳመጫ ታንቡር የሸሹ ድምፆች ሐቅ ተላብሰው የአላህ ፊት ከተሻባቸው በግዜ ሂደት ይጎመራሉ። በእውነትም ያብባሉ። ይህ ሁሉ በግዜ ሂደት የሚፈታ እንቆቅልሽ እንደሆነ እሙን ይሁንልኝ።

ለአላህ ተብለው የተሰሩ ተግባሮች ስራቸው ወደ ምድር እየሰደደ ፍሬያቸው እያበበ ሰዎችም ፈለጎቻቸውን እየቀጠፉና መአዛውን እየታወዱ ይዘወትራሉ። እውቀት ላይ ትእግስት የሌላቸው አካሎች በፍፁም መልካም ፍሬን ሊያፈሩ፣ ስብእናን ሊያንፁና የተንሻፈፈን ሊያቀኑ አይችሉም። ፅናትም አይኖራቸው። ተራ ዝና መሻት ይሰለቻል። ያደክማል። ከዝና ስር ተሰግስገው የተደበቁ እውነተኛ ማንነቶች ከእውቅና ማግስት ይፋ ሲሆኑ ግራ የሚያጋቡ አስገራሚ ስብዕናዎች ሆነው ብቅ ይላሉ።

እውቀት ከማንም በላይ ባለቤቱን ከቃላት ግድፈትና ከእሳቤ ብክነት እርምትን ይሰጣል። እውቀትና ኢኽላስ ያልጎተተው ዝና መኣዛው የጠነዛ፣ ቅምሻው የጎመዛና መጨረሻው መሳለቂያ ነው። ይህን ስል ሀቅ ተናጋሪ አፎችን ለመለጎምና ሀቅ ፀሀፊ እጆችን ለመጠምዘዝ አይደለም። በእውቀት ላይ ተቀምጠናል ብለው ለሚመፃደቁ ዝንጉዎች በፍፁም ብርታት አይሰጥም። ነገር ግን ሁሉም በልኩ እንዲራመድና ከደረጃው በላይ እንዳይንጠራራ ይሁን።

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
¨አግብታ የፈታች አልያም ባል የሞተባት ሴት ክብር!
—————————————————
አንዲት በሰሓቦች ዘመን የነበረች ሴት ባሏ የሞተ አልያም የፈታት ግዜ ሰሓቦች እሷን ለመንከባከብና ለመደገፍ ክብር በተላበሰ መልኩ ይቻኮሉ ነበር። የሰሓቦችን ታሪክ ብናገላብጥ አንዲት ሰሓቢይ ሴት አራት ሰሓቦችን በተለያየ ግዜ እንዳገባች እንረዳለን። አንዱ ሲሞት ሌላውን እያገባች ተከብራ ኖራለች። እሷን የመሰሉ ሴቶችን በንቀትና በጉድለት በፍፁም አይመለከቷቸውም ነበር።

ዐቲካ የምትባልን ሴት ተመልከት!። የታላቁ ሰሀቢይ አቡ በክር ልጅ አገባት። በጣም ታፈቅረው ነበር እሱም በቃላት ሊገለፅሉት በማይችል መልኩ ይንሰፈሰፍላታል። ከግዜያት ቡኃላ ሸሂድ ሆኖ ሞተ። ከዛም ታላቁ ሰሓቢይ ዑመር አል-ፋሩቅ አገባትና እሱም ሸሂድ ሆኖ ሞተ። ከዛም እሷን ለማግባትና ለማክበር የመልእክተኛው ሓዋሪይ የሚባለው ታላቁ ሰሓባ ዙበይር ኢብኑ-ል ዓዋም ተቻኮለ። አገባትም። ከጥቂት ግዜ ቡኃላም ሸሂድ ሆኖ ሞተ። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ሰዎች ሲሞቱ "በባሎቿ ላይ ሙሲባ የምታመጣ! "አልተባለችም። እንደውም "ሸሂድ መሆን የፈለገ ዐቲካን ያግባ!" ተብሏል።

የአስማዕ ቢንት ዑመይስን ታሪክ እናገላብጥ። የመጨረሻ ባሏ ታላቁ ሰሓቢይ ዐሊይ ኢብን አቢጧሊብ ነበር። ከሌሎች ባሎቿ የወለደቻቸውን ልጆች ያጫውታል። የሷን ጣፋጭ ንግግርና የልጆቿን ጨዋታ በመስማት በደስታ ፈገግም ይል ነበር። በቀደሙ ባሎቿ ላይ በፍፁም ቅናት አይሰማውም። "በቀደሙ ባሎችሽ ላይ ስሞቷ ብታሰሚ እቆጣሻለው! እነሱን በፍፁም በመጥፎ ስታነሺያቸው እንዳልሰማ። እነሱ ወዳጆቼ ናቸው።" ይላት ነበር። ሁሉንም አላህ ስራቸውን ይውደድ። የትኛዋም ሰሓቢያ ሌላ ባል ስታገባ የመጀመሪያ ባሏን እያወሳች በክህደት አልተጠረጠረችም።

የአላህ መልእክተኛም ከእናታችን ዐይሻ በስተቀር ድንግል ሴት አላገቡም። መጀመሪያ ትዳርን የመሰረቱትም ከሳቸው በፊት ትዳርን ከምታውቀው ከእናታችን ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ጋር ነበር። የተፈታችን አልያም ባል የሞተባትን ሴት ማግባት እንዲሁም ከአንድ በላይ ማግባት ስነ ምግባርን የሚጥስ፣ ክብርን የሚነካና የሚጠየፉት የወረደ ተግባር ቢሆን ቀድሞውንም ኢስላም ይከለክለዋል። ስነ ምግባርን፣ ልቅናንና እውነተኛ ሰብኣዊነትን ያስተማረን ኢስላም ነውና።

የተፈታች ሴት በፍፁም የውድቀት ምልክት አይደለችም። አላህን ከፈራች ከፍቺውም ቡኃላ አላህ ከችሮታው ያብቃቃታል። የተሻለ የህይወት መስመር ያበጅላታል። ከመጀመሪያ ባሏ የተሻለ መልካም የትዳር አጋር አላህ ሊሰጣት ይከጀላል። መጪው ቀናት በአላህ ፈቃድ መልካም ብስራትና ተስፋ ይዞ ብቅ ይላል። ስለዚህ አንገትሽን አትድፊ!

በሚያሳዝን ሁኔታ በአሁን ወቅት አግብታ የፈታችን ሴት ለማግባት የሚያስብ የሷን መብት ልክ እንደ አሮጌና ያገለገለ መኪና አስመስሎ ፕሮፖዛል የሚያቀርብ አለ። ይህ በሴቶች መብት ላይ ግፍና በደል ነው። ባል የሞተባት አልያም የፈታች እህትና ልጅ ቢኖረህ ለሷ የምትመኘውን ለሌችም እንስቶች መመኘት አለብህ። ይልቁንም የደረሰባቸውን ሀዘን ለመጠገን መሯሯጥ ይገባናል። በብዛት የሚያጋጥማቸውን ሞራላዊና ማህበረሰባዊ ተፅእኖ በመልካም ለመግፈፍ መታተር ይጠበቅብናል። በክፉ ከሚመለከቷቸው የሰው አውሬዎች ልንከላከላቸውና በደካማ ጎናቸው ለማጥቃት ካሰፈሰፉ ዋልጌዎች ልንጠብቃቸው የበኩላችንን ጥረት ማድረግ አለብን።

ስሜት ካወረው ፅልመት ተላቀን ሰብኣዊነት የተሞላ ኢስላሚዊ መንፈስ ይኑረን። ቁምነገሩ የኛ መልካም ስብዕና እንጂ የሷ የቀደመ ትዳር ተፅእኖ አይኖረውም። በብልሀትና በስነምግባር የተሞላ መልካም የትዳር አጋር ካገኘች በአላህ ፈቃድና ችሮታ ያለፈ ህይወቷን አስረስቶ ስኬታማ ትዳርን በሀሴት ይለግሳታል። ኋላ ቀር የሆኑ አባባሎች ጠፍረው አይከርችሙን። መመሪያችን ኢስላም ብቻ ይሁን።

በሙስሊም እህቶቻችን ላይ አላህን እንፍራ!https://t.me/abdurezaq27


እህቶቻችን ወደ ዲን ሲቀርቡ፣ ኒቃብ ሲለብሱ፣ ቁርኣት ላይ ሲያተኩሩ አቅማቸውን የሚፈታተኑ ብዙ ፈተናዎችን ያስተናግዳሉ። ይበልጥ የሚያመው ደግሞ ከውጪው በበለጠ በቅርብ ሰው የሚመጣው ፈተና ነው። ከዚህም ይበልጥ የሚያመው ወደ ዲን ከቀረበው፣ ሰበብ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ከሚጣልበት ወንድም የሚታየው ነገር ይበልጥ ሞራልን የሚያቀዘቅዝ፣ ስሜትን የሚጎዳ መሆኑ ነው። ቀጥሎ የማሰፍረው ከአንዲት እህት የደረሰኝ መልእክት ነው። መቼም የሁላችንም ልብ አንድ አይደለም። ምናልባት ቆም ብለን እናስብ ዘንድ በአላህ ፈቃድ የሆነ ያክል እገዛ ይኖረው ይሆናል።
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
አንዳንዴ ነገሩ ይከብዳል...
ብዙ እህቶች የሚወድቁበት የሆነ ብዙ ከባድ ፈተና አለ። በጣም ጠንካራ የሆኑት እንጂ የጠይቋቋሙት። ደግሞ ሴቶች ደካማ እንደሆኑ ታውቃለህ። የታላቁ ጌታ በፍፁም ከኔ ራህመት ተስፋ አትቁረጡ የሚል የተስፋ ቃል ባልነበረ ብዙ እህቶች ተስፋ በቆረጡ ነበር....

አሏህ ካዘነላቸው የሱና ወንድሞች ዉጪ ነገሩ እንዲህ ሆኗል ከዲን ይልቅ መልክ እድሜ ላይ በርትተዋል። መስፈርቶቹ ከአንድ ሰው ነው የሚላኩት ተብሎ እስኪጠረጠር ድረስ እንድ አይነት በመልክ ወላ በእድሜ ቀይ ቆንጆ እድሜዋ ከዚህ በታች ብዙ ኪታብ የቀራች የተማረች...ብዙ ብዙ ደግሞ እሱ ጋር ኖሮ ቢሆን እሺ።

ሁሉም ሴቶች ቀይ ናቸውን??
እሺ አንድ ሴት ቢያንስ መልኩንና ቂርዓቱን ብታሟላ እንዴት የተማረችና እድሜዋ ከዚህ በታች እንዴት ሊሆን ይችላል??
Maybe ሊኖር ይችላል ግን እጅግ ጥቂት ነው።

የምር እስኪ አንድ ወንድ ሱኒይ ሲሆን ወደ ሱና ሲጠጋ ፂሙን ይለቃል ልብሱን ከፍ ያደርጋል እና ሌሎችንም ነገሮች ይፈፅማል። የታዘዘውን ይሄን በማድረጉ ወሀቢይ ሊባል ይችላል እና ሌላም ፈተና ሊደርስበት ይችላል። ግን ሀቂቃ እንደ ሴቷ አይፈተንም። ሴቷ ኒቃብ ስትለብስ ሙተበሪጅ ሆና ዝም ያሏት ቤተሰቦቿ ሙተሀጂብ የሆነች ቀን ከገዛ ቤተሰቦቿ ፊትናው ይጀምራል። ከዛን ስራዋን ታጣለች። ሌላ ስራ ለማግኝትም ትቸገራለች። እቤት በገባች በወጣች ቁጥር አዛ ትደረጋለች። "እኔ ያስተማርኩሽ ለዚ አይደለም፣ እንደሷ አመድ አፋሽ ሆነሽ እንዳትቀሪ" እየተባለ ምሳሌ ይሰጥባታል። ሀታ በገዛ ቤቷ ባዳ የሆነች ያክል እስኪሰማት ድረስ። ታውቀዋለህ ግን ይሄ ስሜት ምን ያክል እንደሚያም?!! እኔ ግን በጭራሽ አመድ አፋሽ አልሆንኩም። እንዲያውም የጌታዬን እዝነትና ዉዴታን ነው ያፈስኩት። ከዚያም ደርስ ትከለከላለች። ግን የሚገርመው ደርስ ልትሄድ ልትቀራ "የትራንስፖርት አልሰጥም" ያለ ቤተሰብ ለዱንያዊ ትምህርት በሺዎች አውጥቶ ያስተምራል!!

ትራንስፖርት አጥታ በእግርም ቢሆን እየሄድኩ ቂርዓቴን እቀራለሁ ብላ በህመም ምክንያት ያቆመች እህት እንዳለችስ...??

ከዚህ ሁሉ መውጫ ዲኗንም ለመማር ያላት አማራጭ ኒካህ ማሰር እንደሆነ ታስባለች። በቤተሰቦቿ ቤት እንዳትቀራ ተከልክላለችና። ግን ለኒካህ የሚመጡ ወደ ሱና ተጠግተዋል የሚባሉ ወንዶች ይሄ ነው መስፈርታቸው አላህ ካዘነለት ውጪ። ቢያንስ ዲንን አስቀድመው ቢሆን፣ ዲን የላትም ብሎ ቢሆን የሚተዋት በጣም ደስ ይል ነበር።
እስኪ እናንተ የሱና ወንድሞች ካላዘናችሁልን ማን ያዝንልናል? ኢኽዋኑ!? አህባሹ!? በጭራሽ እነሱማ ሂጃባችንንም አቂዳችንንም ሊያጠፉ ነው ሚፈልጉት።

አልገጠመህምን አልሰማህምን ሱኒይ ሆና ኢኽዋኒ አገባች ሲባል?! አንድ የሱና እህት ከዚህ ሁሉ በቃ አስተካክለዋለሁ ብላ ኢኽዋን አግብታ በዛው የቀረች የተገለበጠች። ግን አንዳንዷ ደግሞ የሱና ጀግና እንጂ አይሆንም ብላ ትንሽ እድሜዋ ከፍ ካለ......የሱና ወንድ የሚባሉት ደግም የሚፈልጉት በእድሜ ትንሿን ነው። ሁሉንም እየወቀስኩ አይደለም። ደግሞ የፈለጉትን መሰፈርት ማውጣት መብታቸው ነው።
ማንም የፈለገውን መስፈርት ማድረግ መብቱ ነው ግን...???

አላህ ለነሱ ያለውን ሪዝቅ ማንም አይወስደውም ሶብር ማድረግ ነው አላህ የተሻለውን ምርጡን ያመጣል ግን ያው ሴቶች ደካማ አይደለን
አንዳንዴ ያቅታል። ህመማችን እንዲገባችሁ ነው ይህን የምለው።

ምን እንደምፈራ ግን ታውቃለህ? በፊት ኒቃብ ስለብስ ኡሚ አሪፍ ስራ ነው ያለሽ (የመንግስት ስራ ነበር የምሰራው) "ይሄን ስራ አትተይው። ሌላው ቢቀር ቢያንስ ኒካህ እስከምታስሪ ቆይ። እንዲህ ኒቃብ ከለበሽ ባል አታገኚም። ማን ያይሻል?" ብላኝ ነበር። እኔ ግን ለነፍሴ: "በጭራሽ አላህን በመታዘዝሽ ሪዝቅሽ ቢሰፋ እንጂ አይጠብም። እንዲያውም አላህን መታዘዝ ሪዝቅ ለመምጣት ሰበብ ነው" እያልኩ አበረታት ነበር የመንግስቱን ስራም ተውኩት፣ በኒቃብ መስራት አይቻልምና።
አሁን ግን ድሮም ነግሬሽ ነበር
እኔ ያልኩሽን ብትሰሚ ኖሮ ... መባሉ ያስፈራኛል።
እሷን ደስ ይበላት ብዬ የምወደውን ቂርዓት ትቼ እሷ ደስ የሚያሰኛትን ነገር እየሰራሁ ነው አላህ ነገሮቼን እስከሚያስተካክልልኝ ድረስ።

ኒቃብ ስለለበስኩ ኡሚ ለወራቶች ነው ያኮረፈችኝ። አብረን አንድ ቤት ውስጥ ሆነን ትናፍቀኝ ነበር። ሀቂቃ በጣም የሚያሳምም ነው ስሜቱ። ግን መፀናኛዬ ጌታዬ ነበር። እሱ ቅርብ የሆነ ሁሉን ነገር እያየልኝ እየሰማ ስለሆነ ደስ ይለኝ ነበር። ወሏሂ በጣም የሚያስከፋ ነገር ገጥሞኝ እኔ ግን ጌታዬን እያሰብኩ እስቅ ነበር። ሶብር በማድረጌ ከእሱ የማገኝውን አጅር እያሰብኩ እፅናና ነበር። አልሀምዱሊላህ በፊትም አሁንም በቃላትም በንግግርም ልገልፀው የማልችለው ሰላምና መረጋጋት ደስታ በውስጤ አለ።

ሌሎችም ኒቃባቸውን ቤተሰብ የሚያቃጥልባቸው በጣም ከባድ ፊትና የሚገጥማቸው ብዙ እህቶች አሉ። ከኔም የባሰ ብዙ አለና አብዝቼ ጌታዬን አመሰግነዋል ሁሌም። ኒቃቤ ለኔ ክብሬ ውበቴ ነው ከአጉል እይታ የሚከላከለኝ በጌታዬ ፍቃድ መጠበቂያዬም ጭምር። አላህ ከፊትና ይጠብቀንና የሞትኩ ቀን ቢሆን እንጂ አይወልቅም ኢንሻ አላህ። ዱንያ ላይ ያለውን ነገር ሁሉ እንስጥሽ ቢሉኝ እንኳን ወላሂ ሱመ ወላሂ እኔ በኒቃቤ አልደራደርም። ከፍ ያለው አላህ ለሁላችንም እስቲቃማውን ይስጠን።


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
⚡️ኢኽቲላጥና አደጋዎቹ ‼️

☘ኢብኑ-ል ቀይዪም፦

"ሴቶችን ከወንዶች ጋር እንዲቀላቀሉ ማመቻቸት የሁሉም ፈሳድና አደጋ መሰረት ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ይህ ተግባር ጠቅላይና ሁሉን አካታች ለሆነ ቅጣት ዋናው ምክንያት ነው። የወንድና የሴት መቀላቀል ለብልግናና ለዝሙት መንሰራፋት ዋናው ሰበብ ነው። ለጅምላ ሞት መበራከትም የዝሙት መስፋፋት አብይ ምክንያት እንደሆነ ይታወቃል። ይህም ሴቶች ከወንዶች ጋር እንዲቀላቀሉ በማስመቸት፣ በወንዶች መሀል ተገላልጠውና ተጋጊጠው እንዲጓዙ በመፍቀድ የሚመጣ አደጋ ነው። ሙስሊም መሪዎች ከዲኑ በፊት የዱንያና የህዝቡ መበላሸት ዋናው ሰበብ ኢኽቲላጥ መሆኑን ቢገነዘቡ ኖሮ ነገሩን ጠንከር ባለ መልኩ በመከልከልና አዳራሽ መንገዶቹን በመዝጋት ላይ በትጋት ይበረቱና ይጠነክሩ ነበር።"

#الطرق_الحكمية" (صـ 237) .

https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
⚡️በመረጋጋት ላይ አደራችሁን!!!

-فَعَلَيْكُمْ بِالتُؤَدَةِ ‼️
―――――――――――――
በዚህ ዘመን እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ እውቀት ፈላጊና አስተማሪ ከሆኑ በርካታ ግለሰቦች በስፋት እያነሰ የመጣው በጥልቅ የማስተዋል፣ የመረጋጋትና በዋናነት ደግሞ የስነምግባር ጉዳይ ነው። እርጋታ፣ ብስለትና ስነምግባር የዲኑ አንድ አካል በማይመስል መልኩ ሆደ ሰፊነት በሚያስፈልግባቸው ርዕሶች ላይ በየቦታው በወንድሞቻችን መካከል የሚታዩ ለከት የሌላቸው ነቆራዎች፣ ስድቦችና ያለ አግባብ ስም ማጠልሸቶች ተበራክተዋል። ሰዎችን ወደ ሐቅ ለማድረስ አቋራጭ የሚመስሉንን በሙኻሊፎች አልያም ተሳስተዋል ብለን ባሰብናቸው ወንድሞች ላይ የሚሰነዘሩ መረን የለቀቁ የጥላቻ ሰበካዎች በተዘዋዋሪ ዳዕዋችንን እየጎዳው ነው። ሁሉንም በልክና በብስለት ማስኬድ አፅንዖት የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት። እንዲሁም ከፊሉ በአቅሙ ልክ ውስን ዘርፎችን ሲሸፍን ሌላው ክፍተቱን እየሞላ ዳዕዋውን ማራመድ ካልተቻለ ትልቅ ክፍተት መፍጠሩ አይቀርም።
በዳዕዋው ውስጥ የተሳትፏችን ልክ በእውቀታችን መጠን የሚገደብ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። አንድ ሰው ስለሁሉም ተናግሮ ማስጠንቀቅና አዳርሶም ማስተማር አይችልም። አንተ የአቅምህን ከተወጣህ ሌላው ወንድምህም ከጎንህ የአቅሙን ካበረከተ ተጋግዘን በአላህ ፈቃድ በአጭር ግዜ ለውጥ ይመጣል። ነገር ግን እኔ የገባሁበት ካልገባህ፣ እኔ የታየኝ ካልታየህ፣ የኔን የዳዕዋ ስልት ካልተገበርክና እኔ ያስጠነቀኩትን ካላስጠነቀክ ብለህ ሽኩቻና ነቆራ በወንድሞችህ ላይ ከከፈትክ በተውሒድ ዳዕዋ ላይ እጅግ ከፍተኛ ችግር ትፈጥራለህ። መንገድህም ይረዝማል። ሸይኽ ኢልያስና መሰል ወንድሞች በዚህ ርዕስ ላይ የሚስተዋልባቸው እርጋታና ብስለት፣ ማስተዋልና ስክነት እንዲሁም መሰረታዉ እውቀት ላይ ትኩረት መስጠት ለብዙ ወጣት ዱዓቶች አስተማሪ ነው።
ሰዎች ዘንድ መታወቂያህ ስህተት መልቀምና ስህተት የመሰለህን በመሰብሰብ "ረድ" ማዘጋጀት ከዚያም በአቋራጭ መድረስ ሳይሆን መሰረታዊ የዐቂዳና ተያያዥ ርዕሶችን በማስተማር መሆን አለበት። በእያንዳንዱ ርዕስና አለመግባባት ላይ መልስ ካልሰጠው በተጨማሪም ተዕሊቅና ተድቂቅ ካላደረኩ ማለት እጅግ አስከፊ ውድቀት ውስጥ ይከተናል።
ከጥንት አበዎች አንስቶ እስከ አሁን ያሉ ሊቃውንቶች በቅድሚያ ህዝቡ ዘንድ የሚታወቁት በጀርሕና ተዕዲል ብቻ ሳይሆን በሚያሰራጩት እውቀት፣ በዒባዳቸው ትጋት፣ በስነምግባራቸው ምጥቀት ነው። እነዚህ ምስጉን ስብዕናዎች በነዚህ መልካም ባህሪያት ከመታነፃቸውም ጋር ከተለያዩ አንጃዎችና ግለሰቦች የሚነሱ ውዥንብሮችንና ማምታቻዎችን የአላህን ፊት ፈልገው፣ እውቀትና ስርኣትን በተላበሰ መልኩ መልስ ይሰጣሉ። ውጤቱም ምስጉን ይሆናል።

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
"የሒጃብ ቀን" ወይስ "የፈሳድ ቀን"?!

ኢስላም ራሱን የቻሉ ህልውናዎች ያሉት መሰረቱ የፀና በየግዜያቱ ልማድና ዘዬ በተከታዮቹ ከፍታና ዝቅታ ሙቀትና ቅሬታ የሚቀያየር እምነት አይደለም። መሰረታዊ ነጥቦቹን በየግዜው ብቅ ከሚሉ የከሀዲያን በቀል ተፅዕኖዎች ለመሸሽ በሚል ፈሊጥና ከዘመኑ ጋር እንራመድን ባዘለ ሙግት ፅኑ እሳቤው የሚገፈፍና በሸውራራ ምልከታና በዝንባሌዎች ማዕቀፍ የሚኮላሽ አይሆንም።

እርግጥ ነው ዘመናዊነትን ከኢስላም ጋር በማይጋጩ ነገሮች አጣጥመን ልንጠቀምበት ከዘመኑ ጋር ልንራመድ ህይወታችንን ልናቀልበትና ልናቀናበት ይገባል። ነገር ግን ኢስላምን ዘመናዊ እናድርገው ብለን ወደ ገደል የምንጎትተው እምነት ሊሆን በፍፁም አይችልም። አምላካችን አሏህ ይህን እምነት የደነገገውና የሰዎች መመሪያ ያደረገው እስከ ምፅዐት ቀን እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ዘመናቶች በተሻገሩ ቁጥር ኢስላምን በታወረ ልቦናችን የምንዘምትበት በአጠረ እውቀታችን የምንጠራራበት እምነት አይደለም። ፋይሉ ከ1400 አመታት በፊት ተዘግቷል።

የምዕራባዊያን ተፅዕኖ ያስበረገጋቸው በኢስላም ቀና ማለት ያቃታቸው በስሜት አለንጋ የተገረፉ ስብዕናዎች ኢስላምን እናዘምነው በሚል ወይም ቅቡልነቱን እናግነነው በሚል ሸውራራ እይታ ማህበረሰቡን ከትክክለኛው የኢስላም እሳቤ ወደ ወረደው አዘቅት እያወረዱት የቆመበትን ምንጣፍ እየጎተቱን ይገኛሉ። እውነት ነው አላህ እንዲህ ማለቱ ፦

"አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሀይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈፅሞ አይወዱም " አል-በቀራ 120

ከዛሬ ነገ እየከነፈ ሙስሊሟ ሴት እየተንሸራተተች የት ነው ያለችው? አንዱን ሲያስጥሏት እየወረደች አንዱን እያነሳች በመጨረሻም የእነሱን መንገድ በምልአተ ልቦናዋ ኮቴ በኮቴ እየተከተለች ትጓዝ ይዛለች። መታገል የመጀመሪያው ፈተና ላይ መሆኑን አላወቀችም። ድንበርህን አሳልፈህ ከሰጠህ ቡኃላ በሜዳህ ለሚጫወቱ አካላት መጫወቻ ትሆናለህ። አመቱን ሙሉ የሒጃብ ቀን ብለን ብናከብር የሒጃብን ልቅና በዚህ መንገድ ልናስጠብቀው በፍፁም አንችልም። ይባስ ብሎም ይህ አካሄድ ሴቶችን ከትክክለኛው የሒጃብ መፍሁምና ጭብጥ እያራቃቸው መጥቷል። ለዚህም ነው በየቦታው የቻይና ሱሪና ጠባብ ቀሚስ የታጠቁ ሙልጭልጭ ያለ ሂጃብ የለበሱ በጥቅሉ ማንነታቸው ግራ የገባቸው ሴቶች እንደ አሸን የፈሉት። ሀይ ባይ አጥተው ነውራችን የሆኑት። ግዜው በገፋ ቁጥር ነገሩም እየከፋ አበረታችና አጨብጫቢው እየፋፋ ሴቶችንም ለሐራም ማደኑም እየገፋ መጥቷል።

ፀጉራቸውን እንኳን በተገቢው መልኩ ያልሸፈኑ ብጥስጣሽ ጨርቆችን ከአናታቸው ላይ ጣል ያደረጉ በሰፋፊ ልብሶች መሸፈን ያለበት አካላቸው በጠባብና ባለ ወገብ ማሰሪያ ቀሚሶች ያሰሩና አካላቸውን የማይሰትሩ ቀሚሶች ያጠለቁ ከዚህ ሲከፋም ጠባብ ሱሪዎች ታጥቀው ብቅ የሚሉ እህቶችን ሰብስቦ "የሒጃብ ቀን" እያሉ ማጃጃል ትልቅ ውርደት ነው። የንፁህ ሴት ልጅ ክብርና መገለጫ የሆነውን ጌታዋን የምታመልክበትን ዒባዳ የሒጃብ fashion show በሚል ቀልድና ሞኝነት በወንዶች መንጋ መሀል ሲያመላልሷት እንዲሁም ቧልትና ዛዛታ በበዛበት መድረክ ላይ ወንድና ሴት ፍጥረቶች ያለ ግርዶሽ አፋጠው በሜክአፕ፣ በሊፒስቲክና .....የተበከለ ፊት በቅጡ ያልተሰተረ ማንነት የተከማቸበት ፕሮግራም እንዴት የሒጃብ ቀን ተብሎ ይሰየማል? በነሺዳ ስም የሚቅለሰለሱ ፓንክ ቁርጥ ሙነሺዶች የሚጣዱበት አብዛኞዎቹ ታዳሚያን ትክክለኛውን የሒጃብ መስፈርት ያላሟላ ሒጃብ ለብሰው የሚታደሙበት ፕሮግራም እንዴት የሒጃብ ቀን መሰናዶ ሊሆን ይችላል? በዚህ የፈተና ነፋስ በከፍተኛ ፍጥነት በሚነፍስበት ዘመን እሳትና ጭድን አቀራርቦ ደህና ምክር እንኳን መስጠት ከባድ መፍሰዳ ያስከትላል በሚባልበት እውነታ ከዛዛታው መሀል ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት? ምን አልባት ፕሮግራሙን ኢስላማዊ ለማስመሰል አንዲት ሙሐደራ ቢጤ ነገር ጣል ሊያደርጉባት ይቻል ይሆናል ይህም መሰረቱ በወደቀ ቤት ላይ ሚስማር እንደመምታት ነው።

እውነታውን ስንመለከት "ዓለም አቀፍ የሂጃብ ቀን" ተብሎ በፌብራሪ 1 የሚከበረውን በዓል አንዲት በአሜሪካ የምትኖር ትውልዷ ባንግላዲሽ ዜግነቷ አሜሪካዊ የሆነች በ 11 አመቷ ወደ ሀገረ አሜሪካ ከቤተሰቦቿ ጋር ተሰዳ የምትኖር እንስት በሂጃቧ ምክንያት በሚደርስባት ጫና ያስጀመረችው የሚዲያ ዘመቻ መሆኑ ነው። ማንም ቢሆን መልካም አላማን አንግቦ አንዳች ነገርን ይዞ በዲን ስም ከመነሳቱ በፊት በሸሪዓ ሚዛን ተለክቶና ተገምግሞ የኢስላም ሊቃውንቶችን ትክክለኛ ይሁኝታ ቁርኣንና ሐዲሥን አስደግፎ መስለሓና መፍሰዳው ታይቶ መሆን አለበት። የቢድዓ ጉዳይ ከሆነ ግን ምንም አይነት የቅቡልነት መንገድ አይኖረውም።

ሒጃብ አላህ ለሴቶች የደነገገው ጥበባዊና ፍትሓዊ የሆነ ሸሪዓዊ ልባስ ነው። አንዲት ሴት የጥብቅነትና የጨዋነት ምልክት ነው። በዚህ ርዕስ ላይ ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይ የኢስላም ልሂቃንና ሰባኪያን ሴቶችን ስለ ትክክለኛው ሒጃብ ሊያስተምሩ የመዳኛ መንገድ መሆኑን ሊጠቁሙ የክብሯ፣ የሀሴቷና የልቅናዋ ሰበብ መሆኑን ሊያስገነዝቧት ይገባል።

ነገር ግን አመት ጠብቆ የሒጃብ ቀን ብሎ ማክበርና ከዚህም የባሰው ደግሞ የዛን እለት ብቻ ሒጃብ የሚለበስበትና የተለያዩ እምነት ተከታዮችም እንደ ተራ ፌስቲቫል ሒጃብ ያሉትን ጨርቅ ጣል አድርገው ሲቀልዱ በተነሱት ፎቶ ሶሻል ሚዲያዎችን ሲያጨናንቁ ማየት ከባድ የሆነ ቢድዓና በውስጡም ተዘርዝረው የማያልቁ መፍሰዳዎችን ያካተተ ነው። ይህን ተግባር በፅኑ የሚኮኑንበት ሌላው ምክንያት በተለያዩ ቀናት እንዳሻቸው ክብረ በዓል ከሚያሰናዱ ከሀዲያን ጋር መመሳሰል መንገዳቸውንም መከተል ስላለበት ነው። ኢስላምም ከተደነገጉለት በዓላት ውጪ የተለየ ክብር በዓላትን በየትኛውም መልኩ አያስተናግድም።

ይህን መሰል ነገሮችን የሚያከብሩ ሰዎች በብዛት መስለሓ አለው በሚል ሙግት መሆኑ እርግጥ ነው። ይህን ሲሉ መሰለሓና መፍሰዳን ሚዛን ላይ አስቀምጦ ለመገምገም የሚያስችል የሸሪዓ እውቀትና የቀደመ ኢስላማዊ ልቀትና ምጥቀት ላይ ያሉ ሰዎች አለመሆናቸው ደግሞ ያስተዛዝባል። መፍሰዳና መስለሓን በሸሪዓ ምልከታ፣ በረቀቀ ግምገማና እይታ አላህን ፈሪ በሆነ ልቦና ተመልክተው ብይን መስጠት ያለባቸው በዘርፉ የተካኑ የኢስላም ልሂቃን ብቻ ናቸው። ከዚህ ውጪ በዲን ስም ቢዝነሱን እያጧጧፈ መስለሓ አለው ለሚልሽ ባተሌ ጆሮ አትስጪ ማመዛዘን የሚችለውን ዐቅልሽ አታከራይው ይልቁንም ለዲንሽና ለክብርሽ ዋጋ ስጪ። የመፍሰዳው ብዛት አለች የሚሏትን ጭላንጭል መስለሓ ላይ ቢቆለል አፍነው ይገሏት ነበር። ይህ የነሺዳና ዳንኪራ ጭብጨባ፣ በወንዶች መሀል በፋሺን ሾው ስም ያለ ዕፍረት የሒጃብን መስፈርት በማያሟላ በተጋጌጠና በተቆራረጠ የጨርቅ ቅጥልጣይ ልብስ መመላለስና መሰባበር፣ ኢኽቲላጥና ዛዛታ ሌሎችም ሙንከራቶች እውነት ወደ አላህ የሚያቃርበን ዒባዳ ነውን? በፍፁም!!!

#yes_to_hijab_no_to_hijab_day

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
ወደ ኢስላምና መጣራትና "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት?!

ከኢስላም ውጪ ያሉ የማህረሰብ ክፍሎችን እምነታቸውን መሰረት ያደረጉ በዓላቶቻቸውን ሲያከብሩ "እንኳን አደረሳቹህ!" አልያም "እንኳን ደስ አላችሁ!" የሚሉ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ግለሰቦች ምን አልባት አብዛኞቹ አንድም ቀን ተሳስተውም ቢሆን እነዚህን ሰዎች ወደ ኢስላም ተጣርተው የማያውቁ ናቸው። ሞራሉም የላቸውም።

ግዴታ የሆነውን ሰዎችን ወደ ኢስላም መጣራትን ትተው በተከለከለው የኩፍር ድግስ ላይ የሚረባረቡት ለምን ይመስላችኋል? ለዚህም ጀብዳቸው የውስጥ ሽንፈታቸው የወለደውን ሆደ ሰፊነታቸውን እንደ ሰበብ ሲያባክኑና ሌላውን በአክራሪነት ሲፈርጁ ይስተዋላል።

በክህደቱና በኩፍሩ ላይ "እንኳን ደስ አለህ!" ያልከውን ሰው በምን አፍህ ነው "ይህ ያለህበት እምነት ስህተት ነው!" ለማለትና ወደ ኢስላም ለመጥራት ሞራሉ የሚኖርህ?! ምን አልባት ይህ ግለሰብ ኢስላምን ያወቀ እለትና አሏህ ወደ ኢስላም የመራው ቀን ይታዘብኃል። ከሁሉ በላይ ደግሞ አሏህ የምትሰራውን ይመለከታል!!!

እስኪ እናስተውል!

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا (140)


"በእናንተም ላይ በመፅሀፉ ውስጥ የአሏህን አንቀፆች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ግዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነርሱ ጋር አትቀመጡ። እናንተ ያን ግዜ ብጤያቸው (አምሳያቸው) ናችሁና። አሏህ መናፍቃንን እና ከሓዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና።" [ሱረቱ-ል አን' ኒሳእ: (140)]

የአሏህ አንቀፆች ሲካድባቸውና ሲላገጥባቸው እየተመለከቱ አብሮ መቀመጥ በጥብቅ ከተከለከለና እንዲሁም በዚህ በክህደት ድርጊት ላይ አብሮ መቀማመጥን ካልተዋችሁ የእነርሱ የከሃዲዎቹ አምሳያዎች ናቹህ ከተባለ፣ በእነዚህ የአሏህ አንቀፆች ሲካድባቸውና ሲላገጥባቸው "እንኳን ደስ አላቹህ!" እና "እንኳን አደረሳቹህ!" ማለትስ እንዴት ሊሆን ነው? ጥንቃቄ ያስፈልጋል!!

ለዚህም ሲባል ነው አንድን ግለሰብ አስቀያሚውን ዝሙት ሲፈፅም፣ ሲሰርቅ፣ ሲዋሽና የመሳሰሉ ከባባድ ወንጀሎችን ሲተገብር "እንኳን ደስ አለህ በርታ!" ከማለት በላይ በክህደት በዓላት ላይ "እንኳን ደስ አለህ!" ማለት የበረታ ወንጀል እንደሆነ ኢብኑል ቀይዪምን የመሳሰሉ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች የሚጠቁሙት!!
29/4/2014
https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
⚡️ሸይኽ ሷሊሕ አል-ዑሰይሚይ

"ጁሙዓ አሏህን የመታዘዝ ቀን ናት። በእርሷ ውስጥ አሏህ ዱዓን የሚቀበልበት፣ ባሪያው የጠየቀውን የሚሰጥበት፣ ምኞቱን የሚያገኝበትና ፍላጎቱን የሚቸርበት ለየት ያለች ወቅት አለች። ስለዚህ ከእርሷ አትዘናጉ። ይህችን ወቅት በጁሙዓ እለት መገባደጃ ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ተጠባበቋት። አላህ እንደሚቀበላቹህ እርግጠኞች ሆናችሁ ዱዓን አድርጉ። ጌታችሁ ቸር ነው።"
https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
"እኔ ብቻ ትክክል ነኝ!"
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
☞ኢብኑል ቀይዪም፦

በሁሉም መልኩ ተበዳይና ሐቅ ላይ ነኝ የሚሉ ሰዎች እጅግ በርካታ ናቸው። ነገሩ ግን እንደሚገምቱት በፍፁም አይሆንም። እንደውም ይህ ግለሰብ በአንድ በኩል ሐቅ ሊኖረውና በከፊል ደግሞ በደልና ባጢል ሊኖርበት ይችላል። ባላንጣው ዘንድ ደግሞ ሐቅና ፍትህ ሊኖር ይችላል። አንድን ነገር መውደድህ እውርና ዲዳ ያደርጋል። የሰው ልጅ ነፍሱን በመውደድ ላይ የተፈጠረ ነው። የነፍሱን መልካሟን እንጂ ሌላን አይመለከትም። ተቃራኒውን ይጠላል። የተቃራኒውን መጥፎ ነገር እንጂ አይመለከትም። እንደውም ራስ ወዳድነቱ በርትቶበት የነፍሱን ክፋት እንደ መልካም መመልከት ይጀምራል። ልክ አሏህ እንዳለው፦

{أفمن زين له سوء عمله فرآه حسناً}
سورة فاطر

"መጥፎ ስራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?)"

በዚህም ባላንጣው ላይ ያለው ጥሩ ጎን መጥፎ እስኪመስለው ድረስ ጥላቻው ይበረታል።

ለዚህም ሲባል እንዲህ ተብሏል፦ "በጥላቻ ዓይናቸው ተመለከቱት እንጂ በመልካም ዓይን ቢመለከቱ ኖሮ የጠሉትን ነገር ባወደሱ ነበር!"

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
⚡️ሸይኽ ሷሊሕ አል-ዑሰይሚይ

"ጁሙዓ አሏህን የመታዘዝ ቀን ናት። በእርሷ ውስጥ አሏህ ዱዓን የሚቀበልበት፣ ባሪያው የጠየቀውን የሚሰጥበት፣ ምኞቱን የሚያገኝበትና ፍላጎቱን የሚቸርበት ለየት ያለች ወቅት አለች። ስለዚህ ከእርሷ አትዘናጉ። ይህችን ወቅት በጁሙዓ እለት መገባደጃ ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ተጠባበቋት። አላህ እንደሚቀበላቹህ እርግጠኞች ሆናችሁ ዱዓን አድርጉ። ጌታችሁ ቸር ነው።"
https://t.me/abdurezaq27


⚡️የሸረሪት ቤትና የጣዖታዊያን ምሳሌ!

☘አጫጭር የተውሒድ ትምህርቶች☘

☞ቁጥር ①

🎙ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27


Abdur-Razzaq||Al-Habeshi dan repost
☘የማለዳ ፈዋኢዶች¹¹☘

"ታላላቅ ስብእናዎችን መገንባትና ማነፅ ከፈለግን በዲን የታነፁ እናቶችን ልናፈራ ይገባናል። ይህን ታላቅ ትውልድ ማግኘት የምንችለው ሴቶችን ዲናቸውን በማስተማርና በኢስላማዊ ተርቢያ ማሳደግ ከቻልን ብቻ ነው። ነገር ግን ሴቶቻችንን ዲናቸውን የማያውቁ ሆነው በመሀይምነትና ፅልመት ላይ ከተውናቸው በፍፁም ታላላቅ የኢስላም ስብእናዎችን እናፈራለን ብለን መጠበቅ የለብንም።"

🪴 ~ #آثَار ابن باديس رحمه الله (٢٠١/٤)
https://t.me/abdurezaq27


ጣዕረ—ሞት‼️

ሞት የተጣደው ሰው ላይ መላእክቶች ይወርዳሉ። ከአጠገቡም ይቀመጣሉ። ወደ ሞት እየተጓዘ ያለው ሰውም በአይኑ ይመለከታቸዋል። እርሱ ዘንድ ያወራሉ። ከጀነት ወይም ከእሳት የሆነን ሐኑጥና ከፍን ይይዛሉ። ማቹ ዘንድ ያሉ ሰዎች በክፉም በመልካምም የሚያደርጉትን ዱዓ ተቀብለው አሚን ይላሉ። ጣዕረ ሞት ላይ ለሆነው ሰው ሰላምታን ያቀርቡለታል። ሰውዬውም ሰላምታውን በአንደበቱ አልያም በምልክት መናገርና ማመላከት ካልቻለ ደግሞ በቀልቡ ይመልስላቸዋል። በእርግጥም ጣዕረ ሞት ላይ ካሉ ሰዎች ይህን አይነት ነገር ተከስቷል። "አህለን ወሰህለን እንኳን ደህና መጣችሁ! እነዚህ ፊቶች" ብለዋል። ሸይኻችን ጣዕረ ሞት ላይ ከነበሩ ሰዎች ተነግሮት ይሁን አይቶ አላውቅም እንዲህ ብሎ ነግሮኛል "ጣዕረ ሞት ላይ ያለ ሰው "ዐለይከ ሰላም" እንዳሉ ሰምቻለሁ።

ኢብኑ አቢ ዱንያ ይህን ጠቅሷል "ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዐዚዝ የሞተበት ቀን ላይ ቤተሰቦቹን "አስቀምጡኝ" አለ። ቤተሰቦቹም "አስቀመጡት"። እርሱም "እኔ ነኝ አዘኸኝ ትእዛዝህን ያጓደልኩ! እኔ ነኝ ከልክለኸኝ ያመፅኩ" እያለ ሶስት ግዜ ደጋገመ። ከዚያም "ነገር ግን ላ ኢላሃ ኢልለ ላህ" አለ። ከዚያም አይኑን ከፍ አድርጎ በአትኩሮት ወደ ላይ ተመለከተ። አጠገቡ ያሉ ቤተሰቦቹም "የአማኞች መሪ ሆይ! በጣም አፍጥጠህ በአትኩሮት እየተመለከትክ ነው ምንድነው?" አሉ። እርሱም "እኔ አሁን ሰውም አጋንንትም ያልሆኑ አካላቶች ቀርበው ይታዩኛል" አለና ሞተ።

ፈዳለቱ ኢብኑ ዲናር እንዲህ ብለዋል "ሙሐመድ ኢብኑ ዋሲዕን ጣዕረ ሞት ላይ ሆኖ አገኘሁት። እንዲህ እያለ ነበር "የጌታዬ መላእክቶች እንኳን ደህና መጣቹህ! ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ! ከዚህ በፊት አሽትቼው የማላውቀውን ጥሩ መኣዛ እያሸተትኩ ነው።" አለና ወዲያውኑ አይኑን አንጋጠጠና ሞተ።"

📚አ-ር'ሩሕ ኢብኑል ቀይዪም

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

1 838

obunachilar
Kanal statistikasi