💞ፍቅር ያሸንፋል💕
ክፍል አራት (4)
እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛
ከካሌብ ጋር ሆኜ አባቴ ሲመጣብን ሁለታችንም ተቃቅፈን እንደ ሀውልት
ነበር ደርቀን የቀረነው ይሄን ሲያይ ወግ አጥባቂው አባዬ በጣም በንዴት ጦፎ ለማውራት እራሱ ቃል አጠረው እጄን ከካሌብ ላይ አስለቅቆ እየጎተተኝ እቤት አስገባኝ እስከዛች ደቂቃ ምንም ማለት አልቻልኩም ከዛም አባዬ በጣም ተናዶ ስለነበር ሰውነቴ ውሃ እስኪቋጥር ተገረፍኩ ማፍቀሬ እንደ ሀጥያት ተቆጠረ እኔ ግን እንደዛ እየተመታው ያሳስበኝ
የነበረው መገረፌ ህመሙ ሳይሆን የካሌብና የኔ መጨረሻችን ምን
እንደሚሆን ነበር፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ወቅቱ ክረምት ስለነበር ከቤት መውጫ ሰበብ አጣሁ እቤትም ቁጥጥሩ በዛ እማዬ ሱቅ እንድትልከኝ ብዙ ግዜ ስለምናት አባቴ
ማስጠንቀቂያ ስለሰጠ አይፈቀድልኝም መኝታ ቤቴን ዘግቼ ስለሱ እያሰብኩ ከማልቀስ ውጪ ምንም ምርጫ አልነበረኝም ምግብ አስጠልቶኛል በዛ ላይ አባዬ አዋረድሽኝ እያለ ከዱላው በላይ ቅስም የሚሰብር ንግግር ይናገረኛል ምን አለ እንዳሁኑ ስልክ ቢኖር በምን እድላችን ግን የለም ልክ ይህ በሆነ በሳምንቱ የካሌብ እህት ሜሪ መጣች ሀሙስ ቀን ነበር አባዬ ቢያያት በርግጠኝነት ያባርራት ነበር ግን
ስላልነበረ ለትንሽ ደቂቃ አወራን ስለካሌብ ስጠይቃት በኔ ምክንያት እየተጎዳ እንደሆነ ነገረችኝ ከዛም ከካሌብዬ የተላከልኝ ደብዳቤ ሰታኝ አባዬ ሳይመጣ ቶሎ ብላ ሄደች፡፡ ልክ ስትወጣ ደብዳቤውን ገልጬ ማንበብ ጀመርኩ እንዲ ይል ነበር "የኔ ፍቅር እንዴት እንደምነግርሽ አላውቅም አባትሽ እንዲገርፉሽ ማድረጌ ጥፋተኛ ነኝ ይቅር በይኝ የኔ ልዩ እመኚኝ እክስሻለሁ ውዴ
እኔ አዲስ አበባ መሄዴ ግድ ሁኗል ይዤሽ ብሄድ ደስ ባለኝ ግን አባትሽ እንዲያዝኑብን አልፈልግም የኔ ፍቅር የትም ብሆን ግን አፈቅርሻለሁ ነገ መስኪድ ልሂድ ብለሽ ውጪና ተሰናበቺኝ
የለመድነው ቦታችን ጋር እጠብቅሻለሁ " ይላል እንባዬን መቆጣጠር ተሳነኝ ከተቀመጥኩበት ተነሳው ተመልሼ
ተቀመጥኩ ግራ ገባኝ ሌሊቱን ሙሉ ስለሱ ሳስብ አደርኩ በመጨረሻም አንድ ነገር ወሰንኩ ከካሌብ ጋር መጥፋት አለብኝ ጠፍቼ ከሱ ጋር እንኳን አዲስ አበባ ሲኦል ብገባ በደስታ እኖራለሁ ይህን አስቤ ግዜ ሳላጠፋ ልብሴን አሰናድቼ ጎረቤት አስቀመጥኩ ከረፋዱ 5፡00 ላይ ጁምአ እንደሚሰግድ ሰው
ተጣጥቤ ካሌብ የቀጠረኝ ቦታ ሄድኩ ልክ ስደርስ እየጠበቀኝ ነበር እረጅም ግዜ እንደተለያየ ሰው ተቃቅፈን አነባን ከዛ ከሱ ጋር ጠፍቼ አብሬው ለመሄድ መወሰኔን ነገርኩት በመጀመርያ እምቢ ብሎኝ ነበር ከዛ ግን በስንት መከራ በሀሳቤ ተስማምቶ ለሊት 11፡00 ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘን ተለያየን፡፡ እቤት እንደገባው አባቴ እና እናቴ ተቀምጠው እያወሩ ነበር የደረስኩት ሰላምታ ሰጥቻቸው ወደ ክፍሌ ገብቼ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ማልቀስ ጀመርኩ ለምን እንደማለቅስ ግን አልገባኝም ነበር፡፡
በእንደዚ አይነት ሁኔታ ከምወዳቸው ከቤተሰቦቼ እና ቤቴ መለየቴን በጣም ነበር ያሳዘነኝ ምን ታረጉታላቹ ፍቅር ሲይዝ እውር ያደርጋል ይላል ያገሬ ሰው
እሄ ሁሉ መስዋእት ለፍቅር ስለሆነ ምንም አልመሰለኝ❤️ እናም ከእናትና ከአባቴ ይልቅ ፍቅሬን መርጬ ከካሌብ ጋር ለመጥፋት ወሰንኩ ፡፡ ሰዓቱ ደረሰ እኔም ጠፍቼ ከቤት ወጥቼ ፍቅሬ ጋር ከተቀጣጠርኩበት ቦታ ደረስኩ ፍቅሬን እቅፍ አድርጌ ስሜ ተያይዘን ወደ መናሀሪያ ገብተን የአዲስ አበባ አውቶቢስ ውስጥ ገብተን ጉዞ ጀመርን
ጉዞ ወደ አዲስ አበባ …………….
ኑሮን በአዲስ አበባ ……………
ኑሮን በአዲስ አበባ ሀ ብለን ጀመርን ማንም ረዳት በሌለበትና ሁሉም ለራሱ ለፍቶ አዳሪ በሆነባት ከተማ ኑሮ እንዳሰብነው ቀላል አልነበረም በርግጥ ካሌብዬ ለመማር ስለመጣ ብር ይላክለታል ግን ከቤት ኪራይና ትምህርት
ቤት ክፍያ የዘለለ ትርጉም የለውም፡፡
ስለዚህም የግድ መስራት አለብኝ ካሌብዬ እንድማር ቢፈልግም እኔ ግን እሱ ይቅደም ብዬ በተከራየንበት አካባብያችን ያለ ሆቴል በፅዳት ተቀጠርኩ.......ይቀጥላል
✎ ክፍል አምስት(5) ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like & Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
┄┄┉┉✽✽✽ ┄┄┉┉
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
💗💗------💗💗------
💛 @yefkr_kalee 💜