🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏
በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው አህያና ፍየል ነበረው፡፡ አህያውን ሁሌ ከተማ ወስዶ የሚሸጣቸውን እቃዎች ለማጓጓዣነት ይጠቀምበታል፡፡ አንዳንዴም በእሱ ለመገልገል የሚፈልግ ካለ በገንዘብ ያከራየዋል፡፡
አህያው ቀኑን ሙሉ በርትቶ ስለሚሰራ ባለቤቱ ሁሌም ከፍየሉ የበለጠ ምግብ ይመግበው ነበር፡፡ በዚህም ፍየል ቅናት በልቡ ላይ አደረ፡፡ መጥፎም አስቦ ለአህያው እንዲህ ሲል መከረው፡፡
"ቀኑን ሙሉ ያለምንም ዕረፍት ትሰራለህ፤ የግድ እንደታመመ መስለህ መሬት ላይ መተኛት አለብህ፤ በዚህ ቢያንስ የተወሰነ እረፍት ታገኛለህ፡፡"
አህያው በዚህ ምክር ተስማማ፤ እናም የታመመ መስሎ መሬት ላይ ተዘረረ፡፡ ባለቤቱም የእንስሳት ሀኪም ጠርቶ አሳየው፡፡ ዶክተሩም "አህያህ በአስደንጋጭ ሁኔታ ነው የታመመው፤ ለማዳን፣ ተጠግኖ ወደ በፊት ስራው እንዲመለስ የግድ ከፍየል ሳንባ የተሰራ ሾርባ መጠጣት አለበት" በማለት ለባለቤቱ ነገረው፡፡
ባለቤቱም ፍየሉን አርዶ ከሳምባው ሾርባ ሰርቶ አህያውን አጠጣው፡፡ ፍየሉ በነበረው ክፉ ተፈጥሮ አህያውን ለመጉዳት ሲል የእራሱን ህይወት አጣ፡፡
#ጭብጥ ፡- ለእኛ ደግ ያሰቡ መስለው ገለው ሊቀብሩን በየቀኑ ስለታቸውን የሚስሉ በርካቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን እመኑኝ ፈጣሪ ልጆቹን ለጠላት አሳልፎ አይሰጥም አንፍራ፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር የሚጠብቀው ትዕዛዙን የሚጠብቁትን ነውና እሱን የሚያስከፋ አንዳችም አናድርግ፡፡
እኛ ከክፋት በመነጨ መልኩ በሰዎች ህይወት ላይ ስንፈርድ የፈጠረን አምላክ በእኛ ህይወት ላይ ይፈርዳል፡፡
ከክፋት አዝመራ የሚታጨደው እንክርዳድና ገለባ ብቻ ነው፡፡ ሁሌም ለሰዎች መልካም እናስብ፤ መልካም እንስራ፤ በሌላ በኩል ፈጣሪ በእጥፉ ለእኛ ያስባል፡፡
#ለኔ ና ለእናተ ምክር ነክ
https://t.me/Abalibanos333