↪️ የሀዲያን ህዝብ የማክፈር ዘመቺያ በተለያዩ ዘመናት!
ክፍል ሁለት
ክፍል አንድን ለማግኘት ይህን ይጫኑ
https://t.me/sunnatewhid/222
🔷 ጦረኛ በማዝመት ሰይፍ በመምዘዝ የማክፈር ሂደት። ይህኛው ሂደት የተጀመረው የሠለሞናዊው ስርወ-መንግስት ወደ ስልጣን ከተመለሰ ወዲህ ነበር። ለጉዳዩም ትኩረት በመስጠት ክብረ-ነገስት በሚሰኘው የክርስቲያኑ መንግስት መፅሐፍ ውስጥ የክርስትያኑ መንግስት የሀዲያ ሙስሊሞችን ዘመናትን የተሻገሩ ጠላቶች ብሎ ከሌሎች ሙስሊሞችም ጋር ጨምሮ አስፍሯቸዋል። በጠላትነት ከመፈረጅም አልፎ ወደ ከፋ ጦርነት የተሻገረው ንጉስ አምደ-ፂዮን ስልጣኑን ከተቆጣጠረበት 1314-1344 E,c ጀምሮ ነበር። ከሱበፊት የነበሩ ነገስታት በውስጥ ለውስጥ የስልጣን ሽኩቻላይ ስለነበሩ በሀዲያው ሱልጣኔት ለመዝመት አላስቻላቸውም ነበር አምደ-ፂዮን ከነገሰ ወዲህ ግን የውስጥ ችግራቸውን ለግዜው ትቶት ቀጥታ ወደ ሀዲያ ሱልጣኔ ጦር አዘዘ የመጀመሪያውንም ዘመቻ 1316-1317 ነበር። በዚህ ጦርነት በሙስሊሞች ያደረሰው በደል በጥቂቱ ለመዘርዘር፦
* ብዙዎችን ጨፈጨፈ። ከዚያም ሲደክመው መሪያቸውን ጨምሮ ሽማግሌ፣ ህፃናት፣ ሴት በምርኮ ወደ ግዛቱ አጓጋዘ። በዚህ ጦርነት ክርስትያኖቹ ቢያሸንፋም ሙስሊሞችን ሀይማኖታቸውን ማስቀየር አልቻሉም። በግዜው የሱልጣኔቱ መሪ መስጅድ አታፍርስብን ሀይማኖታችንን አትንካ ግብር እንከፍላለን ብሎ ለመዋጋት አቅም ስላልነበረው ጥያቄ አቀረበለት በግብሩ አፄው ተስማማ። በተጨማሪም በየአመቱ አንዲት ውብ የሆነች ኮረዳ ሴት ከተከበረ ቤተሰብ ተመርጣ ለንጉሱ እንድትገበር አስገደዳቸው። በየአመቱ ከሀገሩ ቆንጆ የባለ-አባት ሴት ልጅ መርጠው፣ አጥበው ሳትሞት ይገንዟትና ሰላተል ጀናዛ ሰግደውባት ለንጉሱ ይገብሯት ነበር። እዛ ከሄደች መክፈሯ ስለማይቀር መክፈሯን እንደ ሞት በመቁጠር እሄን ያደርጉ ነበር። በዛን ግዜ የነበሩ የሱልጣኔቱ መሪዎችም ይሁን ተመሪው ሸሪአዊ እውቀት በጥልቅ አያውቁም ነበርና ለዚህ ነው እንደዛ ያደረጓት ይባላል። ከግብሩም በተጨማሪ ፈረስ ያለኮርቻው እንዲጋልቡ፣ ሰይፍ በፍፁም እንዳይዙም ማእቀብ ጣለባቸው።
🔷 ከሙስሊሙ መህበረሰብ ለነሱ ታመኝ መሪ ማስቀመጥ። በአፄ ዘርዓ-ያዕቆብ ግዜ ገራድ-ማኢቆ ሙሀመድ ለንጉሱ ላለመገበር ሙስሊሙን ከክርስቲያን ንጉስ ለማስጠበቅ ከአዳል ወንድም ሱልጣኔቶች ጋር ተስማምቶ ዝግጅት ላይ ነበር። ነገር ግን አፄው በአካል ግዛቱ ላይ ባይኖሩም ከሙስሊሞች በኩል ለአፄው ታማኝ ቅጥረኛ ነበረው። የሀዲያ ሌላኛው ጋራድ (መሪ) ይህንን እቅዱ ቀድሞ ለአፄ ዘረዓ-ያዕቆብ በማጋለጥና ከጎኑ በመሆን ሙስሊም ወንድሙን ተዋጋው። አፄውም ለዚህ ተግባሩ ማመስገኛ ብዙ ስጦታ እና ጌጦችን ለገሱት። በዚህም ግዜ የሀዲያው ሙስሊሙ ሱልጣኔት በክፋኛ በወንድሙ እና በጠላትቱ ተዳከመ። የክርስትያኑ መንግስትም ከራሱ ግዛት ሹማምንት መርጦ በሙስሊሙ ግዛት አሰፈራቸው ህዝቡም በግዳጅ ለአፄው እጅ ነሳ። ሀይማኖቱን ለማስጠበቅ ሲል መገበሩንም ቀጠለ።
ክፍል ሶስት ይቀጥላል
https://t.me/sunnatewhid