↪️ ለራሴ የገጠመኝ እና እውነተኛ ታሪክ
* ክፍል አምስት
በተመሳሳይ ሁኔታ እዛው ሰፈር ከተወሰነ ጊዜ ቡሀላ መብረቅ በቤት ላይ ወረደ። እና በትንሹ ከዚህ ቤት ጋር በተያያዘ ያጋጠመኝ ነገር ልንገራችሁ። በሰዓቱ እኛ "ታርቤ ማዞሪያ መስጂድ" ቁርአን እየቀራን አንድ የሰፈር ልጅ ከኢሻ ሶላት በኋላ ደዉሎ ትንሹ ወንድሜ ከናንተ ጋር ነው ወይ ብሎ ለጓደኛችን ይጠይቀዋል። የተደወለበት ልጅ ለማናገር ውጪ ወጥቶ ከዳገት ወደታች አርጎ ሲያይ እሳቱ ይታያል። እኛም ከልጆቹ ጋር ወደዚያ ወረድን።
ቤቱ ጋር ስንደርስ ሰው በጣም ተሰብስቧል። ማታም ስለሆነ ሰው እሳት በማጥፋት እየተረባረበ ነው ስንል ነገሩ ግን እንደዛ አይደለም። በጣም አንገት የሚያስደፋ ነገር ብነግራችሁ እኛ ስንወርድ የዛ ቤት እናትና ሌላም የሰፈር እናቶች ለእሳቱ ሱጁድ ወርደው ነበር። የዛ ቤት እናት አጎንብሳ ተመልሻለሁኝ ጥፋቴ አውቄያለሁኝ ትላለች። እኛም ኧረ አላህ ፍሩ ስንላቸው የዛ ቤት እናት ኧረ ተውኝ አለችን ሌሎችም በተመሳሳይ። ወንድሞቼ እንደነገሩኝ ለእሳቱ ሱጁድ ከወረዱ ሴቶች ጭራሽ የጁማአም ሰላትም ይሁን የኢድም ሰላት እንኳን የማይሰግዱ ነበሩ አሉኝ.... ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን። አላህ ﷻ በቁርአኑ እንዲህ ብሏል፦
{وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ} فصلت ٣٧
"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደ ኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡"
ተመልከቱ አላህ ከትላልቅ ተአምሮች ጠቅሶ ለነሱ አትስገዱ ይለናል። ከነሱ በታች ያለውማ ለሱ ሱጁድ ማድረግ የበለጠ የተከለከለ ነው። ከዛ ቀጥሎ ለነሱ ጌታ ለአላህ ብቻ ስገዱ አለ። ከአላህ ውጭ ላለ ነገር መስገድ ተዉሂድን ይንፃረራል። ነቢያች ﷺ በሀዲሳቸው፦
عن عبدالله بن أبي أوفى رضي الله عنه، قال: قال النبي ﷺ :" لو كُنتُ آمراً أحداً أن يسجُدَ لغيرِ اللَّهِ، لأمَرتُ المرأةَ أن تسجُدَ لزوجِها. والَّذي نَفسُ محمَّدٍ بيدِهِ، لا تؤدِّي المرأةُ حقَّ ربِّها حتَّى تؤدِّيَ حقَّ زوجِها "[رواه ابن ماجه (1853)، حسنه الألباني]
ከአብደላህ ቢን አቢ አውፋ እንደተዘገበው አላህ ኸይር ስራቸውን ይውደድላቸውና ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ፡- “ከአላህ ውጭ ላለ አካል እንዲሰገድ ባዝ ኖሮ ሴትን ለቧልዋ እንድትሰግድ አዛት ነበር። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁኝ አንዲት ሴት የአላህን መብት አታሟላም የባልዋን መብት እስከምታሟላ ድረስ።)"
ከሀዲሱ የምንረዳው፦ አንድ ሰው ከአላህ ውጭ ላለ ነገር መስገድ እንደሌለበት ነው። ይህ ደግሞ ተዉሂድን ይፃረናል። እዳሳለፍነው ይህ እሳት አላህ እንደላከው አይተናል ስለዚህ የእሳቱ ጌታ ብቻ ሊሰገድለት የተገባ ነው። በጣም ሚያሳዝነው የፍጡሮች ሁሉ ጌታ የሆነው አላህ የሱ የማይሰግዱ እናቶች ለዚህ እሳት ሲሰግዱ ያሳዝናል። አለህ ቀልበቸው በተዉሂድ ያርጥብላቸው።
ቤቱ ሲነድ ምንም ዓይነት እቃ አላወጡም። እኛ ከመጣን በኋላ እናጥፋው ስንላቸው የመብረቅ እሳት እኮነው አሉን። ጆፎሮ ላይ የተሰባሰቡ ወጣቶች ነበሩ። እኔ እኛ ወጣት ነን ተባብረን እናጥፋው አልኳቸው። ከነሱ መካከል አንድ ልጅ የመብረቅ እሳት በውሀ ለማጥፋት ትሞክራለህ ወይ!!? ኧረ ተወን አለኝ። ትንሽ ወሃ ለመድፋት ስንሞክር ሰዉ ሁሉ መጮህ ጀመረ። ሊያስጨርሱን ውሀ ይደፋሉ በህይወታችን ሰምተን የማናቀው ነገር እያረጉ ነው ብለው ያመጣነው ጀሪካን ወሰዱብን። አንድ አብሮን የሚቀራ ጓደኛችን አሁንም ተስፋ አልቆርጥም ብሎ ተደብቆ ውሃ ማምጣት ጀመረ። ያለው ሰው ብዙ ስለነበረ አሁንም ወዲያውኑ ላይ ነጥቀው ወሰዱበት።
በጣም የሚያሳዝንና የሚያስለቅሰው ነገር የዛ ቤት እናት አንድ ጥጃ ከነህይወቱ ለሱ ፊዳ እንዲሆን ካልጨመርኩኝ አለች። በዛ ጊዜ የሰፈር ልጆችም ተባብረውን ጊደሩ ወስደንባቸው ጓደኛችን ጋር ወስደን አሰርነው። እቺ ጥጃ ምን አጥፍታ ነው በዚህ እሳት ከነ ህይወትዋ ምትጣለዉ?!! ላኢላሀ ኢለላህ!
በዚህ መልኩ ከእነሱም እየታገልን እያለን ቻይና ጋር የሚጠብቁ ልዩ ኃይሎች አመጡብን አላህ ይምራቸው። እነዚህ ልዩ ኃይሎች ማን ነው በንብረቱ የፈለገ ነገር ለማድረግ የሚከለከለው ብለው ሲገቡ እኛ ሾልከን አመልጥናቸው። እኛ ከሄድን በኋላ ያ ውሀ ተደብቆ ሲያመጣልን የነበረው ጓደኛችን እዛው ነበር። ቤተሰብም ስለሆነ አስፈራርተውት ሰው ወደ ቤቱ ከሄደ በኃላ ቤተሰብም እቤት ከገቡ በኋላ አጠገቡ የነበረው ቆርቆሮ ቤት ክፈፉ ጫፍ እሳት ተያይዞበት ውሃ ደፋሁበት አለን።
ከዛ በኋላ በማግስቱ ትላንት እንዳልመጣን ሰው ሆነን ከጓደኛችን ጋር ወረድን። ለዚህ ጋደኛችን ጓደኞቼ ስራ እንጀመር እንጨት እኛ እንፍለጥ እያሉ ነው በላቸው አልነው። ከአዲስ አበባ የመጡም ሰዎችም ነበሩና ይህም ሲሰሙ በጣም ተገርመው እንዴት ነው ስራ ምንጀምረው!! (አዋእ) ጠንቋዩ መጥተው ሳይጨርስ አሉ። ከዛ እኔ ወደ መርከዝ ተመለስኩኝ። ወንድሞች ደውዪ ስጠይቃቸው ወደ (አዋእ) ጋር ሄደው አመጡትና (እንደነገርኳቹ ከመሄድ በፊት የሚሰራ ስራ ሁሉ ሰርተው ነው የሄዱት) እሱ ከመጣ በሀኃላ (አላህ ይግደለው) ስሙ ጕይታኩየ ይባላል። ጕይታ ማለት በጉራጌኛ ጌታ ማለት ነው። ከዛ መጥቶ እንዲህ አለ «በሆነ ቦታ እኔ ስልክ ጠፍቶኝ ከዛ ሲፈተሽ ታጣ። ከተወሰኑ ደቂቃ ቦሀላ ቤቴ ሄጄ ያን ስልክ የሰረቀኝ ሰውዪ የገባበት ቤቱ እዲቃጠል አድርጌ ቤቱ ተቃጠለ አለ» ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለሂ ራጂኡን። በዚህ ንግግሩ የፈልገበት ይሄም ቤት ያቃጠልኩት እኔ ነኝ ለማለት ፈልጎ ነው። ሰውየው ክርስቲያን እኮ ነው በጣም ሚያሳዝነው ሙስሊም ሰዎች እንዲህ ሲል ማመናቸው። እስልምና የበላይ አርጓቸው ለሱ መዋረደቸው ነው። ከዛ እነዛ የተቃጠሉ እቃዎች ባጠቃላይ ንገሩኝ የኔ ናቸው ብሎ የተቃጠለ እቃ ባጠቃላይ እቤት ውስጥ የነበሩ ፋስ፣ መቆፈሪያ በሙሉ ሳይቀር ተነግሮት ገምቶ ብሩ ስጡኝ ብሎ ተሰጠው።
የተወሰኑ የጎረቤት እንሰቶች ጭስ ወጥቶባቸው ትንሽ ደርቀው ነበር። የነሱም ብር ስጡኝ ብሎ የእንሰቱ ባለቤት የነሱም ብር ሰጠው። ብሩ ከተሰጠው በኋላ ስራ ጀምሩ አላቸው። እነሱም በደስታ ተጨረሰ ብለው ወደ ስራቸው ገቡ። የሚያደርጉት ከላይ የጠቀስኩት ማለት ነው።
እነዚህ ሰዎች እደምሳሌ ጠቀስኩላቹ እንጂ በየግዜው መብረቅ በተለያየ ነገር ላይ ይወርዳል። ያ የወረደበት ሰው እነዚህ ሰዎች የሰሩትን የሽርክ ስራ ነው የሚሰሩት። ስለዚህ ወንድሞቼ የኔ አባትና እናት ተዉሒድ ያውቃሉ። ይህን ነገር አይሰሩም ነበር ልትሉ ትችላላቹ። ነገር ግን እነሱ ይህ ስራ አልሰራም ቢሉ እንኳን የሰፈር ሰው አይተዋቸውም ማለትም እንዲህ ካላደረጋቹህ እንዲህ ትሆናላቹ በማለት ያስገድዷቸዋል። "ሰው ያሸንፋል" የሚባል አባባል አለ። ስለዚህ ቤተሰቦቻችንን በማስተማር ላይ እንጠናከር። እነሞር ላይ ብዙ አይነት የሚሰሩ ሽርኮች አሉ።
✍ ወንድም፦ ሰዒድ ሙሰፋ አህመድ
ክፍል ስድስት ይቀጥላል
https://t.me/Gusbajisunna