« የፍቅርን አቅም ማየት ከፈለግክ ኡመሩል ፋሩቅ የረሱሉላህ ህልፈት የተነገራቸው ጊዜ የሆኑትን ልብ በል፣ የሚወዱትን ዳግም ሊያዩት እንደማይችሉ ሲያውቁ ያለውን ሀዘን መቃኘት ከፈለግክ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ረሱሉላህን ሲሰናበት ያለውን አስተውል።
ንፁህ ፍቅር ትዝታው ከባድ እንደሆነ ለማየት ቢላል ኢብኑ ረባህ ወደ መዲና ተመልሶ መጥቶ አዛን ሲል ስለነበረው ክስተት መርምር። ልብ እጅግ የሚመኘውን ንፁህ ፍቅር ሲያገኝ ትንሽ ማየት ከፈለግክ « አላህ ሆይ ለኔና ለሙሀመድ ብቻ ምህረት አድርግ፣ ሌሎቹን ግን ቅጣቸው » ስላለው አዕራብይ ሁኔታ አስብ።
ፍቅር ልቦችን እንደሚያናግር ማወቅ ከፈለግክ ስለ ረሱሉላህ ሲወራ የአማኞችን ፊት ተመልከት። ጌታህ ከማንም አብልጦ እንደሚወድህ ለማረጋገጥ ከፈለግክ አሁንም ድረስ እዝነቱን ልብ በል። ለጌታህ ያለህን ፍቅር መግለፅ ከፈለግክ አሁንም ድረስ የተውበትን በር ክፍት እንዳደረግልህ አስተውል። »
t.me/abdu_rheman_aman