ከ ቀደምቶች ንግግር🔊 dan repost
• ከወድሁ ለማስታወስ ያክል…በረመዷን እና ከረመዷን ዉጪ የሚሠራ ወንጀል አንድ አይደለም፡፡ አላህ ያከበረው ነዉና ወሩ ክብር አለው፡፡ አላህ ያከበረዉን ማክበር ደግሞ አላህን ማክበር ነው፤ አላህ ደረጃ ለሠጠው መስጠት አላህን መፍራት ነው፡፡እንዲያም ሆኖ አናስተዉልም፡፡ ረመዷን እና ሌላው ወር የሚመሳሰልብን ብዙዎች ነን፡፡
ተራዊሕ ለመስገድ የወጣ ሁሉ መስጊድ አይገኝም፡፡ በየካፌው የሚኮሎኮሉትን ብዙ እናገኛለን፡፡ ቁርኣን የሚያነብ መስሎ ጥግ ይዞ የተቀመጠው ሁሉ እያነበበ አይደለም፡፡ ቻት ላይ የተጣደ በርካታ ነው፡፡ መፆም ሲባል ሀያ አራት ሰዓት መተኛት የሚመስለዉም አለ፡፡ ስንፍና ነው፡፡ ወጣትነቴ ስፆም ይብሳል እኮ የሚል ጎረምሳ ታገኛለህ፡፡ የሚገርም ነው፡፡ ግራ ይገባል፡፡ ከሶሻል ሚዲያ ርቄያለሁ ብሎ ረመዷን መግቢያ ላይ ያወጀ ሁሉ የራቀ አይደለም።ለመለወጥ ለማደግ እንታገል። ከራሳችን ጋር እንሁን። ወደራሣችን እንመለስ። ለአላህ ብለን እንጂ ሰው ስለፆመ አንፁም፡፡ ሰው ቁርኣን እየቀራ ነው ብለንም አናስመስል፡፡ ሰው ሁሉ ኢዕቲካፍ ገብቷል ብለን አንግባ፡፡ ረመዷንን ፆምና ዒባዳ እንደ ሸክም አንመልከት፡፡
• አላህ ረመዷን በ ሰላም ደርሰው ከረመዷንም ከሚጠቀሙት ባሮቹ ያድርገን!
= t.me/AbuSufiyan_Albenan