ጅብሪል ሱልጣን dan repost
ማሳሰቢያ :- ከፅሁፎቼ ተመልሻለሁ
ምናልባት የአረዳድ አለመግባባት ተፈጥሮ እንዳይሆን እየሰጋሁ አንድ ነገር ሊል ወደድኩ
ከአሁን በፊት ከአንድ በላይ ስለማግባት የተለያዩ ፅሁፎችን እንደፃፍኩ ይታወቃል ነገር ግን አንዳንድ ውድ ወንድሞቼ የኔን ፅሁፍ ከአንድ በላይ ማግባት አይቻልም ማግባት ዬለባችሁም እንዳልኩ አስመስለው ተረድተውኝ መሰል ምላሽ ሲፅፉ ከአሁን በፊትም አይቻለሁ ነገር ግን ውድ ወንድሞቼ እኔ በጭራሽ እንደዛ አላሰብኩም አላልኩምም ሊያስብም አይገባኝም ቆይ በምን አቅም እና ድፍረት ነው እሱን የሚለው ' ወላሂ እኔ በጭራሽ እንደዛ አላሰብኩም ላስብም አልችልም ' በምን ሞራል አላህ ሃላል ያደረገውን የፈቀደውን አድርጉ ያለውን ነቢዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሰርተው ያሳዩንን ተግባር እኔ እጋጫለሁ ይህን በፍፁም አላሰብኩበትም ።
ፅሁፌን በቀናነት (positively) ያነበበው ይህን ይረዳል
እኔ አሁንም የሚለው ( በምክር ደረጃ ነው ) ሁለተኛ ስናስብ ቢክራ መምረጥ 100% መብታችን ነው ግን አንዳንዴ ከደግነት አንፃርም አግብተው በመንሀጃቸው ምክንያት የተፈቱትን ባላቸው የሞተባቸውን ሰለምቴዎችን እንምረጥ ይህ የነቢዩም ፈለግ ነው የሚል ነው እና ደሞ ለእህቶች በማሰብ በየወሩ አንዷን አግብተን አስረግዘን ፈታሁሽ አንበልና ሌላ ለማግባት አንሩጥ ነው ምናልባት ይህንንም ተግባር ሸሪዓው ከደገፈው ከእሱም ተመልሻለሁ ከሸሪዓው መጋጨት አልፈልግም ( እኔ በማውቀው ግን ይደግፈው አይመስለኝም ) በእህቶች አንጫወት ብያንስ ሴቶች ጥፋት ይኖርባቸዋል ትንሽም ሲያጠፉ በቃ እንዲህ እንዲህ ነሽ ብለን ለፍቺ ከምንሮጥ እና ሌላ ከምንፈልግ እኛ ወንዶችን አላህ ከሴቶች በላይ አስተዋዮች አድርጎናልና ረጋ ብለን ለማሻሻል ለማስተካከል እንጣር ለፍቺ አንጣር ነው መልዕክቴ ምናልባት ለዚህም ሸሪዓዊ ድጋፍ ካለው አላውቅም እኔ ዛሬም ነጌም ሁሌም ከሸሪዓው ከመጋጨት የጠራሁኝ ነኝ ከሸሪዓው የተጋጨሁባቸው መልዕክቶች ካሉኝ ከእነሱ እኔ የጠራሁኝ ነኝ ።
ሳጠቃልል :- የኔ አቋም ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት በአንዴ ማግባት ይቻላል ከእነሱ ምናልባት ከአቅም በላይ የሆነ እስከ ፍቺ የሚያደርስ ችግር ቢፈጠር መፋታት ይቻላል ( ፍቺ አላህ የማይወደው ግን ሃላል ያደረገው ነው ) ከእነሱ ከተፋታ ቦሃላ ሌላ ማግባት ይችላል ። ለሁለተኛ ለሶስተኛ ለአራተኛ ብሎም ለአንደኛም ሲያገባ ድንግልናን መስፈርት ማድረግ ይችላል መብቱ ነው ።
وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا
በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
ከእነዚህ አቋም ውጪ የሚያንፀባርቅ መልዕክት አዘል ፅሁፍ እኔ እስከማውቀው አልፃፍኩም የፃፍኩትም ካለ የኢስላም ሊቃውንት የማይደግፉት ሸሪዓው የማይደግፈው ፅሁፍ የፃፍኩት ካለ 1 ) ከእሱ ፅሁፍ ተመልሻለሁ አላህ ይቅር ይበለኝ ይለኝም ዘንድ ዱዓዕ አድርጉልኝ (ሌሎችንም ወንጀሎቼን ) 2 ) ፅሁፉን ላኩልኝና በላካችሁልኝ ቅጽበት ላጥፋው
✍ ጅብሪል ሱልጣን
═════ ❁✿❁ ══════
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan