الدين هو النصيحة


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


يَٰلَيْتَنِى قَدَّمْتُ لِحَيَاتِى
«ዋ እኔ! ምነው ለሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ»
┈┅•٭📚🌹📚٭•┅┈

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ጅብሪል ሱልጣን dan repost
አስደሳች ዜና እና ታላቅ ብስራት
=======================

አዲስ መጽሓፍ በቅርብ ቀን

የአክፍሮት ሃይላት ዲኑን ባለማወቁ ምክንያት ሊያከፍሩት አቅደው ቆርጠው ለተነሱት ህዝብ ዲኑን በቋንቋው በማስተማር እንድረስለት ።

ፀሀፊ :- መካ ሀጂ ሹክሬ
ከሸይኽ አብድል ሀሚድ ተቅዲም ጋር

ሉክቴያ ( መልዕክቴ ) በሲልጢኛ ቋንቋ

ዲነክ በልቻሎትከ መሳ የኩፍሪ ወራባ ሊበላይ ሉጥ ባለ ለቄራዪ ኡመት ዲነካን ባፍቻ ባችሎት ለጂጅነኒ

ሉክቴያ በሲልጢኛ አፍ በቁርብ አያም

ከታቢሎ የሀጂ ሹክሬይ መካ

የለተሞይ ሸክ ተቅዲም አስቡያን

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan




ፈትዋ J 36
===================

ጥያቄ :-

1 ) ከሃይድ ጋር በተያያዘ ከመጣው

( እኔ ደሞ እንደሷ ሳልሆን ባሌ ሌላ ሃገር ለትምህርት ሄዶ ትምህርቱን እስኪጨርስ ድረስ መርፌ ወይም Implant ተጠቅሜ ነበር የኔውም ሃይድ እንደሷው ተዛባብኝ ይሃው ዛሬ ሃያ ሁለተኛ ቀኔ ነው ሃይዴ ግን አምስት ቀን ነበር ምን ይሻለኝ ? )

ምላሽ :-
ፈዲለቱ አሽ_ሸይኽ አብድል ሀሚድ አል_ለተሚይ ሀፊዘሁሏህ

═════ ❁✿❁ ══════

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ጅብሪል ሱልጣን dan repost
ማሳሰቢያ :- ከፅሁፎቼ ተመልሻለሁ

ምናልባት የአረዳድ አለመግባባት ተፈጥሮ እንዳይሆን እየሰጋሁ አንድ ነገር ሊል ወደድኩ

ከአሁን በፊት ከአንድ በላይ ስለማግባት የተለያዩ ፅሁፎችን እንደፃፍኩ ይታወቃል ነገር ግን አንዳንድ ውድ ወንድሞቼ የኔን ፅሁፍ ከአንድ በላይ ማግባት አይቻልም ማግባት ዬለባችሁም እንዳልኩ አስመስለው ተረድተውኝ መሰል ምላሽ ሲፅፉ ከአሁን በፊትም አይቻለሁ ነገር ግን ውድ ወንድሞቼ እኔ በጭራሽ እንደዛ አላሰብኩም አላልኩምም ሊያስብም አይገባኝም ቆይ በምን አቅም እና ድፍረት ነው እሱን የሚለው ' ወላሂ እኔ በጭራሽ እንደዛ አላሰብኩም ላስብም አልችልም ' በምን ሞራል አላህ ሃላል ያደረገውን የፈቀደውን አድርጉ ያለውን ነቢዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሰርተው ያሳዩንን ተግባር እኔ እጋጫለሁ ይህን በፍፁም አላሰብኩበትም ።

ፅሁፌን በቀናነት (positively) ያነበበው ይህን ይረዳል

እኔ አሁንም የሚለው ( በምክር ደረጃ ነው ) ሁለተኛ ስናስብ ቢክራ መምረጥ 100% መብታችን ነው ግን አንዳንዴ ከደግነት አንፃርም አግብተው በመንሀጃቸው ምክንያት የተፈቱትን ባላቸው የሞተባቸውን ሰለምቴዎችን እንምረጥ ይህ የነቢዩም ፈለግ ነው የሚል ነው እና ደሞ ለእህቶች በማሰብ በየወሩ አንዷን አግብተን አስረግዘን ፈታሁሽ አንበልና ሌላ ለማግባት አንሩጥ ነው ምናልባት ይህንንም ተግባር ሸሪዓው ከደገፈው ከእሱም ተመልሻለሁ ከሸሪዓው መጋጨት አልፈልግም ( እኔ በማውቀው ግን ይደግፈው አይመስለኝም ) በእህቶች አንጫወት ብያንስ ሴቶች ጥፋት ይኖርባቸዋል ትንሽም ሲያጠፉ በቃ እንዲህ እንዲህ ነሽ ብለን ለፍቺ ከምንሮጥ እና ሌላ ከምንፈልግ እኛ ወንዶችን አላህ ከሴቶች በላይ አስተዋዮች አድርጎናልና ረጋ ብለን ለማሻሻል ለማስተካከል እንጣር ለፍቺ አንጣር ነው መልዕክቴ ምናልባት ለዚህም ሸሪዓዊ ድጋፍ ካለው አላውቅም እኔ ዛሬም ነጌም ሁሌም ከሸሪዓው ከመጋጨት የጠራሁኝ ነኝ ከሸሪዓው የተጋጨሁባቸው መልዕክቶች ካሉኝ ከእነሱ እኔ የጠራሁኝ ነኝ ።

ሳጠቃልል :- የኔ አቋም ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት በአንዴ ማግባት ይቻላል ከእነሱ ምናልባት ከአቅም በላይ የሆነ እስከ ፍቺ የሚያደርስ ችግር ቢፈጠር መፋታት ይቻላል ( ፍቺ አላህ የማይወደው ግን ሃላል ያደረገው ነው ) ከእነሱ ከተፋታ ቦሃላ ሌላ ማግባት ይችላል ። ለሁለተኛ ለሶስተኛ ለአራተኛ ብሎም ለአንደኛም ሲያገባ ድንግልናን መስፈርት ማድረግ ይችላል መብቱ ነው ።


وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا
በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡

ከእነዚህ አቋም ውጪ የሚያንፀባርቅ መልዕክት አዘል ፅሁፍ እኔ እስከማውቀው አልፃፍኩም የፃፍኩትም ካለ የኢስላም ሊቃውንት የማይደግፉት ሸሪዓው የማይደግፈው ፅሁፍ የፃፍኩት ካለ 1 ) ከእሱ ፅሁፍ ተመልሻለሁ አላህ ይቅር ይበለኝ ይለኝም ዘንድ ዱዓዕ አድርጉልኝ (ሌሎችንም ወንጀሎቼን ) 2 ) ፅሁፉን ላኩልኝና በላካችሁልኝ ቅጽበት ላጥፋው

✍ ጅብሪል ሱልጣን

═════ ❁✿❁ ══════

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ጅብሪል ሱልጣን dan repost
🔻ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

♦️ የዘይድ ብን ሣቢት የቁርኣን ሂፍዝና መስረታዊ የሸሪዓ እውቀቶች ማዕከል በ online ተማሪዎችን በተለያዩ የእውቀት ዘርፍ ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ጀምሯል

የሚሰጡት ትምህርቶች :—

   ① ቁርኣን በሒፍዝ በሶስት(ሪዋያ) የአቀራር ዘይቤ ማለትም  ✔️ ሀፍስ ዐን ዓሲም
                    ✔️ ሱሲ ዐን አቢ ዐምር
                     ✔️ ኸለፍ ዐን ሀምዛ
② ቁርኣን በነዘር( እያዩ አስተካክሎ) መቅራት
③ የመንሀጅ የዐቂዳ ክታብ
④ የተጅዊድ ክታቦች በየደረጃውና በየአይነቱ
⑤ የአረብኛ አፃፃፍ
⑥ የነህው
⑦ ሰርፍ
⑧ ቃዒደቱ ኑራኒያ
9. የፊቂህ ኪታቦች


⏰ደርሱ የሚሰጠው በሳምንት አምስት ቀን ነው

📌በተጨማሪም በትምህርታቸው ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች ሰርተፍኬትየሚሰጥ ይሆናል

📢በመጨረሺያም: – ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ከዚህ በታች ባሉት ዩዘሮች ና ስልኮችን በመጠቀም  ማናገር ና መመዝገብ ትችላለችሁ

🔴ለወንዶች ይህንን  አድራሻ በመጫን ይመዝገቡ 👇👇👇
@Abushuraih12

🟢ለሴቶች ይህንን አድራሻ በመጫን ይመዝገቡ 👇👇👇

@Umu_Abdurehman

አላህ ጠቃሚ እውቀትን ይወፍቀን ለሁላችንም

            አሚን‼
https://t.me/abushuayb1
https://t.me/abushuayb1
https://t.me/abushuayb1


የጁመዓ ኹጥባ
====================

ርዕስ :- በግዜ እና በአጋጣሚዎች የተደነገጉ ኢባዳዎች

✔️ ወሳኝ ርዕሶች ተዳስሰውበታል

🎙 ኻጢብ :- ፈዲለቱ አሽ_ሸይኽ አብድል ሀሚድ አል_ለተሚይ ሀፊዘሁሏህ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ፈትዋ J 31
===================

ጥያቄ :- እነሳዳት ከማልን የበደዓችሁበት ምክንያት እንደ ድሮ መሳደብ ስለተዉ ነው ?

ምላሽ :- ፈዲለቱ አሽ_ሸይኽ አብድል ሀሚድ አል_ለተሚይ ሀፊዘሁሏህ ከእራሱ ከሳዳት ድምፅ ጋር

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


አብራር አወል ( Abu ubeyda) dan repost
በአላህ ፍቃድ ከሰአት የሚቀሩ ኪታቦች
⏰ 8:00 ሰአት ላይ ቀጥታ ስርጭት አርበኡነ ለተሚያ ይጀምራል ኪታብን አዘጋጁና በጊዜ ገባ ገባ በሉ ከሱ በመቀጠል ደግሞ አዱረቱል በሂያ ይቀጥላል


https://t.me/AbraribnAwal
@bilalibnurebahmedresa
@bilalibnurebahmedresa


ፈትዋ J 30
============

ጥያቄ :- አላህ ከአርሽ በላይ ተቀምጧል ማለት እንዴት ይታያል ?

ምላሽ :- ፈዲለቱ አሽ_ሸይኽ አብድል ሀሚድ አል_ለተሚይ ሀፊዘሁሏህ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ውድ ቤተሰቦቻችን እንደምን ወላችሁልን

መልካም ጤናን ተመኘንልዎ !!

ከአጠቃላይ ቀዶ ጥገና ጋር በተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት በግሩፓችን መጠየቅ ይችላሉ በሙያው ብቃት እና ስፔሺያሊቲ ባላቸው ብቁ ዶክተሮች ይመለስላቹሃል ።

ሀላባ ኬር መካከለኛ ክሊኒክ !
https://t.me/halabacare
https://t.me/halabacare


አዲስ
==============°====

ርዕስ :- ተቅዋ
ክፍል :- አንድ


✔️ ብዙዎቻችን የዘነጋነው ርዕስ ተቅዋ የአላህ ፍራቻ

🎙 ፈዲለቱ አሽ_ሸይኽ አብድል ሀሚድ አል_ለተሚይ (ሀፊዘሁሏህ)

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan




ጅብሪል ሱልጣን dan repost
ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ...
-------------.-------------------------

ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ብቻ ሳይሆን መቼም አይፈቀድም የማይፈቀድን ነገር ማድረግ ደሞ ጉደት እንጂ ጥቅምን አምጥቶ አያውቅም ። ስለዚህ ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍም ይሁን ተቃውሞዋዊ ሰልፍም ዬለም በተለይ እንደ ሃገራችን ደግሞ ከቀኝም ከግራም ከፊትና ኋላም የሙስሊሙ ቁጥር መብዛት የሚያስጨንቃቸውና የት አግኝቼ በአንድ ላይ ልደፍጥጣቸው የሚል አስተዳደር ቋምጦ በጠበቀበት አጋጣሚ የሙስሊም ስሞች በዝቷል እያለ የሚያወራ አስተዳደር ባለበት ደግሞ ነገሩን ይበልጥ የከፋ ያደርገዋል ። አይደለም ካፊር በሚያስተዳድርበት ሃገር ቀርቶ ሙስሊም ሃገራት ላይ ራሱ ሙስሊም በሚያስተዳድርበት ሃገር ሰላማዊ ሰልፍ ተብሎ ተወጥቶ በሰላም ድምፃቸውን አሰምተው የገቡበትን አጋጣሚ ብንቆጥራቸው ከጣታችን ቁጥር ያንሳል ።

ስለይህ በተለይ እንደ ሃገራችን ኢትዮጵያ ባለው ተጨባጭ ሰላማዊ ሰልፍ ውጤቱ ሰላም ሳይሆን አደጋ ነው ።

እኔ ደሞ አንድ የተረዳሁት ነገር አለ ወደኋልዮሽ ታሪክ ዘወር ብለን ስናይ ምናልባት ሰነዱን በግልጽ ባላውቀውም የንጉሱን አስተዳደር በምናስታውስበት ግዜ በርግጥ በግዜው ከባድ ጭቆና ከመኖሩም ጋር ንጉሶች በሃገሪቱ ያሉ ትላልቅ አሊሞችን በጣም ይፈሯቸው ነበር መፍራትም ብቻ ሳይሆን በጉዳዮቻቸው እየመጡ ያማክሯቸው ብሎም ዱዓዕ አድርጉልን ይሏቸው እንደነበር ይወራል ። ምክንያቱም የዛኔ የነበሩ ትውልዶች የዱዓዕ power ሃይል ነበራቸው ። የአላህና የነቢዩ ትክክለኛ ፍቅር ነበራቸው ሁለቱን ከህይወታቸው ያስበልጧቸው ነበር ። አይደለም ሁለቱ ተነክተውባቸው በመልካም ስማቸው ሲታወሳቸው በራሱ ቀልባቸው ገላቸውን በድን አድርጋ ወጥታ ትጠፋለች ። በርግጥ ዲን የአሁኑን ያህል አልተስፋፋም ነበር ስላልተስፋፋም ብዙ ኹራፋቶች ይኖሩ ነበር ነገር ግን የተስፋፋችው ዲን በጣም ጥቂት ብትሆንም የሚሰሩባት ከልባቸው ነበር። ስለሆነም አንዴ እጃቸውን አንስተው ያ አላህ ካሉ የሚመጣውን ከባድ Consequence መሪዎቹ ጠንቅቀው ያውቁታልና ይፈሩ ነበር ።

ነገር ግን የአሁኑ ትውልድ በዱዓም ከአላህ ጋር ባለውም ትስስር (chain) ሲደክም ጭንቀቱን ሃዘኑን በዱዓዕ ገመድ ወደ አላህ ከማሰማት ይልቅ እራሱን ለአደጋ እየጣለ ሰላማዊ ሰልፍ ብሎ እየወጣ ለጠላት መሪው ካላሰማሁ እዬዬ ይላል ታድያ ይህ አይነት ትውልድ እንዴት ሆኖ ሊፈራና ሃያል ሊሆን ??

አላህ ይሁነን ብቻ !!

©ጅብሪል ሱልጣን
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


وليسَ المقصودُ بالحكمةِ تمييع الأمور وتضييعها؛ والمجاملات وما شاكل ذلك الَّتي تُؤدّي إلى ضَياع الدّعوة، وتدخل في المداهنة! "

| العلَّامة ربيع بن هاديّ المدخليّ –حَفِظَهُ اللهُ تَعَالَى-. ["وقفات منهجيّة" / عام: (1416هـ)]


ወቅታዊ ፈታዋ :-

ተ.ቁ = ሸ002

ጥያቄ :-
#አስሉ ሱኒይ የነበረን ሰው ሁጃ መረጃ ሳይቆምበት ሙብተዲዕ ማለት ይቻላልን ?

  አስሉ ሱኒይ የነበረን ሰው ሁጃ ሳይቆምበት መበደዕ አይቻልም የሚሉ አሉ አብራሩልን ?

ምላሽ :-
🎙 #ፈዲለቱ ሸይኽ አብድል ሀሚድ አል_ለተሚይ ሀፊዘሁሏህ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ጅብሪል ሱልጣን dan repost
❓ #ስሙማ
ፆመኛ ነበርኩኝ ከዛ መስጂድ ገብቼ ተኛሁ ሲነቃ ለካ ኢህቲላም አይቼ ተጀንቤያለሁ ይህ ሙህተሊምነቴ ፆሜን ይጎዳዋልን ? ይህን እያወኩም ሻወር አልወሰድኩም ሻወር ሳልወስድም እዛው ሳልታጠብ ሰላቴን ሰገድኩ ይህስ ፆሜን ይጎዳዋል ? ሌላ ቀን ደግሞ የሆነ ድንጋይ ጭንቅላቴን ብሎ ፈነከተኝና ደም ፈሰሰኝ ይህስ ፆሜን ያበላሸው ይሆን ?
=========================

ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ወሳኝ ጥያቄዎች መሃል እንዲህ የሚል ይገኝበታል

📮#ጥያቄ:-

ፆመኛ ነበርኩኝ ከዛ መስጂድ ውስጥ ተኛሁ ሲነቃ ለካ ኢህቲላም አይቼ ተጀንቤ አየሁ ይህ ሙህተሊምነቴ ፆሜን ይጎዳዋልን ? ይህን እያወኩም ሻወር አልወሰድኩም ሻወር ሳልወስድም እዛው ሳልታጠብ ሰላቴን ሰገድኩ ይህ ፆሜን ይጎዳዋል ? ሌላ ቀን ደግሞ የሆነ ድንጋይ ጭንቅላቴን ፈነከተኝና ደም ፈሰሰኝ ይህስ ፆሜን ያበላሸው ይሆን ?

👜 #ምላሽ :-

#ኢህትላም ፆምን አያበላሽም ምክንያቱም በፍላጎትህ ላድርገው ብለህ የሚሆን ነገር አይደለም ። ነገር ግን መኒይ ከወጣው መታጠብ አለበት ። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ ስለዚህ ጉዳይ በተጠየቁ ግዜ ሲመልሱ ሙህተሊም ፈሳሽን ማለትም መኒይን ካየ መታጠብ አለበት ብለው መልሰዋል ። አንተ ግን ያለ ትጥበት መስገድህ ይህ ያንተ ስህተት ነው ከባድ ውግዘትም ነው ። ከተውበት ወደ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ከመመለስ ምህረትን ከመጠየቅ ጋር ከትጥበት ቦሃላ ሰላቱን መልሰህ መስገድ አለብህ ።

ደም እስኪፈስህ ጭንቅላትህን የፈነከተህ ድንጋይ ደሞ ፆምህን አያበላሸውም ያለፍላጎትህ ያስታወከህ ትውከት ፆምህን አያበላሸውም ። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ :-
(( من ذرعه القيء فلا قضاء عليه، ومن استقاء فعليه القضاء )) رواه أحمد وأهل السنن الأربع

ትውከት ሀይሎት ያስታወከው ቀዳዕ ዬለበትም ። ሆን ብሎ ትውከቱን ፈልጎት ያስታወከ ግን ቀዳዕ አለበት ።

💼 #ምንጭ:-
ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች የወሰድኩት

✍ ጅብሪል ሱልጣን

ከረመዷን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፈትዋዎች ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ጅብሪል ሱልጣን dan repost
ቆይ ግን በሱጁድ አት_ቲላዋ በሱጁድ አስ_ሰህው እና በሱጁድ አሽ_ሹክር ምንድነው የሚባለው ?
==========================

በመርሳት ሱጁድ በሹክር በምስጋና ሱጁድ እና በቲላዋ ሱጁድ ሲወረድ ምንድነው የሚባለው ?

ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች መሃል እንዲህ የሚል ይገኝበታል

📮 #ጥያቄ :-
ሰጋጅ የሆነ ሰው በመርሳት ሱጁድ ምንድነው የሚለው ?


📖 #ምላሽ:-

በሱጁደ ቲላዋም ይሁን በመርሳት በሱጁደ ሰህው የሚለው በሰላት ሱጁድ ውስጥ ሲል የሚለውን እራሱኑ ነው የሚለው እንዲህ ይላል :-

((سبحان ربي الأعلى سبحان ربي الأعلى))

በገራለት መልኩ አላህን ይለምናል ።

👉 እንዲህም ይበል :-
اللهم لك سجدت وبك آمنت ولك أسلمت ، سجد وجهي للذي خلقه وصوره وشق سمعه وبصره بحوله وقوته ، تبارك الله أحسن الخالقين.

ይህንን ዚክር በሱጁደ ሰህውም በሱጁደ ቲላዋም ይሁን በሱጁደ ሹክር ይበለው ።

💼 #ምንጭ :-
ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች የወሰድኩት


ከረመዷን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፈትዋዎች ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ጅብሪል ሱልጣን dan repost
ቁርዓን ድምፄን ሳላወጣ በእይታ ብቻ እያስተነተንኩ ቢቀራ አጅር አገኝበት ይሁን?
==========================

ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች መሃል እንዲህ የሚል ይገኝበታል

📮 #ጥያቄ :-
ክቡር ሸይኽ ሆይ አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ

#ከፊል ሰዎች ቁርዓንን ሙስሀፉን ይይዙና ከንፈራቸውን ሳያንቀሳቅሱ ያነባሉ ይህ ሁኔታ ቁርዓን መቅራት የሚላው ስያሜ ይሰጠዋልን ? ወይስ ቁርዓን የመቅራቱን አጅር ያገኝ ዘንድ የግድ ቁርዓን ሲቀራ ማውራት ማሰማት አለበት ? ሰውየው ቁርዓኑን በማየቱ ብቻ አጅር ያገኛል ? ይመልሱልን ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን

👜 #ምላሽ :-
ወአለይኩም ሰላም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ

#ሳያስተነትኑ እና ትርጉሙን ሳይረዱ ቁርዓንን በእይታ ብቻ ከመቅራት ምንም ከልካይ ዬለም ነገር ግን ይህ ሰው ቃሪዕ ቁርዓን የሚቀራ አይባልም ቁርዓን በመቅራት የሚገኘውም ምንዳ አጅር አይገኝለትም ምንዳውን የገኝ ዘንድ በዙሪያው ያሉ ሰዎች ባይሰሙት እንኳን የግድ ቁርዓንን ማውራት አለበት ። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ :

(اقرءوا القرآن فإنه يأتي يوم القيامة شفيعا لأصحابه).  رواه مسلم.

ቁርዓንን ቅሩ እርሱ (ቁርዓን) እኮ የቂያማ ቀን ለባለቤቱ (ለሚቀራው ሰው) አማላጅ ሆኖለት ይመጣል ።

የነቢዬ ﷺ ፍላጎት "ለባለቤቱ" ሲሉ የሚሰሩበትን ነው በሌላ ሃዲስም እንዳለው :-

(من قرأ حرفًا من القرآن فله به حسنة ، والحسنة بعشر أمثالها) خرجه الترمذي ، والدارمي بإسناد صحيح

ከቁርዓን አንዲትን ፊደል የቀራ በሷ በቀራት አንድ ሀሰና መልካም ምንዳ አለው ሀሰናዎች መልካም ምንዳዎች ደሞ በአስር ነው የሚባዙት ።

የእውቀት ባለቤቶች እንዳሉት ደሞ አንድ ሰው ሲናገር ድምፅ ሲያሰማ እንጂ ካልሆነ አንባቢ ቃሪዕ አይባልም ።

💼 #ምንጭ :-
ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች የወሰድኩት

✍ጅብሪል ሱልጣን

ከረመዷን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፈትዋዎች ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ጅብሪል ሱልጣን dan repost
መሸት ሲል የሆነ ድምፅ ሰምቼ አዛን ያለ መስሎኝ ቢበላና ከዛም ያ ድምፅ አዛን ባይሆንስ ?
==========================

ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች መሃል እንዲህ የሚል ይገኝበታል

📮 #ጥያቄ :-
አንድ ሰው በረመዳን አዛን ያለ መስሎት ጠጣ ነገር ግን (ሲያጣራ) አዛን አላለም ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ምንድነው ማድረግ ያለበት ?

🧳 #ምላሽ:-

ፀሃይ ከመግባቷ በፊት መጠጣቱን ያወቀ ፆሙን ይመልሳል ። ነገር ግን የተለያዩ ምልክቶችን አይቶ ፀሃይ የገባች መስሎት የጠጣ ምንም ዬለበትም ። ነገር ግን ፀሃይ የገባች መስሎት ጠጥቶ ነበር ከዛም ፀሃይ ወገግ አለችና ወጣች ይህ ሰው ትክክለኛው አብዝሃኛዎቹ የዕውቀት ባለቤቶች ዘንድ የዚህን ቀን ፆም ቀዷዕ ያወጣል የዚህን ቀን ፆም ይከፍላል ። የተሻለውም ይህ ነው ።

👉 ከፊል ዑለማዎች መክፈል አለበት አይሉም ምክንያቱም ይህ ሰው ሆን ብሎ ስላልሆነ ኡዝር ይሰጠዋል ። ነገር ግን ወደ ሀቅ የቀረበውና ግልፁም ይህ ሰው ይከፍላል ። ልክ እንደዚሁ ፈጅር ጎህ ከወጣ ቦሃላ (ከነጋ ቦሃላ) ገና አልነጋም ለሊት ነው ብሎ አስቦ ቢበላ እና ሲያይ ነግቷል በቀን እንደበላም ታወቀው ይህም ይህን ቀን ፆም ይከፍላል ። ይህ አመዛኙ ነው ።

💼 #ምንጭ :-
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች የወሰድኩት

✍ ጅብሪል ሱልጣን

❓ከረመዷን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፈትዋዎች ለማግኘት ወደ ግሩፓችን ይግቡ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan


ጅብሪል ሱልጣን dan repost
ፆመኛ ሆኜ ሳለሁ ጥም ሲያስቸግረኝ ጥሙን ሊቀንስልኝ ብዬ ሻወር ቢወስድስ ?
=========================

ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች መሃል እንዲህ የሚል ይገኝበታል

📮 በረመዷን ቀን ላይ ከአንድ ግዜ በላይ ሻወር መግባት እንዴት ይታያል?

📠 ምላሽ :-

#ይቻላል ምንም ችግር ዬለውም ነቢዩ ﷺ ፆመኛ ሆነው ሳለ ለሙቀት እና ለጥም ብለው በጭንቅላታቸው ላይ ውሃ ያፈሱ ነበር ።

💼 #ምንጭ :- ኢብኑ ኡሰይሚን ከተጠየቋቸው ፈትዋዎች የወሰድኩት

✍ ጅብሪል ሱልጣን

ረመዷን ነክ ፈትዋዎችን ለማግኘት ወደ ቻናሉ ይግቡ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

656

obunachilar
Kanal statistikasi