የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱ መጀመሩን ተከትሎ ለዜጎቹ ባስተላለፈው መልዕክት “የሚወጡ መመሪያዎችን በንቃት እንዲከታተሉ” አሳስቧል።
የኢራን የሚሳዔል ጥቃት መጀመሩን ተከትሎ የእስራኤል ጦር የአገር ውስጥ ዕዝ በአንዳንድ አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች ወደ መከላከያ ስፍራዎች እንዲገቡ የሚያዝ “ነፍስ አድን” ያለውን መመሪያ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት አስተላልፏል።
የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ደግሞ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ ከጥቃት የመሸሸጊያ ስፍራዎች በመግባት ተጨማሪ መመሪያዎችን እንዲጠባበቁ መክረዋል።
ቃል አቀባዩ ጨምረውም የእስራኤል የአየር ጥቃት መከላከያ ሥርዓት “ሙሉ ለሙሉ በሥራ ላይ ሆኖ የሚተኮሱ ሚሳዔሎችን በመለየት እያከሸፈ” መሆኑን ተናግረዋል።
@Addis_Mereja