አዋሽ ፈንታሌ በመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን መፍረሳቸው ተሠምቷል
በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡
በመሬት መንቀጥቀጡ መሬት መሰንጠቁንም ዩኒቨርቲው ዛሬ ሰኞ ማለዳ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።
በፈንታሌ ተራራ ላይ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከሁለት ሳምንታት በላይ በተለያየ አጋጣሚ መከሰቱን ባለሞያዎች ገልጸዋል።
ትናንት መስከረም 26/2017 ምሽት 2፡10 ገደማ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት ነበር።
"የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል" ያለው ዩኒቨርሲቲው፤ አደጋው በተከሰተበት ሳቡሬ ቀበሌ ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሥራቱን ገልጿል።
የአካባቢው ነዋሪዎች የትናንቱ መንቀጥቀጥ ተወሰኑ ቤቶችን እንዳፈረሰ፣ መሬትን እንደሰነጠቀ እና በተለይ እንስሳት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ እንደገቡ ገልጸዋል::
የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች ነዋሪዎች ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። ትናንት እሑድ ምሽት የተከሰተውና በአዲስ አበባ በነዋሪዎች ላይ መደናገጥ የፈጠረው የመሬት መንቀጥጠጥ ለ18 ሴኮንድ የቆየ እንደነበረ ባለሞያዎች መናገራቸውን አሐዱ ዘግቧል።
@Addis_Mereja