መንጃ ፍቃድ❗️
ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ እንደሚታደሱ ተገለፀ!
ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ እንደሚታደሱ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣኑ ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን ገልጿል።
በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ አስታውቋል፡፡
አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት ሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆንም ተመላክቷል።
@Addis_Mereja