የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ #አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ ግዙፍ አውሮፕለን በተያዘው ጥቅምት ወር እንደሚረከብ ገለጸ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውና ''Ethiopia land of origins'' በሚል መጠሪያ የተሰየመውን ኤ350-1000 የመንገደኞች አውሮፕላን በተያዘው ጥቅምት ወር ከኤርባስ ኩባንያ እንደሚረከብ ገለጸ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፤ 400 መቀመጫዎች ያሉት ኤ350- 1000 አውሮፕላኑ በአይነቱ ልዩና ለደንበኞች የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።
አቶ መስፍን፤ አየር መንገዱ በአፍሪካ የአቪዬሽን መስክ ያለውን የቀዳሚነት ድርሻውን ለማስቀጠል በየጊዜው አዳዲስ አውሮፕላኖችን በማስመጣት እንዲሁም ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን በማስፋት ላይ ይገኛል ብለዋል።
አየር መንገዱ ኤ350-900 አውሮፕላኖችን መጠቀም ከጀመረ ሰባት ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑን ጠቅሰው አሁን ላይ ሃያ የኤ350- 900 አውሮፕላኖች በስራ ላይ መሆናቸውንም አንስተል።አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል ተብሏል።
@Addis_Mereja