እስራኤል በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች!
እስራኤል ከእኩለ ለሊት ጀምሮ በኢራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።ኢራንም በበኩሏ ንጋት ላይ እንዳስታወቀችው በዋና ከተማዋ ቴህራን፣ ኹዜስታን እና ኢላም በተባሉ ግዛቶቿ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ሰፈሮች የእስራኤል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው አስታውቃለች።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን የፈጸመው ኢራን እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ አጋሮቿ የሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ለፈጸሙት “ለወራት የዘለቀ ጥቃት" ምላሽ መሆኑን አስታውቋል።ይህ የእስራኤል ጥቃት የተፈጸመው ቴህራን ውስጥ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር የሐማስ ፖለቲካ መሪ በመገደላቸው ኢራን ከ200 በላይ ባሌስቲክ ሚሳዔሎችን መስከረም 21/2017 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ከተኮሰች በኋላ ነው።
የእስራኤል አየር ኃይል ሌሊቱን የፈጸመው ጥቃት ኢራን በእስራኤል ላይ የተኮሰቻቸውን ሚሳኤሎች የሚያመርቱ ተቋማትን፣ የአየር ጥቃት መከላከያ እና የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ሥርዓቶችን ዒላማ መደረጋቸውን ተገልጿል።ኢራን በወታደራዊ ይዞታዎቿ ላይ ጥቃት እንደተፈጸመባት አረጋግጣ፤ ነገር ግን “ጥቃቱ ውስን ጉዳት” ቢያደርስም በተሳካ ሁኔታ ማክሸፏን አስታውቃለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
@Addis_Mereja