ስድስት መራጮች ባሏት ከተማ ትራምፕ እና ሃሪስ እኩል ድምፅ አገኙ!
ዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ እና ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳቸውን አጠናቀዋል።የምርጫ ኮሮጆ ለድምፅ ሰጭዎች ክፍት ያደረገችው የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ከተማ ኒው ሀምፕሸር ግዛት የምትገኘው ዲክስቪል ኖች ናት።
በከተማዋ የምርጫ ጣቢያዎች የተከፈቱት በአካካቢው ሰዓት አቆጣጠር ሰኞ እኩለ ለሊት ነው። ከተማዋ ሁሌም የምርጫ ጣቢያዎቿን የምትከፍተው እኩለ ለሊት ነው። የምርጫ ጣቢያው ሁሉም መራጮች ድምፃቸውን እስኪሰጡ ክፍት ሆኖ ቆይቷል።ባለፈው ጥር በከተማዋ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሲካሄድ ድምፅ ለመስጠት የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር 6 ነበር።
የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ኒው ሀምፕሸር ግዛት የአሜሪካ ምርጫ ምን ሊመስል እንደሚችል ፍንጭ የምትሰጥ ግዛት ናት ይሏታል።ስድስቱም የአካባቢው ነዋሪዎች ድምፅ ከሰጡ በኋላ ቆጠራ የተደረገ ሲሆን ሃሪስ 3 ትራምፕ 3 ድምፅ አግኝተዋል።
Via BBC
@Addis_Mereja