በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ዛሬ ሌሊት 9:52 ሰዓት አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍ ያለ እንደነበር ጉዳዩን የሚከታተሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ካወጧቸው መረጃዎች መረዳት ተችሏል።
የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤትም ሆነ ቮልካኖ ዲስከቨሪ ያወጧቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት፥ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ ሆኗል።
ትላንት ምሽት 5.5 ሬክተር ስኬል መመዝገቡን ተከትሎ፥ ቮልካኖ ዲስከቨሪ ባወጣው መረጃ፥ ይህን ያህል ሬክተር ስኬል የተመዘገበበት የመሬት መንቀጥቀጥ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ አልተከሰተም ማለቱን መዘገባችን አይዘነጋም።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተደጋጋሚ እየተከሰተ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ፥ በተለይም የክስተቱ መነሻዎች (ኢፒሴንተር) አካባቢ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ስጋትን ደቅነዋል።
@Addis_Mereja