#መጻጒዕ
ሰው የለኝም ያለ በሰው የተረሳ
የዳነው መጻጒዕ ያዳነውን እረሳ
በአምስቱ እርከኖች በአዕማደ ሚስጥራት
ቤተ ሳይዳ ላለች ከመቅደስ ላኖርካት
በበደል ለምናዝን ምሕረትን ፍለጋ
በንሰሐ ማረፍ ካራተ ዝንጋኤ ከኃጢአት አልጋ
አዝ.....................
በጠበሉ ደጃፍ ለጸኑት የሚላክ
ለቀድሶተ ማይ የሚወርደው መላአክ
በመንገድ ጠብቆ ሞትን የሚያሳልፍ
ዛሬም ይድረስልን ቀድመው ከገቡት ጋር ነፍሳችን እንድታርፍ
አዝ.....................
አልጋው ተሸክሞት ደክሞ ለሚጨነቅ
አልጋን አሸክመህ ሕመም የምታርቅ
ደዌያችንን ነስተህ ቆስለህ የምትፈውስ
የመጻጒዕ ረዳት የነፍሳት መጠጊያ መድኃኒት ክርስቶስ
አዝ.....................
የባሰ እንዳያየው ቃሉን ያልጠበቀ
እጁን ሰዶ ጸፍቶ ከደዌው ታረቀ
ሰንበት የሻረ ከሚሉት እንዳንውል
ለትንሣኤው ደስታ የሰንበትን ጌታ አርብ እንከተል
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
💚
@Addis_mezmure 💚
💛
@Addis_mezmure 💛
❤️
@Addis_mezmure ❤️