አዲስ የተዋሕዶ መዝሙር


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
#አዲስ_የተዋሕዶ_መዝሙር
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ያሬዳዊ መዝሙሮችን እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
እንዲሁም አዳዲስ የሚወጡ የኦርቶዶክስ መዝሙሮችን በትንሽ ሜጋባይት በዚህ ቻናል ያገኛሉ
#ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


🔴 አዲስ የልደት ዝማሬ "ተወለደ " በዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሣሙኤል
   💚 @Addis_Mezmure 💚
💛 @Addis_Mezmure 💛
❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችው

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊአ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደርያ /2/
              #አዝ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
                #አዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ላለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
                 #አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉስ መቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተልሄም ታዉራ
ዝማሬ ሲወጣ ከርስቱ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
                  #አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰዉ
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለዉ
ገረማት ጥበቡ ታናሹአን ሙሽራ
ተዋህዳልና ቃል ከ ስጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#በቤተልሄም

በቤተልሄም ድንግል ወለደች
አማኑዔልን ታቅፋ ታየች
እረኞች ተቀኙ መላዕክት ዘመሩ
ስብሀት ለእግዚአብሔር በሠማይ በምድሩ

የያዕቆብ ኮከብ ከሩቁ ያየነው
በኤፍራታ ዋሻ በዱር አገኘነው
ድንቅ መካንሀያል ወንድ ልጅ ተሠጠን
በከብቶቹ ግርግም ተወልዷል ሊያነፃን
       ድንግል ያጠባችው
       ማርያም ያዘለችው
       ሁሉ በእርሱ የሆነ እግዚአብሔር ነው

#አዝ___

ያረምና ሠባ የቴርሠሥ ነገስታት
ከሩቅ ምስራቅ መጡ ወድቀው ሊሰግዱለት
አንቺ ቤተልሄም የይሁዳ ምድር
እልልታሽ ተሰማ የዳዊት ሀገር
     ድንግል ያጠባችው••••••

#አዝ____

ማርያምን ለመውሰድ ዮሴፍ ሆይ አትፍራ
ከመንፈስ ቅዱስ ነው ይሄ ድንቅ ስራ
ያለዘራ በዕሲ ጌታን የወለደች
የያቄም ልጅ ፅዮን እመብርሀን ነች
     ድንግል ያጠባችው•••••••

#አዝ___

በስጋና በደም ስለተካፈለ
ፍፁም አምላክና ፍፁም ሰው ተባለ
ወልደ-ማርያም ነው ወልደ-እግዚአብሔር
ለአለም የሠጠህ ሠላምና ፍቅር
    ድንግል ያጠባችው••••••••

   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#እሰይ_ተወለደ

እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት/3/
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት/3/
         አዝ-----
ትንቢት ተናገሩ ነብያት በሙሉ/3/
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ/3/
         አዝ-----
ሰብዓ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ/3/
የእስራኤል ንጉስ ተወልዷል እያሉ/3/
         አዝ-----
ሰብዓ ሰገል መጡ ይዘው እጅ መንሻ/3/
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ለማርያም እጅ መንሻ/3/
         አዝ-----
በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ/3/
ብስራተ ልደቱን ለሁሉም ሊያስረዳ/3/
          አዝ-----
ሕጻናት እንሂድ ልደቱ ቤት/3/
ውሃ ሆኗልና ማርና ወተት/3/

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ተወልደ_ናሁ

ተወልደ ናሁ እም ድንግል(2)

ሲነገር ነበረ በነብያት አፍ                                
በአንዱ በእግዚያአብሔር ባንዱ በመንፈስ
አንድ ቀን እንዲሆን ፀሀይ እንዲወጣ
የናፈቅነው ንጉሥ ስጋ ለብሶ መጣ
       አዝ-----
አብርሃም ያንን ቀን ለማየት ናፈቀ
ዳዊት በኤፍራታ ልደቱን አወቀ
ኢሳያስ ከድንግል ሲወልድ አየና
ትንቢት ተናገረ ምልክት አለና
       አዝ-----
ኮከብ ከያእቆብ ይወጣል ሲባል
ሰማይ ሆነችለት እናቱ ድንግል
በህዝቡ መካከል ሆኖ የሚያበራ
በእርሱ ፈራረሰ የጨለማው ሥራ
       አዝ-----
ከእረኞች ጋራ ቤተልሔም ግቡ
ከነገስታቱ ጋር አምኃን አቅርቡ
እንስገድ ለህጻኑ ይገባዋልና
አለቅነት ስልጣን በጫንቃው ነውና

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
               •➢ ሼር // SHARE
  💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ተወለደ_ጌታ_ተወለደ

ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ

አንዲት ብላቴና የአስራ አምስት ዓመት ልጅ
ጌታን ወለደችው በመላእክት አዋጅ
በህቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ
       አዝ = = = = =
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋሕዶ
አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ
       አዝ = = = = =
ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች
እንደምን አምላክን በማህፀን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ጌጠ የሔዋን አለኝታ
       አዝ= = = = =
አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
በምድር ተፈልጎ እንዳንች አልተገኘም
በሀሳብ በግብር ንፁህ ስለሆነች
የአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች
      አዝ = = = = =
ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች
እንደምን አምላክን በማህፀን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደቸው ድንግል የሔዋን አለኝታ

   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#በኤፍራታ_በጎል

በኤፍራታ በጎል በኤፍራታ ሆ
የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ ተወለደ ጌታ/2/

ብርሃን ተገለጠ ጨለማ ተዋጠ
በራ በምድር ላይ የናዝሬቱ ፀሃይ የናዝሬቱ ፀሃይ
ሠራዊት ሳያዘምት ተኝቶ በበረት
በታላቅ ማዳኑ ማረከን ህፃኑ/2/

አዝ________________

ዓለምን በእፍኙ ጨብጦ አዳኙ
በከብቶቹ ግርግም አቀፈችው ማርያም/2/
መጡ ሰብዐ ሠገል ሊሠግዱ ለልዑል
ዕጣን ለክህነቱ ወርቁን ለመንግስቱ/2/

አዝ________________

የመቅደሡ ናፍቆት በክንዱ መዘርጋት
ቤንሆር ተዋረደ መሲህ ተወለደ /2/
የጥሉ መንጦላይት ለይቶን ከገነት
ሕይወትን አገኘን ልደቱ አስታረቀን/2/

አዝ________________

ምድር ተፈወሠች አዳኟን ስላየች
ሠውና መላዕክት ተቀኙ በአንድነት ዘመሩ በአንድነት
በሠላም አለቃ ኩነኔው ሊያበቃ
ስቃይ ሊመነገል ወለደችው ድንግል/2/

አዝ________________

ብርሃን ተገለጠ ጨለማ ተዋጠ
በራ በምድር ላይ የናዝሬቱ ፀሃይ የናዝሬቱ ፀሃይ
ሠራዊት ሣያዘምት ተኝቶ በበረት
በታላቅ ማዳኑ ማረከን ህፃኑ/2/

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#አንፈርዐፆ_ሰብዐ_ሰገል

አንፈርዐፆ ሰብአ ሰገል/2/
አምኃ ሆሙ ኧኸ አምጽኡ መድምመ/2/
       አዝ-----
ምድር አይታ ቸርነትህን
በበረት ውስጥ መጠቅለልህን
ትህትናህን እያደነቀች
በደስታ ለአንተ ዘለለች
       አዝ-----
ጥበቃ ላይ እያሉ ተግተው
ከመላእክት ዜማውን ሰምተው
እረኞችም እየተመሙ
ለምስጋና ተሽቀዳደሙ
       አዝ-----
ያለ ገደብ ስለወደደን
ስጋ ለብሶ የተዛመደን
መድኃኒት ነው ሃይሉ እወቁ
የተዋህዶ  ምስጥር አድንቁ
       አዝ-----
የተባለው ተስፋችን ደርሶ
የአብ ቃሉ ስጋዋን ለብሶ
ስላየነው በአይኖቻችን
እጥፍ ድርብ ሆኗል ደስታችን

   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#በኤፍራታ_ምድር

በኤፍራታ ምድር በቤተልሔም/፪/
ጌታ ተወለደ ከድንግል ማርያም/፪/
ብርሃናዊው ኮከብ ከሰማይ ዝቅ አለ/፪/
ፍጥረትም ዘመረ ሃሌሉያ እያለ/፪/
#አዝ
መንጋውን በሌሊት ሲጠብቁ እረኞች
ከሰማይም ሰሙ ታላቅ የምሥራች
በመላእክቱ ግርማ ምድር ስታበራ
የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ
#አዝ
ድንገትም የሰማይ ሠራዊት ተገልጠው
በአንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋር ሆነው
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው
ሰላምም በምድር በጎ ፈቃድ ለሰው
#አዝ
ቤተልሔም ሄደው ጌታን ተሳለሙት
ከእናቱ ጋር ሆኖ በግርግም አገኙት
የመላእክትን ዜና እረኞች አወሩ
በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ
#አዝ
ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ፍስሐ ደስታ
በዳዊት ከተማ ተወለደ ጌታ
ሕፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈለጉት
እርሱ ነው ለሰዎች የድኅነት ምልክት

   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ናሁ_ሰማህ_ናሁ

ናሁ ሠማህ ናሁ በኤፍራታ/2/
ናሁ ሠማህ ናሁ በኤፍራታ/2/
       አዝ-----
በኤፍራታ      ኧኸ   በኤፍራታ        ኧኸ
ተወለደ         ኧኸ   የዓለም ጌታ     ኧኸ
ከንፅህይት    ኧኸ    ከድንግል        ኧኸ
ሥጋን ነሳ      ኧኸ    አማኑኤል       ኧኸ
የሠይጣንን   ኧኸ    ጥበብ ሊሽር   ኧኸ
ሠው ሆነልን  ኧኸ    እግዚአብሔር   ኧኸ
       አዝ-----
በኤፍራታ      ኧኸ    በኤፍራታ   ኧኸ
በኤፍራታ      ኧኸ    በበረት       ኧኸ
ተወለደ         ኧኸ    መድኃኒት   ኧኸ
ዘመሩለት      ኧኸ    መላዕክት   ኧኸ
ከእረኞች ጋር  ኧኸ    በአንድነት   ኧኸ
       አዝ-----
በኤፍራታ         ኧኸ  በኤፍራታ       ኧኸ
ጥበበኞች        ኧኸ  ሊሠግዱለት   ኧኸ
ኮከብ አይተው  ኧኸ  ተከተሉት        ኧኸ
ደስ አላቸው      ኧኸ  ሲያገኙት        ኧኸ
ሲቀበሉ            ኧኸ  በረከት           ኧኸ
       አዝ-----
በኤፍራታ    ኧኸ   በኤፍራታ        ኧኸ
አቀረቡ       ኧኸ  እጅ መንሻውን   ኧኸ
ከርቤን እና   ኧኸ  ወረቅ ዕጣኑን   ኧኸ
እመቤቴ      ኧኸ   ደስ ይበልሽ     ኧኸ
መድኃኒቱን   ኧኸ   ስለወለድሽ     ኧኸ
       አዝ-----
በኤፍራታ              ኧኸ   በኤፍራታ ኧኸ
በጨለማ              ኧኸ   ለሚኖሩ   ኧኸ
በመርገም ውስጥ  ኧኸ   ለነበሩ     ኧኸ
ብርሃን ወጣ          ኧኸ   አእውነት  ኧኸ
ከብስራቷ              ኧኸ   እመቤት   ኧኸ
       አዝ-----
በኤፍራታ       ኧኸ    በኤፍራታ   ኧኸ
ድምፅ ሠማን ኧኸ    ከበረቱ       ኧኸ
ሢዘምሩ         ኧኸ   መላዕክቱ    ኧኸ
ዛሬም እኛ      ኧኸ    እንደነሡ     ኧኸ
ዘመርንለት      ኧኸ   በመቅደሡ   ኧኸ

   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


እንኳን ለሊቀ መላእክ ቅዱስ ገብርኤል #ዓመታዊ በዓል በሰላም በጤና  አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!

#ታህሳስ_19 የራማውን ልዑል ሊቀ መላእክ ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

❖የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጠብቆት አይለየን።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


ተወዳጁ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ አዲስ የዝማሬ አልበም

      🙏 ተመሰገን ተመስገን 🙏

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#እመኑ_በእርሱ

እመኑ በእርሱ ድንቅ ያደርጋል ጌታ
በረዶ አዝንቦ  ጠላት እየመታ
ውቅያኖስ ጥልቁን ፈትሎ ያተነነ
ነገር ለወጠ ሁሉ በርሱ ሆነ{፪}

እመኑ በእርሱ  ተራራው ነደደ እመኑ በእርሱ ሸለቆ ታወከ
እመኑ በእርሱ ዝኩ ተስባብሮ እመኑ በእርሱ አለቱ ደቀቀ
እመኑ በእርሱ የአህዛብ ጣዖታት እመኑ በእርሱ ብፊቱ ረገፉ
እመኑ በእርሱ በስሙ የታመኑ እመኑ በእርሱ ውጀቡን ቀዘፉ

እመኑ በእርሱ የማይነጋ ለሊት እመኑ በእርሱ የማያልፍ ቀን የለም
እመኑ በእርሱ ሁሉ ይቻለዋል እመኑ በእርሱ ጌታ መድሐኔያለም
እመኑ በእርሱ ፍቅር ነው ዘላለም እመኑ በእርሱ ደግ አባት ለልጁ
እመኑ በእርሱ ሁሌ ተዘርግታ እመኑ በእርሱ ትኖራለች እጁ

እመኑ በእርሱ ወገን የማይሰብረው እመኑ በእርሱ ፅኑ መርከብ አለ
እመኑ በእርሱ አንፈራም አንሰጋም እመኑ በእርሱ ከርሱ ጋር እያለ
እመኑ በእርሱ ጠላት ተሸንፈዋል እመኑ በእርሱ ሰይጣን አፍሮዋል ዛሬ
እመኑ በእርሱ ወይኔ ይለዋወጥ እመኑ በእርሱ በታላቅ ዝማሬ

እመኑ በእርሱ ጎዶሎ አይሰራም እመኑ በእርሱ የጠላት ፉከራ
እመኑ በእርሱ የማይተወን ጌታ እመኑ በእርሱ አለ ከእኛ ጋራ
እመኑ በእርሱ እጅግ አትረፍርፎ እመኑ በእርሱ ጸጋ ከበዛልን
እመኑ በእርሱ በሞት ጀርባ ቆመን እመኑ በእርሱ ገና እንዘምራለን


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች⬇️
            •➢ ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.