🌾የጁምዓ እለት ትሩፋት
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌾 فضلُ يوم الجمعةِ
⚂የጁምዓ እለት የሳምንቱ ምርጥ ቀን ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አላህ ዘንድ ከቀናቶች ሁሉ በላጩ የጁምዓ እለት ነው።» ብለዋልና በዚህ እለት ስራዎቻችንን ይበልጥ ማሳመር ይገባናል።
📚صححه الألباني في
السلسلة الصحيحة - رقم: (1502)
صحيح الجامع - رقم: (1098)
⚂የጁምዓ እለት በጀማዓ (በህብረት) የተሰገደ የፈጅር ሰላት ከየትኛውም ወቅት ሰላት በላጭ ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አላህ ዘንድ በላጩ ሰላት በጁምዓ እለት በጀማዓ የተሰገደ የሱብህ ሰላት ነው።» ብለዋልና ከየትኛውም እለት በበለጠ ቀድሞ ለመገኘት መጣር ይበልጥ ያስመነዳል።
📚السلسلة الصحيحة -
الألباني صحيح - رقم: 1566
⚂የጁምዓ እለት ከሌሎች ቀናት በበለጠ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት የማውረጃ ቀን ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«በጁምዓ ቀንና በጁምዓ ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ። በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ያወርዳል።» ብለዋልና ትንሽ ሰርተን ከአስር እጥፍ በላይ ለማግኘት ከወዲሁ እድሉን እንጠቀም።
📚صحيح الجامع
الألباني حسن - رقم: 1209
⚂የጁምዓ እለት መኖሩም መሞቱም ለሙስሊሙ ፀጋ ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«ማንኛውም ሙስሊም የጁምዓ ቀን ወይም የጁምዓ ሌሊት የሞተ እንደሆን አላህ ከቀብር ፈተና ሳያድነው አይቀርም።» ብለዋል።
ስለዚህ በመጀመርያ የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን
♂አርካኑል ኢስላምን በስርዓቱ የተገበረ ሙስሊም እንሁን።
♂በማስከተልም አላህ በራህመቱ ከቀብር ፈተና እንዲጠብቀንና ለዚህ ሰበብም እንዲያበቃን ሁሌም እንለምነው።
📚حسنه الألباني في صحيح الترمذي - رقم: (1074) ، تخريج مشكاة المصابيح - رقم: (1316) الألباني :إسناده حسن أو صحيح لغيره
⚂የጁምዓ እለት የሳምንቱ ከኃጢኣት መንፂያ ቀን ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱት በስተቀር አምስቱ ሰላቶች እንዲሁም ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ያለውን ኃጢኣት ያብሳሉ።»¹ በሌላ ዘገባም «ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ላለው ማበሻ ናቸው።»² ብለዋል።
ስለዚህ ከከባባድ ወንጀሎች በመራቅ ወይም ተውበት በማድረግ፣ አምስቱን እለታዊ ሰላቶች ጠብቆ በመስገድና የሳምንቱን ልዩ የስብስብ ቀን የጁምዓን ሰላት በመስገድ ተጨማሪ ግድፈቶቻችንን እናፅዳ።
¹📚صحيح مسلم - رقم: (233)
²📚الألباني - صحيح الجامع رقم: (3110)
⚂ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የመከባበርያ ቀን ነው።
ሁሉም ሙስሊም ክቡር ነው። ሀብታም ከድሃ ታላቅ ከታናሽ፣ ገዢ ከተገዢ የሚለይበት ቦታ አየደለምና መስጂድ ሲደርስ ያገኘበት ክፍት ቦታ ሊቀመጥ ይገባዋል እንጂ ማንንም አስነስቶ ወይም እንዲነሳ አስደርጎ ሊቀመጥ አይገባውም።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አንዳችሁ በጁምዓ ቀን ወንድሙ የተቀመጠበት ቦታ ሊቀመጥ ብሎ እንዳያስነሳው። ነገር ግን ሰፋ ሰፋ አድርጉ ይበል።» ብለዋልና ኢማሙ ኹጥባ ያልጀመሩ እንደሆነ ሰዎችን እንዲጠጋጉለትና እንዲሸጋሸጉለት በስርዓት ማግባትም ይችላል።
📚صحيح مسلم - رقم: (2178)
⚂ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የፅዳት ቀን ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አንዳችሁ ወደ ጁምዓ ሲሄድ ይታጠብ።» ማለታቸው ተዘግቧል።
📚صحيح البخاري - رقم: (882)
⚂ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የቁርኣን ቀን ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቀጣዩን ብለዋል☞
«በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።»
📚حسنه الألباني في
تخريج مشكاة المصابيح - رقم:(2116)
በሌላም ዘገባ እኛ በተለምዶ ሐሙስ ማታ በምንለው የጁምዓ አጥቢያ ምሽቱን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው አጅሩ እጅግ በጣም ሰፊ ነው።
«ለይለቱል ጁምዓ ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ (በካዕባ) መካከል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
📚صححه الألباني في
صحيح الترغيب -رقم: (736)
⚅በተጨማሪም የጁምዓ እለት የማንንም ክብርና መብት የማንጥስበት፣ ከውስጥም ከውጭም በወሬም ሆነ በሌላ ጉዳይ ሰውን እንዳንረብሽ የተከለከልንበት ልዩ ቀን ነው። ይህንንም ለዒባዳ ብለን መስጂድ እንኳን መጥተን ክፍት ቦታ ፍለጋ ከሰው ትከሻ ላይ እየተረማመድን እንዳንሄድ ከልክለውናል። ኢማሙ ኹጥባ ላይ ሳሉ ምንም አይነት ቃል ትንፍሽ እንዳንል ተከልክለናል። ጣቶቻችንን ከመሰባበርም ሆነ ልብሶቻችንን ሆነ ሌላ ነገር አየነካካን እንዳንጫወት ተከልክለናል።
ማንኛውም ሰው በጁምዓ እለት ወደ መስጂድ ሲመጣ ክፍት ቦታ ከፊትለፊቱም ሆነ ከጎኑ ክፍተት እንዳይኖር ወደፊት መጠጋትን የመሰለ እንደገባ በማመቻቸት መቀመጥ አለበት። ምክንያቱም ከኋላ የሚመጡት ቦታ ፍለጋ ስህተት እንዳይፈፅሙና ክብሩንም እንዳይነኩ ይረዳልና። በመሰረቱ ቦታ ፍለጋ ከሰው ትከሻ ላይ መረማመድ ተከልክለናል። ኢማሙ ኹጥባ ላይ ሳሉ ምንም አይነት ቃል ትንፍሽ እንዳንልም ተከልክለናል። ጣቶቻችንን ከመሰባበርም ሆነ ልብሶቻችንን ሆነ ሌላ ነገር አየነካካን እንዳንጫወትም ተከልክለናል።
ባጠቃላይ
የሰው ትከሻ አትርገጥ~እንዳትወራገጥ
አርፈህ ተቀመጥ~በፀጥታ አድምጥ
ለጌታህ እጅ ስጥ
اللهم صل وسلم على نبينا محمد وعلى آله وأصحابه أجمعين
~
Abufewzan
© ተንቢሀት
Via = ኡስታዝ አህመዲን ጀበል