Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ኸጢቦች ጥንቃቄ ብታደርጉ
~
ባለፉት ሳምንታት ጁሙዐን በተለያዩ ሰፈሮች ሰገድኩኝ። ሁሉም ጋር የገጠመኝ ዝናብ እየጣለ ረጅም ኹጥባ ነው የሚያቀርቡት። ዝናቡን ስላላወቁ ነው እንዳይባል ኹጥባቸውን ሲያገባድዱ ውጭ ላይ ዝናብ ስላለ ጠጋ ጠጋ በሉ ይላሉ። ይህንን ካሉ በኋላም በሶላታቸው ላይ እንደ ወትሮው አድርገው ቁርኣን ይቀራሉ። አንድ ሰው ቢያደርገው ራሱ የሚገርም ነው። በተለያዩ ሰፈሮች እንዲህ ሲደጋገም ግን የበለጠ ይደንቃል። "ይሄ ገርሞ፣ ገርሞ የሚገርም ነው" አሉ ሸይኽ መሐመድ ወሌ።
ኸጢቦቻችን ሆይ! ኹጥባችሁንም ሶላታችሁንም ሰጋጁንና ወቅቱን ታሳቢ እያደረጋችሁ መጥኑ'ንጂ። ዝናብ እየጣለ የምታደርጉት ኹጥባ በሌላ ጊዜ ከምታደርጉት ኹጥብ እንዴት ተመሳሳይ ይሆናል? ብዙ ሰጋጅ ዝናብ ላይ እያለ የሚፈፀም ሶላት እንዴት ከሌላው ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ይሆናል?ይሄኮ ግዴለሽነትን ነው የሚያሳየው። ለምን ሰው በዚያ መልኩ እንዲያስባችሁ ታደርጋላችሁ? ለምን ሰው ተረባብሾ ተቀይሞ እንዲሰግድ ታደርጋላችሁ? ራሳችሁን ዝናብ ላይ ያሉ ሰጋጆች ቦታ በማድረግ የሚኖራቸውን ስሜት አስቡ እስኪ። ሰው ዝናብ እየተመታ የምታስረዝሙትስ ቁርኣን ሱና የሚሆን መስሏችሁ ነው? ሱናው የሰዎችን ሁኔታ ከግምት ያስገባ አፈፃፀም ነው። ነብያችን ﷺ የሚያለቅስ ልጅ ድምፅ ሲሰሙ እናቱ እንዳትረበሽ ብለው ሶላት ያሳጥሩ ነበር። እባካችሁ! ቢቻል በየትኛውም ጊዜ ኹጥባ በልክ አድርጉ። ካልሆነ ቢያንስ ቢያንስ በዝናብ ጊዜ እንኳ ትኩረት አድርጉ። ያለንበት ወቅት ክረምት መሆኑም አይረሳ።
መልእክቱን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለማይኖሩትም አድርሱልኝ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor