"ምንም አይነት ነገር ቢመጣ ከዚህ የሚከብድ አይመስለኝም....ከዛን ቀን በላይ ከባድ ምሽት የሚኖረኝ አይመስለኝም...እጃችሁን ይዤ እያለቀስኩኝ ነበር...በተኛችሁበት ይቅርታ እየጠየቅኳችሁ ነበር....በብርሀን አይናችሁን እያየሁ ማድረግ አልቻልኩም...."ጥያቹ ልሄድ ነው" ለሚል መርዶ የሚሆን ይቅርታ ይኖራል...?....."ካሁን በኃላ አይኔን ስለማታዩት ይቅር በሉኝ..."....ይባላል...?
ለረጅም ሰአት እያየኃችሁ ነበር ....ስትተኙ ደግሞ ይበልጥ ታሳሱ ነበር.....እንቅልፋችሁ ላይ እምነት ነበረ....ስትነቁ ሁሉም ነገር እንደሚቀጥል የሚነግራችሁ እምነት....
"ለምን እውነቱን አልነገርኳቸውም...?"....የምልበት ቀን አበዛዙን አታውቂም እድሏ.....የሆንኩትን አታውቂም እድሏ....ስንት ቀን እግሬን አንስቼ እንደመለስኩት አታውቂም ልጄ.....አንዴ አቅፌያችሁ ለመመለስ የፀለይኩትን ፀሎት አታውቂም ልጄ....ለልደታችሁ ሻማ እንደማበራ....ፎቶአችሁን በትልቁ እንደሰቀልኩ... የብቻ ቤቴ አድባር እናንተ እንደሆናችሁ አታውቂም የኔ ልጅ....
ከአመታት በኃላ ተመልሼ ልመጣ ሻንጣዬን ሸክፌ ነበር....እንዳትጎዱብኝ ብዬ ተውኩት እንጂ......ይቅር በሉኝ ልጆቼ....ይቅር በሉኝ....አልመጣም አትጠብቁኝ....እወዳችኃለሁ።".....ብሎ የሚዘጋ ደብዳቤ አንብቤ ለእህቴ ሰጠኃት....ስለ እናቷ የማወቅ መብቷን ከዚህ በላይ ልጋፋ አልፈለግኩም.....
'መምጣቴ ይጎዳችኃል' ነው ያለችው አይደል....! ...አሁን ማን ይሙት ለዘመናት ከእናት መለየት ቆዳ ተልጦ ጨው እንደተነሰነሰበት ሰውነት እንደሚለበልብ ጠፍቷት ነው....?...እንደዚህ ይደረጋል....?....አልመጣም ለማለት ይሄ ሁሉ ጊዜ ይጠበቃል.....
**
እውነቱ ግን ራስ ወዳድ መሆኗ ላይ ነው...የልጆቿን እምባ እና ድንጋጤ በአይኗ ማየት የሚፈጥርባትን ከባድ ስሜት ለማምለጥ ነው...ሁላችንም እንዲህ አይደል የምናደርገው....እኛ ሳናይ ስለሚወርዱት ዘላዎች ማሰብ አንፈልግም....ብቻ ማምለጥ....ብቻ መፈርጠጥ...
ብናምንም ባናምንም ሁላችንም ስለሚጎዳው ስሜታችን ስናስብ እንደደነበረ በሬ የሚያስፈረጥጥ ራስ ወዳድነት አለብን...
✍ሸዊት
ቀጣይ የመጨረሻው ክፍል ✨
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1