የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ።
ተከሳሽ አስቻለው የኔዓለም የተባለ ግለሰብ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 አካባቢ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 16 ልዩ ቦታው ህፃናት ኦፕሪስ የተባለ አካባቢ የዉሃ ፓምፕ እና የላሜራ ብረት ከ30ኪ.ግ ሚስማር ጋር በመዝረፍ ኮድ 1 ሰሌዳ ቁጥር 75329 በሆነች ባጃጅ ጭኖ ለመሄድ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሏል።
ምርመራውም በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ በ6ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ክፍል ተጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተላከ።
የምርመራ መዝገቡ የደረሰው የባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤትም ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ግለሰቡ በ4 ዓመት ፅኑ እስራት እንድቀጣ ወስኖበታል።