ሰላም ለሁሉም፣ሁሉም በሰላም፣ሁሉም ለሰላም ...
ሰላም ለሁሉም...
ሰላም ለሰው ልጆች፣ሰላም ለእንስሳት፣ሰላም ለዕፅዋት፣ሰላም ህይዎት ለሌላቸው መሰረት ነው።ሰላም ከጤናም በላይ ነው ጤነኛም ሆኖ በግጭት የተነሳ መሞት ወይም አካልን ማጣት ወይም የስነልቦና ህመምተኛ መሆን አለና።
ያለሰላም የሰው ልጅ ምንም ነገር መከወን፣ምንም ነገር መፈፀም ሆነ ማሳካት ፈፅሞ ይሳነዋል ።ሰርቶ መኖር፣በልቶ ማደር፣ተምሮ መለወጥ፣ነግዶ ማትረፍ፣አርሶ ማምረት፣ወልዶ መሳም፣አርሶ መቃም የሚባሉ የሰው ልጅ የህይወት ሁነቶች አይታሰቡም።ሌላው ቀርቶ ግጭት ለሞተም አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል፣በጦርነት ምክንያት ሞተው በክብር መቀበር የነበረባቸው ግለሰቦች ሳይቀበሩ መቅረታቸው እንደማሳያ መውሰድ ይቻላል።
ያለሰላም እንሰሳቶች ይገደላሉ፣ይታደናሉ፣መኖሪያቸው ይወድምና ብርቅየ የተባሉ የእንሰሳት ሀብቶቻችን ከሀገር ይሰደዳሉ፣ለመኖር ይቸገራሉ፣የሰው ልጆች የግጭት ቀጥተኛ ፍዳ በቀጥታ አሊያም በተዘዋዋሪ በእንሰሳት ላይም ይከሰታል።በእንክብካቤ ፋንታ ይገድላሉ።
ያለ ሰላም ህይዎት ሳይኖራቸው ትርጉምና ፋይዳ ያላቸው ነገሮችም ትርጉማቸውን ይነጠቃሉ።መሰረተ ልማቶች ይወድማሉ፣ህንፃዎች ይፈራርሳሉ፣ትምህርት ቤቶች፣ድርጅቶች የመሳሰሉት ህይዎት ሳይኖራቸው ህይዎት የሚዘሩ የፍጡራን መሰረቶች በራሱ በሰው ልጅ የጦርነት ተግባር እንዳልነበሩ ይሆናሉ።ይሄንንም ከሀገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ የምናያቸው፣የምንሰማቸው የጦርነት ውጤቶች በቂ ማሳያ ናቸው።
ጠቅለል ሲል ❝ሰላም ለሁሉም❞
ሁሉም በሰላም...
ሁሉም ነገር ከሰላም ጋር የጠበቀ ግንኙነት፣የጠነከረ ቁርኝት አለው።ሰላም ሲኖር ሁሉም ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ተዛምዶ ማስቀጠል ይቻለዋል።ሰላም ሲኖር ፍቅር አለ፣ሰላም ሲኖር መረጋጋት፣መተባበር፣ ወጥቶ መግባት፣ሰርቶ መብላት፣መማር፣መውለድ ይሳለጣል።
ሰላም ሲኖር፦ህይዎት የተፈጥሮ ዑደቷን ታስቀጥላለች፣ህይዎት የሌላቸው ነገሮችም ህይዎት ላላቸው ፍጥረታት የሚሰጡትን ጥቅም መስጠታቸውን አያቋርጡም ።
በአጠቃላይ ❝ሁሉም በሰላም❞
ሁሉም ለሰላም...
ሁሉም በሰላም ካልን ሁሉም ለሰላም የበኩሉን አበርክቶ ማድረግ ይጠበቅበታል።ሰላም የሚረጋገጠው በአንድ ወይም በተወሰኑ አካላት ጥረት አይደለም በሁሉም አካል የጋራና የጠነከረ እርብርብ እንጂ።ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ከወዛደር እስከ ወታደር፣ከአርሶ አደር እስከ አርብቶ አደር ...ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ግድ ይላል።ሁሉም ለሰላም ከሰራ ሰላም በሁሉም ላይ ይሰራል።
ስለሆነም ❝ሁሉም ለሰላም❞