"የሴቶችን ጥቃት ለማስቆም የወንጀል መከላከልና ምርመራ ስራዎችን ማሻሻል አለብን" ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ የተከበረውን የጸረ ፆታዊ ጥቃት ነጭ ሪቫን ቀን ምክንያት በማድረግ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ሰራተኞች ምክክር አድርገዋል።
"የሴቷ ጥቃት የኔ ነው፤ ዝም አልልም" በሚል መሪ መልዕክት በተከበረው በዚህ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሸን ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን ቀኑን ስናስብ በተለያዬ አጋጣሚ ፆታዊ ጥቃት የሚደርስባቸውን ሴቶች ለመጠበቅ ግንዛቤያችንን በማሳደግ መሆን አለበት ያሉት ኮሚሽነሩ ከገጠር እስከ ከተማ የሴቶች ጥቃት እየጨመረ መሆኑን ገልፀዋል።
በተለይም አሁን በገጠመን የፀጥታ ችግር ቀዳሚ ተጠቂ የሆኑትን ሴቶች ከፃታዊ ጥቃት እስከ ሀብት መነጠቅ ድረስ ባለው ሂደት ቅድሚያ ሰጥቶ በልዩ ትኩረት ለመጠበቅ የወንጀል ምርመራ ስራዎቻችንን ማሻሻል ይጠበቅብናል ብለዋል።
የፖሊስ ኮሚሽኑ ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሀገርነሽ ፀጋው በበኩላቸው በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በትብብር መስራት አለብን ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተለያዩ ክስተቶች ቅድሚያ ተጋላጭ ከሚሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶች፣ ሕፃናትና አካል ጉዳተኞች በመሆናቸው በልዩ ትኩረት ለመጠበቅ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።