"በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በአብዛኛው በቤት ውስጥ በመሆኑ ከደረስንበት ይልቅ ያልታወቀው የበዛ ነው"
ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ_የሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኅላፊ
በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፀረ ፃታ ጥቃት ቀንን ለመዘከር በተሰናዳው መድረክ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ አንደኛው ችግር ሌላኛውን እየወለደ የሴቶችን ተጠቂነት አባብሶታል ብለዋል።
ስለ ስርዓተ ፆታ ያለው ግንዛቤ ባለመቀዬሩ ከጎጂዎች ይልቅ ተጎጂዎች የሚደበቁበትና የሚሸማቀቁበት አግባብ እየተፈጠረ መሆኑን ያነሱት ቢሮ ኀላፊዋ ፖሊስ ያለመገፋፋት መስራት ይኖርበታል። በተለይም በቤት ውስጥ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ከታወቀው ይልቅ ያልተደረሰበት ስለሚበልጥ ድርጊቱን ለማስቆም ፖሊስ የረቀቀ የምርመራ አቅምን ማሳደግ ይጠበቅበታል ብለዋል።
በአማራ ክልል የፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪና አሰልጣኝ የሆኑት ወ/ሮ አበባ ታደሰ ለመድረኩ ታዳሚዎች በሴቶችና ህፃናት ጥቃት ዙሪያ ፁሁፍ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት "የሴቶችን ጥቃት ለማስቆም የህግ አስከባሪዎችን ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል"ብለዋል።
በተለያዩ ክስተቶች ቅድሚያ ተጋላጭ ከሚሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶች፣ ሕፃናትና አካል ጉዳተኞች ናቸው የሚሉት ወ/ሮ አበባ ተጋላጭነታቸውን በመቀነስ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል እና የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ለመሥራት ቀኑ ታስቦ መዋሉ ጠቀሜታው የጎላ ሲሆን በተለይም ፖሊስ እንደተቋም የሴቶችን ጥቃት የመከላከልና የመጠበቅ ድርብርብ ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በግጭቶች እና በሌሎች ተያያዥ ችግሮች ምክንያት የሚፈፀሙ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች መበራከታቸውን ስንመለከት ከቀን ማክበር በዘለለ ችግሩን ለመከላከል መተባበር እንዳለብን ያሳያል ብለዋል።
የሴቷ ጥቃት የኔም ነው፤ዝም አልልም !