❝የሰላም ሂደቱን አጠናክሮ በመቀጠል የማህበረሰባችንን ችግር መፍታት የሁላችንም ድርሻ ነው።❞የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር እሱባለው መኮንን
የብሄረሰብ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እሱባለው መኮንን እንደገለፁት በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ከ162 በላይ በተሳሳተ መንገድ ወደጫካ የገቡ ታጣቂዎች እጂ የሰጡ ሲሆን ይህንንም ፈር ቀዳጅ ተግባር እንደ ተሞክሮ በመውሰድ አሁንም በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ ወደ ማህበረሰቡ ሊቀላቀሉ ይገባል ብለዋል።
እነዚህ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ መንግስት እና ማህበረሰቡ በደመቀ ሁኔታ የተቀበላቸው ሲሆን ይህንንም ኹነት በመረዳት ቀሪዎቹም ከመጠራጠርና ከመፈራራት በመላቀቅ ወደማህበረሰቡ በሰላም መምጣት ይኖርበታል ነው ያሉት ኃላፊው።
የዞኑ ብሎም የክልሉ ሰላም ይመለስ ዘንድ ከነፍጥና ሸፍጥ ባሻገር ጊዜ መጣኝ ተግባሩ ሰላምን አማራጭ ሳይሆን ምርጫ ማድረግ ግደታችንና ብቸኛው መፍትሄ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።
እንደ ኮማንደር እሱባለው ገለፃ አሁናዊ የዞኑ የፀጥታ ሁኔታ አንፃራዊ ሰላም የሚስተዋልበት ሲሆን ይህም በፀጥታ ኀይሉ እና በማህበረሰቡ ልዩ ትጋትና ቅንጂት የተገኘ አንፀባራቂ ድል ነው ብለዋል።