‘’የጸጥታ መዋቅሩን እና የኅብረተሰቡን አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም ዘላቂ ሰላም የማፅናት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል’’ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር
አማራ ፖሊስ፦ ጥር 26/2017 ዓ/ም
የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ሕግ የማስከበር ሥራ አፈፃፀም እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ገምግሟል። ከሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው ግምገማው የተካሄደው።
በግምገማ መድረኩ የተገኙት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ኀላፊ አይተነው ታዴ እንደ ክልል የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማስከተሉን ተናግረዋል።
የጸጥታ መዋቅሩ በጠንካራ ሕዝባዊ ድጋፍ ታጅቦ በከፈለው መስዋዕትነት የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው መመለሳቸውንም ምክትል አሥተዳዳሪው ገልጸዋል።
የፀጥታ መዋቅሩን እና የኅብረተሰቡን አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም የብሔረሰብ አሥተዳደሩን ዘላቂ ሰላም የማፅናት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ምክትል አሥተዳዳሪው አንስተዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ጌታቸው ቢሻው የሕይዎት እና የአካል መስዋዕትነት ተከፍሎበት የተገኘው ሰላም እንዳይቀለበስ ዘላቂ ሰላምን የማስፈን ሥራ ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖረው እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
በብሔረሰብ አሥተዳዳሩ አሁን እየመጣ ላለው ሰላም የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የኅብረተሰቡ ሚና የጎላ እንደኾነም ኀላፊው አንስተዋል።
የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት በሠሩት ሥራ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከ240 በላይ የታጠቁ ኀይሎች የመንግሥት እና ሕዝብ የሰላም ጥሪን ተቀብለው ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቅለዋልም ነው ያሉት።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር እሱባለው መኮንን በበኩላቸው ለሕገ መንግሥቱ እና ለሕዝብ ዘብ የቆመ የጸጥታ መዋቅር በመገንባት ሕግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።