19ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት ስፖርት ውድድር የተሳተፈው አማራ ፖሊስ ውድድሩን በአራተኝነት አጠናቀቀ።
መጋቢት 1/2017 ዓ.ም (አማራ ፖሊስ)፡-ከየካቲት 22 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው 19ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት ስፖርት ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም የካቲት 30/2017 ዓ.ም በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል፡፡
በ10 የስፖርት ውድድር ዓይነቶች የፌዴራል ፖሊስን ጨምሮ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችና 12ቱ ክልል ፖሊስ ተቋማት መካከል ሲካሄድ በቆየው የስፖርት ውድድር የአማራ ፖሊስ በሶስት የስፖርት ዓይነቶች ማለትም የወንዶች እግርኳስ፣አትሌቲክስና ኢላማ ተኩስ በመሳተፍ ውድድሩን በአራተኝነት አጠናቋል።
አማራ ፖሊስም በኢላማ ተኩስ ውድድር ዋንጫ ያስመዘገበ ሲሆን በእግር ኳስ አራተኛ ደረጃ፤ በአትሌቲክስ ሶስት ወርቅ፣ ሁለት ብር፣3 ነሀስና 10 ዲፕሎማ በማምጣት ውድድሩን በአራተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
116ኛውን የፖሊስ ምስረታን አስመልክቶ የተዘጋጀው 19ኛው ውድድር ተተኪ ስፖርቶኞችን ከማፍራት ባሻገር የፖሊስ ሰራዊቱን ጓዳዊ ዝምድና ማጠናከሩ ተገልጿል።
ውድድሩ ከተቋረጠበት 2004 ዓ.ም 12 ዓመት በኋላ መሰናዳቱ መልካም ቢሆንም ከተጨዋች ተገቢነትና ዝግጅት አንፃር የነበሩ ክፍተቶችን በማረም በሚቀጥለው ዓመት በድሬደዋ ከተማ ለሚዘጋጀው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ውድድር ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚገባ ተገልጿል።
በማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ድሬዳዋ ፖሊስ ቀጣዩ የ20ኛ ሀገር አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት ስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጅ የተመረጠ ሲሆን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተረክቧል።