#ቢድዓ_ሁሉ_ጥሜት_ነው
🚩ተከታታይ ፅሑፍ ክፍል ፡ 6⃣
🏴ንዑስ ርእስ ፦ መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች የሚያመጧቸው ብዥታዎች ላይ የሚሰጥ መልስ
__
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው.
°
♦️እስካሁን በነበሩት 5 ተከታታይ ፅሑፎች ላይ ቢድዓ ማለት ቁርአናዊም ሆነ ሐዲሳዊ እንደዚሁም እንደኢጅማዕ ያሉ ትክክለኛ ማስረጃዎች የማይደግፉት ለዲን ተብሎ የሚሰራ ተግባር ወይም እምነት መሆኑን ተረድተናል ፤ ቢድዓ ሁሉም ጥሜት መሆኑን ከሐዲስ እና ከሰለፎች ንግግርም ለማየት ሞክረናል። እንደዚሁ ያልተገደቡ የአምልኮ ዘርፎችን መገደብ , የተገደቡ የአምልኮ ዘርፎችን ደግሞ ገደባቸውን ማንሳትም ቢድዓ እንደሚሆን ተመልክተናል። በተጨማሪም ቢድዓ ሁሉም ጥሜት አይደለም የሚሉ ሰዎች የሚያመጧቸውን ዋና ዋና ማምታቻዎች በመጥቀስ መልስ ሰጥተናል። ዛሬ በአላህ ፍቃድ መውሊድ አክባሪዎች የሚያነሷቸው ብዥታዎች ላይ የሚሰጡ ምላሾችን ተመልክተን ፅሑፋችንን እናሳርጋለን።
°
♦️መውሊድን ለማክበር በዋናነት የሚጠቅሱት ነገር በዲን ውስጥ መልካም ቢድዓ መፍጠር ይቻላል ብለው በክፍል 4 እና 5 ላይ የተመለከትናቸውን ማምታቻዎች ነው። እነዚህ ማምታቻዎች ደግሞ አዲስ ቢድዓ መፍጠር እንደማያስችላቸው መልስ ሰጥተንበት አልፈናል። ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱትን ነገር እንመልከት ፡
▪️#የመጀመሪያ_ማምታቻ ፡ ተከታዩ የቁርአን አንቀፅ ነው ፦
{ قُلْ بِفَضْلِ اللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ }
[| «በአላህ ችሮታና #በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡ |] (ዩኑስ ፥ 58).
°
♦️በዚህ አንቀጽላይ እዝነቱ ማለት ሙሐመድ - ﷺ - ናቸው እና በሳቸው እንደሰታለን። ይላሉ ፡ ለዚህ የሚሰጠው መልስ በሁለት መልኩ ነው ፦
°
🔻1ኛ. ቁርአኑ ላይ እዝነቱ የተባለው እንደአብዛኛዎቹ የተፍሲር ሊቃዎንቶች ገለፃ ቁርአን ወይም እስልምና ነው እንጂ ሙሐመድ - ﷺ - አይደሉም። እንደምሳሌ ተፍሲር አጥ-ጦበሪ , ቁርጡቢ , በገዊ, ኢብኑ-ከሲር, ተፍሲር አስ-ሰዕዲ እና ሌሎችንም መመልከት ይችላል።
°
♦️ቁርአን ወይም እስልምና ተብሎ ለመተርጎሙ ደግሞ ከበፊቱ ያለውን አንቀጽ ስንመለከት የበለጠ ግልፅ ይሆንልናል። አንቀጹ እንዲህ ይላል ፦
{ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ }
[| እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና #እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡ |] (ዩኑስ ፥ 57). ስለዚህ አንቀጹ እያወራ ያለው ስለቁርአን ነው ማለት ነው።
°
🔻2ኛ.እንደእነሱ አባባል ሙሐመድ - ﷺ - ናቸው ብንል ታዲያ ይሄ እንዴት ብሎ ነው በአመት አንድ ጊዜ የተወለዱበትን ቀን ጠብቃችሁ, ተሰባስባችሁ, ምግብ እያበላችሁ አክብሩት እና አሳልፉት ለማለት ማስረጃ የሚሆነው? የተወለዱበትን ቀን ብቻ ገድቦ አመት ጠብቆ መደሰት ከየት የመጣ ነው??
°
▪️#ሁለተኛ_ማምታቻ ፡ ነብዩ - ﷺ - ሰኞን ቀን ይፆሙ ነበር ፤ ለምን ሲባሉም [ የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ ] (ሙስሊም ፥ 1978).በማለት ተናግረዋል ፤ ስለዚህ እሳቸው የተወለዱበትን ቀን ስላላቁት እኛም በማክበር እናልቀዋለን የሚል ነው።
°
🔻ለዚህ የሚሰጠው መልስ ፡ ነብዩ - ﷺ - የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ ፆመዋለሁ ብለው ፆሙ እንጂ ሁልጊዜ አመት ከአመት እየተጠባበቁ, በዛ ጊዜም ምግብ እየበሉ ሰውንም እያበሉ አላሳለፉም የሚል ነው። እውነተኛ የነብዩ - ﷺ - ውዴታ ከሆነ እሳቸው የሰሩትን መስራት የተዉትን መተው ነውና እሳቸው ቀኑን ፁመውታል እናንተም መፆም አለባችሁ እንጂ ያንን ቀን ለይታችሁ አመት ከአመት እየተጠባበቃችሁ ማክበር ከየት የመጣ ነው?? እነሱ ፆም በመፆም ስላከበሩ እኛ ደግሞ መውሊድ በማውጣት እናከብረዋለን የሚለው አባባል ልክ የኡሱሉል ፊቅህ ሊቃውንቶች እንደሚሉት "قياس فاسد" ወይም የተበላሸ ማመሳሰል ነው። ምክንያቱም መፆም እና መብላት ተቃራኒ ነገሮች ስለሆኑ ማለት ነው።
°
♦️ከዚህ ውጭ የሚጠቅሷቸው ማምታቻዎች እዕምራዊ ማስረጃዎች ናቸው ከነሱም ውስጥ ፦
❇️1⃣.መውሊድን የምናከብረው ለአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ካለን ውዴታ ነው የሚል ነው.
°
🔻ይህን በሁለት መልኩ መመለስ እንችላለን ፦
የመጀመሪያው መልስ ፦ ነብዩን - ﷺ - መውደድ ማለት እሳቸው የሰሩት መስራት የተውትን መተው ነው እንጂ እሳቸው ያልሰሩትን እየሰሩ ወድጄያለሁ ማለት አያስኬድም። እንደውም ከውዴታ መገለጫ ምልክቶች ውስጥ እውነተኛው ምልክቱ ወዳጁ አካል ለሚወደው ወገን ተከታይ ሲሆን ነው ፤ አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - እንዲህ ይለናል፦
{ ﻗُﻞْ ﺇِﻥ ﻛُﻨﺘُﻢْ ﺗُﺤِﺒُّﻮﻥَ اﻟﻠَّﻪَ ﻓَﺎﺗَّﺒِﻌُﻮﻧِﻲ ﻳُﺤْﺒِﺒْﻜُﻢُ اﻟﻠَّﻪُ ﻭَﻳَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻜُﻢْ ﺫُﻧُﻮﺑَﻜُﻢْ ۗ ﻭَاﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭٌ ﺭَّﺣِﻴﻢٌ }
[| በላቸው ፦ «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» |] (አልኢምራን ፥ 31).
°
ይህ እውነተኛ ውዴታን መግለጫ ምልክት ከሆነ ፤ ነቢዩን - ﷺ - በዚህ ጉዳይ ላይ መከተል ማለት ይህንን ቢድዓ አለመስራት ማለት ነው። ምክንያቱም ይህ ተግባር የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ያለሰሩት ስለሆነ ማለት ነው።
°
🔻ሁለተኛው መልስ ፦ እናንተ ከኹለፋዎቹ እና ከሶሓባዎቹ የበለጠ ለነቢዩ - ﷺ - ውዴታ የላችሁም። ማንኛውም ሰው የአላህ መልእክተኛን - ﷺ - ከአቡበከር ፣ ከዑመር ፣ ከዑስማን ፣ ከዐሊይ ከሌሎችም ሶሓባዎች እና ታቢዒዮች በላይ እወዳለው ማለት አያስኬድም, የሚሆን ነገርም አይደለም ፤ እነዚህ ሁሉ ደግሞ አልሰሩትም ፤ ምክንያቱም እነሱ የሚፈልጉት ረሱል - ﷺ - የሰሩትን ነገር ሰርተው, የተዉትን ነገር ደግሞ ትተው ትክክለኛ ውዴታን ማስገኘት ስለሆነ ማለት ነው። ረሱል - ﷺ - የሰሩትን ስራ መስራት ሱና እንደሆነው ሁሉ #ለመስራት_የሚያስችል_ምክንያት_ኑሮ_ከልካይ_ነገር_ሳይኖር የተውትን ነገር መተውም ሱና ነው። ይህንን የተቃረነ ደግሞ ቢድዓ ይባላል።
°
❇️2⃣.መውሊድ ማክበር እኮ ምግብ ማብላት ነው ፤ ሰደቃ ደግሞ የተወደደ ተግባር ነው ከዚህ በተጨማሪ የሳቸውን ሲራ እንናገራለን , እናስተምራለን እና ይሄ እንዴት ክልክል ይሆናል? ይህ ሁሉ ስራ ተፈላጊ ተግባር አይደለምን? የሚል ማምታቻ ያቀርባሉ።
°
🔻ለዚህ የሚሰጠው መልስ ፡
አው! ሰዎችን ማብላት, ሰደቃ ማድረግ የተፈቀደ ተግባር ነው ፤ ነገር ግን ልክ በክፍል 3 ፅሑፋችን ላይ ለማንሳት እንደሞከርነው ነብዩ - ﷺ - በቦታ እና በጊዜ ያልደገቡትን አንድን የአምልኮ ዘርፍ ገድቦ መስራት ቢድዓ ይሆናል። እነዚህን ነገራቶች በቦታ እና በጊዜ መገደብ አይገባችሁም። በቦታ እና በጊዜ መገደባችሁ ይሄ ነው ቢድዓ ያስባለው ብለን መልስ እንሰጣቸዋለን።
°
♦️ስለዚህ ከላይ እንደተመለከትነው መውሊድ ማክበር ይቻላል የሚሉ ሰዎች የሚያመጧቸው ማምታቻዎች ውድቅ ናቸው። መውሊድም ቢድዓ መሆኑ ግልፅ ነው። ከዚህም ባለፈ መውሊድ ውስጥ ብዙ ሐራም ነገሮች ይፈፀማሉ ፤
ከነሱም ው