ዐቂዳህን ከቁርአንና ከሀዲስ ያዝ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan



Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


«خَيْرُكُمْ مَنْ تَعَلَّمَ الْقُرْآنَ وَعَلَّمَهُ» dan repost
ቁርአን ከሱረቱል ፋቲሃ መቅራት የምትፈልጉ እንዲሁም ቀዒደቱ ኑራንያ መቅራት የምትፈልጉ ውድ እህቶች በዚህ ሊንክ
المجموعة التجويد القرأنN1
https://t.me/tejweedtilawa ገብታቹ ከየት መጀመር እንደምትፈልጉ እየተናገራቹ ወደ ዋናው ግሩፕ ትገባላቹ
🌸ሴቶችን ብቻ ነው።


በኡስታዝ ሑሴን ዒሳ【حفظه الله تعالى】የቁርኣን ተፍሲር እና የኪታብ ደርሶች የሚተላለፍበት ቻናል💿🎙! dan repost
Aselamu alikum,
Alhamdulilah I'm excited to announce that Nesiha Da'wah Atlanta now has an app on Android Google play (Nesiha Atlanta) so that all the class that sheikh Hussain Isaa gives will be accessible inshallah at a tip of your finger at one place at any time. In this app you will be able to play, share, comment and get notified when the class is live. So I kindly ask everyone to download, comment and share to all your friends and family.
Barakllah fikum.

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.spreaker.custom.prod.app_59885

As for iOS(iPhone) it be available soon inshallah.


💎قدوتنا الصحابيات💎የምር ሱንይ ሴት ሁኚ! 💎ክብር ማለት ሱና ነው! ሱናህ የኑሕ መርከብ ናት፤የተሳፈረባት ይድናል።ወደ ኃላ የቀረ ይሰምጣል።«السلفية منهجي»💎 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
➧ተገላልጦ መሄድ ጥሩ አኽላቅን ኢማንን የሚያጠፋ ጀርም ነው!!

►ፀያፍ ተግባሮችና ፀያፍ ቃላቶች መሀበረሰቡ ውስጥ እንዲሰራጭ የሚያደርግ ነገር ነው። ፀያፍ ቃል፣ፀያፍ ተግባር አይን አውጣነት እንዲስፋፋ
የሚያደርጉ ኢብሊስና የእብሊስ ሰራዊቶች ናቸው። እነዚያ ያመኑ ሰዎች ዘንዳ ፀያፍ ተግባር እንዲስፋፋ የሚፈልጉ በአዱንያም በአኼራም አሰቃቂ ቅጣት ይጠብቃችዋል አላህ ያቃል እናንተ ግን አታቁም ይላል አላህ-ﷻ-እህቴ ሆይ አንቺ ተኳኩለሽ፣ተቀባብተሽ፣ሒጃብን ጥለሽ በምትሄጅበት ሰአት ፈሳድ መጥፎ ነገር እየተስፋፋ እንደሆነ እወቂ! የአላህ ቁጣ እንዲወርድ ሰበብ እየሆንሽ እንደሆነ እወቂ!!ወንዱ ከግራ ከቀኝ ስንት ፊትና እየተፈታተነው እያለ ውንድ አንቺ ሙስሊም ናት የምትባይዋ ሴት ሙስሊምነትሽን በከፊል የሚገልፅ አለባበስ ለብሰሽ ተኳኩለሽ ፣ተውበሽ፣ ሽቶ ተለቅልቀሽ ስተወጪ ሙስሊሙ ወንድምሽ አጠገብሽ ቁጭ ብሎ ምንድነው ሚያስበው???!! ውስጡ ላይ ምንድነው የሚመላለሰው???!! ሸር እንዲያስብ በር አትክፈቺ!ካፊሩ የጎተጎተውና ያስቸገረው አንሶ አንቺ በድምፅሽ በመቅለስለስሽ ሙስሊም ወንድምሽን ለጀሃነም አትዳርጊው!!ሸር እንዲያስብ አታድርጊው ሰው ነውና!! የራስሽ ወንጀል አንሶሽ ወንጀል ላይ ወንጀል አታታነባብሪ!!
እያለ ግሳፄዎን ጣፍጭ ምክሩን ……ቀጠለ ይከታተሉት ኡስታዙና {አላህ ይጠብቅህ}
【{وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَىٰ تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ}】 [سورة_الذاريات_ آية_55]
፞ •⊰✿🌹✿⊱• ፞
⚘••..¦ t.me/TewhidSunnah
ڪونـﮯغاليــة عفيفــة نقية






Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish




Haliya khdire ام يوسف dan repost
وصف الحور العين ..




የተለያዩ ግጥሞች ሚለቀቅበት ቻይናል dan repost
Audio from اشتقت لك ابي حبيبي


እህቶች ሆይ!!
በሚጥል በሽታ የተጠቃች አንዲት ታላቅ ሴት ነበረች — በነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘመን ።

ነብያችን ዘንድ በመቅረብ ያንገላታትን በሽታ በተመለከተ አላህን እንዲለምኑላት ጠየቀቻቸው ። መልእክተኛውም

إن شئت صبرت ولك الجنة وإن شئت دعوت الله أن يعافيك

" ከፈለግሽ ታገሺና ላንቺ ጀነት አለልሽ። ከፈለግሽ ደግሞ ጤና እንዲለግስሽ አላህን ልለምንሽ " አሏት ።
ይህቺ አኺራዋን ከዱንያዋ— ለዛውም አሳሳቢ ከሆነው ጤናዋ— ያስቀደመች ሴት በሽታዋን በተመለከተ
" እታገሳለሁ " አለች ።
ልብ በሉ እህቶች! ! "በበሽታው ምክንያት መውደቄን እታገሳለሁ" ነበር አባባሏ! — ይህንን ከባድ በሽታ እታጋሳለሁ ነበር ነገሯ ! !
ነገር ግን ልትታገሰው የከበዳት አንድ ጉዳይ ነበርና ነብዩን እንዲህ ስትል ጠየቀች ፣ " በምወድቅ (በሽታው በሚጥለኝ ግዜ) ሰውነቴ ይጋለጣልና አካሌ እንዳይራቆት አላህን ለምኑልኝ አለች ። አንዳንድ ዘገባዎች ላይ እንደተብራራው ይህቼ ሴት ከነብዩ ዱዓ በሇላ በሽታዋ ቢጥላትም ሰውነቷ በፍፁም አይጋለጥም ነበር— በነብዩ ዱዓ በረካ።
ይህች ታላቅ ሴት በበሽታዋ ምክኒያት መደበቅ ያለበት አካሏ ቢጋለጥ እንኳን ነገሩ በፈቃዷ የተከሰተ አይደለምና የምትጠየቅበት ወንጀል አይደለም ። ከዚህም ጋር ጉዳዩ ይህን ያህል አሳስቧት ነበር — አላህን መፍራት ማለት ይሄ ነው! ቀደምት ምርጦቻችንና ተምሳሌቶቻችን እንዲህ ነበሩ!!
ታዲያ ምን ነው?!.... አንዳንድ እህቶች በዳዕዋ ስም ተቀባብተው ለጅምላ እይታ መቅረባቸው? ! ምን ነው ታዲያ አንዳንድ እህቶች ተኳኩለውና መደበቅ ያለበትን አካል ገላልጠው አደባባይ መውጣታቸው? ! ኧረ አይበጅም እህቶች !! አላህን ፍሩ! ! ይሄ ገላ ከመፈራረሱ በፊት ይህንን ገላ ወደሰጣችሁ አላህ ተመለሱ! !


🔖 ሱረቱል ዐስር እና ሱረቱል ሁምዘህ

🎙 ሸይኽ ሙሐመድ አህመድ ዑመር አል ባሲጢይ

Http://t.me/albasity


🔊 ሙሐደራዎች ግብዣ 📀

⏯ ርዕስ ፦ ቁርኣን!

🎙 በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

⏰ርዝመት፦ 20:43 ደቂቃ

💾 መጠን 9.6 mb

🏳ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ

https://telegram.me/nesihastudio






📢 ለታዳጊ ወንዶች የተዘጋጀ ልዩ መሰረታዊ የዲን ትምህርት

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 አደባባይ) ልዩ መሰረታዊ የዲን ትምህርት ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ አደራ እንላለን።

﴿ِّإِنَّهُم فِتيَةٌ آمَنوا بِرَبِّهِم وَزِدناهُم هُدًى﴾ الكهف: ١٣

« እነሱ በጌታቸው ያመኑ ወጣቶች ናቸው። መመራትንም ጨመርንላቸው፡፡» ሱረቱል ከህፍ 13

👌በየሳምንቱ ቅዳሜ
☞ ከ8፡00–10፡00

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

Http://t.me/merkezuna


《وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ》

➣እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡
➣«ስለ_ተውሒድ»

ክፍል-①

🎙 #በኡስታዝ_አቡ_ሙስሊም
「【حفظه الله تعالى】」

         ↷⇣🔊⇣↶
t.me/AbumuslimAlarsi


ዐቂዳህን ከቁርአንና ከሀዲስ ያዝ:
ዐቂዳህን ከቁርአንና ከሀዲስ ያዝ:
عَنْ عُمَرَ  أَيْضًا قَالَ: " بَيْنَمَا نَحْنُ جُلُوسٌ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ، إذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعْرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ. حَتَّى جَلَسَ إلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم . فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إلَى رُكْبَتَيْهِ، وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخْذَيْهِ، وَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ أَخْبِرْنِي عَنْ الْإِسْلَامِ. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إنْ اسْتَطَعْت إلَيْهِ سَبِيلًا. قَالَ: صَدَقْت . فَعَجِبْنَا لَهُ يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ! قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ الْإِيمَانِ. قَالَ: أَنْ تُؤْمِنَ بِاَللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ. قَالَ: صَدَقْت. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ الْإِحْسَانِ. قَالَ: أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّك تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاك. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ السَّاعَةِ. قَالَ: مَا الْمَسْئُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنْ السَّائِلِ. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ أَمَارَاتِهَا؟ قَالَ: أَنْ تَلِدَ الْأَمَةُ رَبَّتَهَا، وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ الْعَالَةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبُنْيَانِ. ثُمَّ انْطَلَقَ، فَلَبِثْنَا مَلِيًّا، ثُمَّ قَالَ: يَا, أَتَدْرِي مَنْ السَّائِلُ؟. قَلَتْ: اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ. قَالَ: فَإِنَّهُ جِبْرِيلُ أَتَاكُمْ يُعَلِّمُكُمْ دِينَكُمْ ". رَوَاهُ مُسْلِمٌ [رقم:8] .



የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ እንዲህ አለ። “የሆነ ቀን ከአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀምጠን እያለ፡ በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው፥ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ፥ የመንገደኛ ምልክት የማይታይበት፥ ከኛ ውስጥም ማንም የማያውቀው ሰውዬ ብቅ አለና እነብዩ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀመጠ። ጉልበቱን ከጉልበታቸው ጋር አገጣጠመ፥ መዳፉንም ታፋው ላይ አስቀመጠ። ከዛም አንተ ሙሓመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ኢስላም ማለት ፦ በእውነት የሚመለክ ጌታ አንድ አላህ ብቻ ነው ብሎ እና ሙሓመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሶላትን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስገድ፣ ዘካን ማውጣት፣ ረመዳንን መጾም፣ የአላህ ቤትን ከቻልን መጎብኘት።” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ዑመርም እንዲህ አለ “በሱ ተገረምን! እሳቸውን ይጠይቃል መልሶ እውነት ተናገርክ ይላቸዋል!” ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢማን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢማን ማለት ፦ በአላህ ማመን፣ በመላኢኮች ማመን፣ በመጻህፍት ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፣ በአላህ ውሳኔ ከፋም በጀም ማመን” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢሕሳን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢሕሳን ማለት አላህን እንደምታየው አድርገህ ልታመልከው ነው፥ አንተ ባታየውም እሱ ያየሃል እና።” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ሰአቷን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ የሚያውቅ አይደለም” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ምልክቶቿን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ባርያ ጌታዋን ልትወልድ ነው፣ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ፥ እርቃናቸውን የነበሩ፥ ድሆች የነበሩ የፍየል ጠባቂዎች ህንጻ ለመስራት ሲሽቀዳደሙ ልታይ ነው።” ከዛ ቡሃላ ሰውየው ሄደና ብዙ ቆየን። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “አንተ ዑመር ሆይ!ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?” ዑመርም “አላህና መልእክተኛው ያወቁ ናቸው።” በማለት መለሰ። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ የመጣው እኮ ጂብሪል ነው፥ ሃይማኖታቹህን ሊያስተምራቹህ መጣቹህ።” ሓዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።ዐቂዳህን ከቁርአንና ከሀዲስ ያዝ
https://t.me/Aqidahin


ስጥ ፦ 1.ነብዩን - ﷺ - ከልክ በላይ በማወደስ አላህ የማይምረው የሺርክ ወንጀል ውስጥ መዘፈቅን ያስከትላል
2.ሴት እና ወንድ መደባለቅ "ኢኽቲላጥ" ይገኝበታል
3.ጭፈራ እና ጩሐት ይገኝበታል። ከዚህም ሌላ ሐራም ነገራቶች በውስጡ ይሰራሉ።
°
♦️በመጨረሻም በዲናችን ላይ የሚከበሩት በዓላቶች ሁለት አመታዊ በዓላቶች (ዒደል ፈጥር እና ዒደል አድሓ) እና አንድ ሳምንታዊ ጁሙዓ ዒድ ናቸው። ከነዚህ ውጭ ሌላ ዒድ የለንም።
__
▪️ክፍል 1ን ለማንበብ ፡ https://goo.gl/PqJcEc
▫️ክፍል 2ን ለማንበብ ፡ https://goo.gl/7c6Bxe
▪️ክፍል 3ን ለማንበብ ፡ https://goo.gl/L4Giye
▫️ክፍል 4ን ለማንበብ ፡ https://goo.gl/t6S3jP
▪️ክፍል 5ን ለማንበብ ፡ https://goo.gl/ftSDDm
____
©ዲን መመካከር ነው
____
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ  @ Ibn yahya Ahmed 
📆እሮብ ሶፈር 29/1440ሂ. # ጥቅምት 28/2011. ላይ የተፃፈ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦ https://telegram.me/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777
🛑የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ ፦ https://goo.gl/Ext9jr


#ቢድዓ_ሁሉ_ጥሜት_ነው
🚩ተከታታይ ፅሑፍ ክፍል ፡ 6⃣
🏴ንዑስ ርእስ ፦ መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች የሚያመጧቸው ብዥታዎች ላይ የሚሰጥ መልስ
__
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው.
°
♦️እስካሁን በነበሩት 5 ተከታታይ ፅሑፎች ላይ ቢድዓ ማለት ቁርአናዊም ሆነ ሐዲሳዊ እንደዚሁም እንደኢጅማዕ ያሉ ትክክለኛ ማስረጃዎች የማይደግፉት ለዲን ተብሎ የሚሰራ ተግባር ወይም እምነት መሆኑን ተረድተናል ፤ ቢድዓ ሁሉም ጥሜት መሆኑን ከሐዲስ እና ከሰለፎች ንግግርም ለማየት ሞክረናል። እንደዚሁ ያልተገደቡ የአምልኮ ዘርፎችን መገደብ , የተገደቡ የአምልኮ ዘርፎችን ደግሞ ገደባቸውን ማንሳትም ቢድዓ እንደሚሆን ተመልክተናል። በተጨማሪም ቢድዓ ሁሉም ጥሜት አይደለም የሚሉ ሰዎች የሚያመጧቸውን ዋና ዋና ማምታቻዎች በመጥቀስ መልስ ሰጥተናል። ዛሬ በአላህ ፍቃድ መውሊድ አክባሪዎች የሚያነሷቸው ብዥታዎች ላይ የሚሰጡ ምላሾችን ተመልክተን ፅሑፋችንን እናሳርጋለን።
°
♦️መውሊድን ለማክበር በዋናነት የሚጠቅሱት ነገር በዲን ውስጥ መልካም ቢድዓ መፍጠር ይቻላል ብለው በክፍል 4 እና 5 ላይ የተመለከትናቸውን ማምታቻዎች ነው። እነዚህ ማምታቻዎች ደግሞ አዲስ ቢድዓ መፍጠር እንደማያስችላቸው መልስ ሰጥተንበት አልፈናል። ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱትን ነገር እንመልከት ፡

▪️#የመጀመሪያ_ማምታቻ ፡ ተከታዩ የቁርአን አንቀፅ ነው ፦

{ قُلْ بِفَضْلِ اللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ }

[| «በአላህ ችሮታና #በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡ |] (ዩኑስ ፥ 58).
°
♦️በዚህ አንቀጽላይ እዝነቱ ማለት ሙሐመድ - ﷺ - ናቸው እና በሳቸው እንደሰታለን። ይላሉ ፡ ለዚህ የሚሰጠው መልስ በሁለት መልኩ ነው ፦
°
🔻1ኛ. ቁርአኑ ላይ እዝነቱ የተባለው እንደአብዛኛዎቹ የተፍሲር ሊቃዎንቶች ገለፃ ቁርአን ወይም እስልምና ነው እንጂ ሙሐመድ - ﷺ - አይደሉም። እንደምሳሌ ተፍሲር አጥ-ጦበሪ , ቁርጡቢ , በገዊ, ኢብኑ-ከሲር, ተፍሲር አስ-ሰዕዲ እና ሌሎችንም መመልከት ይችላል።
°
♦️ቁርአን ወይም እስልምና ተብሎ ለመተርጎሙ ደግሞ ከበፊቱ ያለውን አንቀጽ ስንመለከት የበለጠ ግልፅ ይሆንልናል። አንቀጹ እንዲህ ይላል ፦

{ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ }

[| እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና #እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡ |] (ዩኑስ ፥ 57). ስለዚህ አንቀጹ እያወራ ያለው ስለቁርአን ነው ማለት ነው።
°
🔻2ኛ.እንደእነሱ አባባል ሙሐመድ - ﷺ - ናቸው ብንል ታዲያ ይሄ እንዴት ብሎ ነው በአመት አንድ ጊዜ የተወለዱበትን ቀን ጠብቃችሁ, ተሰባስባችሁ, ምግብ እያበላችሁ አክብሩት እና አሳልፉት ለማለት ማስረጃ የሚሆነው? የተወለዱበትን ቀን ብቻ ገድቦ አመት ጠብቆ መደሰት ከየት የመጣ ነው??
°
▪️#ሁለተኛ_ማምታቻ ፡ ነብዩ - ﷺ - ሰኞን ቀን ይፆሙ ነበር ፤ ለምን ሲባሉም [ የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ ] (ሙስሊም ፥ 1978).በማለት ተናግረዋል ፤ ስለዚህ እሳቸው የተወለዱበትን ቀን ስላላቁት እኛም በማክበር እናልቀዋለን የሚል ነው።
°
🔻ለዚህ የሚሰጠው መልስ ፡ ነብዩ - ﷺ - የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ ፆመዋለሁ ብለው ፆሙ እንጂ ሁልጊዜ አመት ከአመት እየተጠባበቁ, በዛ ጊዜም ምግብ እየበሉ ሰውንም እያበሉ አላሳለፉም የሚል ነው። እውነተኛ የነብዩ - ﷺ - ውዴታ ከሆነ እሳቸው የሰሩትን መስራት የተዉትን መተው ነውና እሳቸው ቀኑን ፁመውታል እናንተም መፆም አለባችሁ እንጂ ያንን ቀን ለይታችሁ አመት ከአመት እየተጠባበቃችሁ ማክበር ከየት የመጣ ነው?? እነሱ ፆም በመፆም ስላከበሩ እኛ ደግሞ መውሊድ በማውጣት እናከብረዋለን የሚለው አባባል ልክ የኡሱሉል ፊቅህ ሊቃውንቶች እንደሚሉት "قياس فاسد" ወይም የተበላሸ ማመሳሰል ነው። ምክንያቱም መፆም እና መብላት ተቃራኒ ነገሮች ስለሆኑ ማለት ነው።
°
♦️ከዚህ ውጭ የሚጠቅሷቸው ማምታቻዎች እዕምራዊ ማስረጃዎች ናቸው ከነሱም ውስጥ ፦

❇️1⃣.መውሊድን የምናከብረው ለአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ካለን ውዴታ ነው የሚል ነው.
°
🔻ይህን በሁለት መልኩ መመለስ እንችላለን ፦
የመጀመሪያው መልስ ፦ ነብዩን - ﷺ - መውደድ ማለት እሳቸው የሰሩት መስራት የተውትን መተው ነው እንጂ እሳቸው ያልሰሩትን እየሰሩ ወድጄያለሁ ማለት አያስኬድም። እንደውም ከውዴታ መገለጫ ምልክቶች ውስጥ እውነተኛው ምልክቱ ወዳጁ አካል ለሚወደው ወገን ተከታይ ሲሆን ነው ፤ አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - እንዲህ ይለናል፦

{ ﻗُﻞْ ﺇِﻥ ﻛُﻨﺘُﻢْ ﺗُﺤِﺒُّﻮﻥَ اﻟﻠَّﻪَ ﻓَﺎﺗَّﺒِﻌُﻮﻧِﻲ ﻳُﺤْﺒِﺒْﻜُﻢُ اﻟﻠَّﻪُ ﻭَﻳَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻜُﻢْ ﺫُﻧُﻮﺑَﻜُﻢْ ۗ ﻭَاﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭٌ ﺭَّﺣِﻴﻢٌ }

[| በላቸው ፦ «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» |] (አልኢምራን ፥ 31).
°
ይህ እውነተኛ ውዴታን መግለጫ ምልክት ከሆነ ፤ ነቢዩን - ﷺ - በዚህ ጉዳይ ላይ መከተል ማለት ይህንን ቢድዓ አለመስራት ማለት ነው። ምክንያቱም ይህ ተግባር የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ያለሰሩት ስለሆነ ማለት ነው።
°
🔻ሁለተኛው መልስ ፦ እናንተ ከኹለፋዎቹ እና ከሶሓባዎቹ የበለጠ ለነቢዩ - ﷺ - ውዴታ የላችሁም። ማንኛውም ሰው የአላህ መልእክተኛን - ﷺ - ከአቡበከር ፣ ከዑመር ፣ ከዑስማን ፣ ከዐሊይ ከሌሎችም ሶሓባዎች እና ታቢዒዮች በላይ እወዳለው ማለት አያስኬድም, የሚሆን ነገርም አይደለም ፤ እነዚህ ሁሉ ደግሞ አልሰሩትም ፤ ምክንያቱም እነሱ የሚፈልጉት ረሱል - ﷺ - የሰሩትን ነገር ሰርተው, የተዉትን ነገር ደግሞ ትተው ትክክለኛ ውዴታን ማስገኘት ስለሆነ ማለት ነው። ረሱል - ﷺ - የሰሩትን ስራ መስራት ሱና እንደሆነው ሁሉ #ለመስራት_የሚያስችል_ምክንያት_ኑሮ_ከልካይ_ነገር_ሳይኖር የተውትን ነገር መተውም ሱና ነው። ይህንን የተቃረነ ደግሞ ቢድዓ ይባላል።
°
❇️2⃣.መውሊድ ማክበር እኮ ምግብ ማብላት ነው ፤ ሰደቃ ደግሞ የተወደደ ተግባር ነው ከዚህ በተጨማሪ የሳቸውን ሲራ እንናገራለን , እናስተምራለን እና ይሄ እንዴት ክልክል ይሆናል? ይህ ሁሉ ስራ ተፈላጊ ተግባር አይደለምን? የሚል ማምታቻ ያቀርባሉ።
°
🔻ለዚህ የሚሰጠው መልስ ፡
አው! ሰዎችን ማብላት, ሰደቃ ማድረግ የተፈቀደ ተግባር ነው ፤ ነገር ግን ልክ በክፍል 3 ፅሑፋችን ላይ ለማንሳት እንደሞከርነው ነብዩ - ﷺ - በቦታ እና በጊዜ ያልደገቡትን አንድን የአምልኮ ዘርፍ ገድቦ መስራት ቢድዓ ይሆናል። እነዚህን ነገራቶች በቦታ እና በጊዜ መገደብ አይገባችሁም። በቦታ እና በጊዜ መገደባችሁ ይሄ ነው ቢድዓ ያስባለው ብለን መልስ እንሰጣቸዋለን።
°
♦️ስለዚህ ከላይ እንደተመለከትነው መውሊድ ማክበር ይቻላል የሚሉ ሰዎች የሚያመጧቸው ማምታቻዎች ውድቅ ናቸው። መውሊድም ቢድዓ መሆኑ ግልፅ ነው። ከዚህም ባለፈ መውሊድ ውስጥ ብዙ ሐራም ነገሮች ይፈፀማሉ ፤
ከነሱም ው

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

144

obunachilar
Kanal statistikasi