ጥር 25 ቀን 2017ዓ.ም
ማስታወሻ
ለተማሪዎች በሙሉ፤
የመጀመሪያው ሴሚስተር ማጠቃለያ የፈተና ወረቀት ለተማሪዎች የሚመለሰው ሰኞ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በጠዋቱ ፈረቃ ብቻ መሆኑን ቀደም ሲል ገልጸንላችኋል።
በዚሁ መሠረት ሁላችሁም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያላችሁ ተማሪዎች ነገ በጠዋት በየመማሪያ ክፍላችሁ ተገኝታችሁ የፈተና ወረቀታችሁን ከመምህራን እንድትቀበሉ፤ የእርማት ወይም ሌሎች ችግሮች ካሉ በዕለቱ ብቻ እንድታስተካክሉ እና በሁሉም የትምህርት አይነቶች ያላችሁን የተሟላ ውጤታችሁን ማወቅ የሚገባችሁ መሆኑን እንገልጻለን።
ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ስትመጡ የተማሪ የደንብ ልብስ (Uniform) እና መታወቂያ አሟልቶ መምጣት ያስፈልጋል።
ት/ቤቱ