Commercial Bank of Ethiopia - Official dan repost
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል የባንክ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
****************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመንግስት ባለቤትነት ከሚተዳደሩ የልማት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂዷል፡፡
የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ተደራሽነት እና የዲጂታል ባንክ አገልግሎት አቅርቦትን ጋር ተያይዞ ላነሱዋቸው ጥያቄዎች የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኢትጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሀገሪቱ ስለሚሰጠው የቅርንጫፍ የባንክ አገልግሎትን ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቅርንጫፍ እና ሪቴይል የባንክ አገልግሎት ኤክስኪውቲቭ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ደረጀ ፉፋ ፦ ባንኩ ደንበኞች ወደ ቅርንጫፍ መሄድን ሳይጠበቅባቸው፤ ባሉበት ሆነው በዲጂታል የባንክ አገልግሎት እንዲገለገሉ ፤ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
የባንኩን የወደፊት የትኩረት አቅጣጫን ያስረዱት አቶ ደረጀ፦ በከተሞች ዲጂታል ባንክን አገልግሎት እያስፋፋን፤ የባንክ አገልግሎትን ተደራሽ ባልሆነባቸው የገጠር መንደሮች ቅርንጫፍ እየከፈትን ፤ በከተማ ደግሞ የተደራረቡ እና አዋጭ ያልሆኑ ቅርንጫፎችን በማዋሀድ ፤ የዲጂታል የባንክ አገልግሎትን አጠናክረን እንሰጣለን ብለዋል፡፡
የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች በውይይት ላይ ባንኩ የግብርናውን ዘርፍ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ለማገዝ ምን እየሠራ ይገኛል ብለው ላነሱት ጥያቄ፤ የባንኩ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወጋየሁ ገብረማርያም በሰጡት ማብራሪያ፦ ባንኩ የማዳበሪያ ግዥና ሽያጭን በዲጂታል መተግበሪያ የታገዘ በማድረጉ ከፈተኛ ገንዘብ በዲጂታል ሥርዓት እንዲዘዋወር አድርጓል፡፡ ከግብርና ጋር የተያዙ አዳዲስ መተግበሪያዎችን በቅርቡ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡
ባንኩ የዲጂታል የባንክ አገልግሎትን ለማስፋፋት ቁርጠኛ ነው ያሉት አቶ ወጋየሁ፦ የዲጂታል መተግበሪያ ከሚያበለጹጉ ፊንቴኮች ጋር በመሆን ፤ልዩ ልዩ መተግበሪያዎችን እየሠራ ነው፡፡ የመንግስት የልማት ተቋማትም የፋይናንስ ሥርዓታቸውን እንዲያዘምኑ ፤ ከባንኩ ጋር የተናበበ አሠራር ለመፍጠር እንዲቻል፤ በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ተደራሽትን አስመልክቶ ለተነሳው ጥያቄ የባንኩ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አማረ አሰፋ በሰጡት ማብራሪያ፦ ባንኩ የኢንተርኔት አገልግሎት በሌለባቸው ቦታዎች ሁሉ ለሚገኙ ማኅበረሰብ ፤ገንዘብ በቀላሉ ማዘዋወር፣መክፈል የሚያስችለውን የሲቢኢ ብር መተግበሪያን በማዘጋጀት የፋይናስ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን መሥራቱን አብራርተዋል፡፡
የመንግስት ልማት ድርጅቶች በየዕለቱ የሚፈጹሙትን የፋይናንስ እንቅስቃሴ ባሉበት ቦታ ሆነው የኢንተርኔት ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን፤ የፋይናንስ እንቅስቃሳቸውን እንዲያቀላጠፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡
#cbe #Ethiopia #EIH #Cusomer #commercialbankofethiopia