የለውጥ ፍርሃት (Metathesiophobia)
ሰው በተፈጥሮው አንድ አይነት ዑደትን የመውደድ ባህሪይ አለው፡፡ ጠዋት ጸሐይ ትወጣለች፣ ማታ ደግሞ ትጠልቃለች፣ በአመት አንዴ የዝናብ ወቅት ይመጣል ከዚያም ይሄዳል … አንድ አይነትነት!
እነዚህ የለመድናቸው ሁኔታዎች ለወጥ ሲሉ ግር ይለናል፡፡ ይህ ስሜት ደግሞ በትክክለኛው መጠን መኖሩ የጤናማነት ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ለውጥን ፈጽሞ የማንፈልግ ከሆነ የ“ፎቢያ” ችግር ሊኖርብህ ይችላል፡፡
የለውጥ “ፎቢያ”የአንድን ሰው የመኖር ጉጉት የሚሰርቅ የፍርሃት አይነት ነው፡፡ የዚህ ፍርሃት ተጠቂዎች በኑሮ ደረጃቸው፣ በእውቀት አለማቸው፣ በንግዱና በስራ መስካቸውም ሆነ የሚኖሩበትን ስፍራና ሁኔታ አስመልክቶ ምንም አይነት ለውጥ የማድረግ ፍላጎቱም የላቸው፤ ከመጣም ለውጡን አጥብቀው ይቋቋሙታል፡፡
በአጭሩ ምንም አይነት ነገር ከቁጥጥራቸው ውጪ እንዲሆን ስለማይፈልጉና ለውጥ ደግሞ ያንን ሁኔታ እንደሚፈጥርባቸው በማሰብ ስለሚፈሩ ባሉበት ሁኔታ ኖሮ ማለፍን ይመርጣሉ፡፡
ዙሪያችን ተለውጦ ሳለ አለመለወጥ፣ የእድገት እድል እያለ እንኳን መኖሪያን፣ ስራንና የንግድ ዘርፍን መቀየር መፍራት፣ ለማደግ አለመፈለግና የመሳሰሉት ጠንቆች የዚህ ፍርሃት ሰለባዎች ችግር ናቸው፡፡
ለማስታወስ ያህል …
• ለውጥን በጥንቃቄ አይን ማየትህ ትክክለኛ የለውጥ ምላሽ መሆኑን አስታውስ፡፡
• ወደድክም ጠላህም ለውጥ የሕይወትህ አካል መሆኑን አምነህ ተቀበለው፡፡
• አንተ የለውጥ እርምጃ ወሰድምክ አልወሰድክ፣ ለውጥ መምጣቱ አይቀርም፡፡
• ለውጥ በራሱ ሲመጣም ሆነ፣ ለውጥ በአንተ አነሳሽነት ሲከናወን ከለውጡ ጋር አብረህ መራመድ ለስኬታማነትህ ወሳኝ ነው፡፡
• ከለውጥ ጋር የሚመጣ የማይመች ስሜት ጤናማ፣ ትክክለኛና ሁሉም ሰው የሚጋራው ስሜት መሆኑን አትርሳ፡፡
ራእያችሁን ማወቅና ያንን መከተል ነባሩን አሰልቺ ሂደት በመቀየር ወደ አዲስ ለውጥ የሚያሸጋግር አስገራሚ ልምምድ ነው፡፡
👉 🙏🏽☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 @superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/@superboostup