አራቱ ተግባቦቶች
***
ከሰዎች ጋር ዕለት ተዕለት በሚኖረን ግንኙነት ወቅት የሚኖሩንን የተግባቦት አይነቶችን በአራት ከፍለን ማየት እንችላለን::
1- Aggressive (ቁጡ/ሃይለኝነት ያጠላበት):- እነዚህ ሰዎች ሃሳባቸውን በሃይለ ቃል እና በስሜታዊነት በመግለጽ ይታወቃሉ:: ሲያወሩ ጠረጴዛ እየደበደቡ፣ ደምስራቸው ተገታትሮ፣ በከፍተኛ የንዴት ስሜት ውስጥ ሁነው፣ ቡጢ ጨብጠው ነው::
የራሳቸውን ሃሳብ ሌሎችን በሚጎዳ መልኩ መግለጻቸው ችግር ይፈጥራል::
የቀድሞ የኢሰፖ መሪ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማሪያምን ንግግሮችን በዋቢነት መጥቀስ ይቻል ይሆን? 😊
2- Passive:- ሁሉን በጸጋ የሚቀበሉ፣ ሽቁጥቁጥ፣ ሃሳባቸውን ለመግለጽ ፈራ ተባ የሚሉ አይነት ናቸው:: እነዚህ ሰዎች ችግር ቢከሰት ባይከሰት የማይደንቃቸው ፣ ለስሜታዊነት ሩቅ የሆኑ፣ ነገር በሩቅ የሚሸሹ ናቸው:: የራሳቸውን ጥቅም ለሌሎች በማሳለፋቸው ምክንያት ለብዝበዛ ሊጋለጡ ይችላሉ::
3- Passive-Aggressive:- እነዚህ ሰዎች የታመቀ ሃይለኝነት ቢኖራቸውም ሃሳብ አስተያየታቸውን ፊት ለፊት ለማቅረብ ይፈራሉ:: ይልቁንስ ብስጭት እና ቅሬታቸውን በህቡዕ መፈጸም ይቀናቸዋል:: ማለትም ስም በማጥፋት፣ ስራን በማበላሸት፣ በመልገም እና በመሳሰሉት ንዴታቸውን ሲገልጹ ይስተዋላሉ:: እነዚህ ሰዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች አደገኞች ናቸው::
4- Assertive:- ሃሳብ አስተያየታቸውን ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ በቀጥታ መግለጽን የተካኑ ናቸው:: እነዚህ አይነት ሰዎች የሚፈጠሩ ቅራኔዎችን በጥበብ መፍታትን መለያቸው ነው:: በዚህም መሰረት ሁለቱንም ወገን የሚጠቅም መፍትሄ ላይ ይደርሳሉ::
እናንተስ ከሰዎች ጋር ስታወሩ ፣ ስታወጉ ፣ ስትወያዩ አልያም ስትከራከሩ የትኛውን አይነት ተግባቦት ትጠቀማላችሁ?
አሻም አሻም!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
@Biblicalmarriage