#ድንግልናሽን_ካልሰጠሽኝ_እጣላሻለሁ (Repost)
አንድ ማርታ(የተቀየረ ስም) የምትባል ልጅ ነበረች። እድሜዋ 20 ሲሆን 2ኛ አመት የምህንድስና ተማሪና የተማሪዎች ህብረት መሪ ነች።ዳንኤል(የተቀየረ ስም) ከሚባል ልጅ ጋር ከተዋወቀች 1 ዓመት ከ 2 ወራት አልፏል! በነዚህ ጊዜያት ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው እንክብካቤ ያሳያታል እሷም በጣም ትወደዋለች! ታምነዋለች። ሁልጊዜ መንፈሳዊ ነገር ያስተምራታል። ይህ ልጅ ለእሷ የሚያስብና የሚሳሳ ሰው ነው። ያስጠናታል። እሷም በነዚህ ጊዜያት ባየችው ፍቅርና እንክብካቤ ተማርካ ሙሉ ልቧን ሰጥታዋለች!ከባለታሪካችን ጋር ቆይታ እናድርግ...."ይህማ የወደፊት ባሌ ነው ብዬ አስብ ነበር" ትላለች ባለታሪኳ! "ነገር ግን ይህንን ፍቅርና እንክብካቤ ማጣጣም በጀመርኩበት ወቅት ዳኒ እጅጉን ነጭናጫና ብስጩ ሆነ። ቃሎቹም እኔን እየከበዱኝ ይመጡ ጀመር። እኔ ግን ከሱ ውጭ ማሰብ አልቻልኩኝም! ትምህርቴንም በተወሰነ መልኩ ችላ አልኩኝ። ዳኒ ምን ሆኗል ብዬ ማሰብ ሆነ ስራዬ። ዳኒ ጓደኞቹም ላይ ተቀይሯል!" እያለች ታሪኳን ትቀጥላለች።በዚህ መሃል ነበር እንባዋል መቆጣጠር አቅቷት አይኗ በእምባ ተሞላ። እኔም ታሪኩን እንድትጨርስ አደረኳት ታሪኩም እንዲህ ይቀጥላል..." ዳኒ 'ዛሬ በጣም እፈልግሻለሁ' ብሎ Text አደረገልኝ። እኔም ላለፈው ሳምንት ድምፁንም ስላልሰማሁ በአካልም ስላላገኘሁት ከግቢ ውጭ ወደ ቀጠረኝ ካፌ በፍጥነት ሄድኩኝ። ዳኒም ሰላም ካለኝ ካለኝ በኋላ ቀጥሎ 'አንቺ ግን ትወጂኛለሽ?' የሚል ጥያቄ ነበር የጠየቀኝ።እኔም ውስጤን ስለማውቀው ለእርሱ ያለኝን ከፍተኛ ፍቅር እንባ እየተናነቀኝ ነገርኩት። እርሱም 'ዛሬ ግቢ አንገባም ውጭ ነው የምናድረው!' ሲለኝ ይህ እንደማይሆን አጥብቄ ብነግረውም ይባስ ይጮህብኝ ጀመር እኔም በፍቅር ለምን ውጭ እንደማናድር ደጋግሜ ብነግረውም ጭራሽ ተቆጥቶኝ ጥሎኝ ሄደ። እንደዛ ይሳሳልኝ የነበረው ዳኒ ምን ሆኗል ብሎ ማሰብ ሆነ ስራዬ።" በማለት ምሬትም ንዴትም ጭንቀትም በሞላበት ስሜት ሃሳቧን ቀጠለች።"ጓደኞቼም 'ዳኒ የሆነ ነገር ሳይሆን አይቀርም!' ሲሉኝ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ የማወቅ ጉጉቴ የበለጥ ጨመረ። እንደወትሮዬም ከዚህ በፊት አብረን የምንቀመጥበትና የምንገናኝበት ቦታ እሱን ፍለጋ ስሄድ ያየሁትን ነገር ማመን አቃተኝ።ደነገጥኩኝ! ከዛ በኋላ የሆንኩትን ነገር አላውቅም። ከ30 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ስነቃ ራሴን ያገኘሁት ሆስፒታል አልጋ ላይ ነበር። 'ማርቲዬ አይዞሽ እኔን..ምክንያቱ እኔ ነኝ' የሚል ድምፅ ሰማሁኝ። ይህን ድምፅ በደንብ አውቀዋለሁኝ። የራሴ የልብ ጓደኛዬ የሆነችው ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ አብረን የተማርን እንደ እህቴ የማያት ጓደኛዬ ነበረች። ይህንን ድምፅ ስሰማ ይባስ ተበሳጨሁ ተናደድኩኝ ተለዋወጥኩኝ። 'አንቺ ነሻ የኔ የምለውን ዳኒን የቀየርሽብኝ። እያመንኩሽ ጉድ የሰራሽኝ ከሃዲ' ብዬ መጮህ ጀመርኩኝ። ዳኒን ፍለጋ ስሄድ እዛ ቦታ ያየሁት ሲሳሳሙ ነበር።ከዚህ በኋላ አይንሽን ማየት አልፈልግም ብዬ ከዛ ሆስፒታል ብቻዬን ወደ ግቢ ሄድኩኝ። አሁንም ግን ዳኒን ይፈልጋል ልቤ። አሁን ባየሁትና እሱ እየሆነ ያለው ነገር ትላንትን ሊሸፍንብኝ አልቻለም። ድንገት የእጅ ስልኬ ላይ Text ገባ። ክፍቼ ሳነበው 'እባክሽ ሚስጥር ለንገርሽ ስለምፈልግ ማታ 12 ሰዓት ላይ ግቢ ፊት ለፊት ያለው ካፌ እንገናኝ' ይላል። እቺ ልጅ ጉድ የሰራችኝ ጓደኛዬ ጓደኛ ናት። ይህንንማ ማወቅ አለብኝ ብላ ቀጠለች። ሰዓቱን መጠበቅ ስላልቻልኩኝ እባክሽ ከቻልሽ አሁን እንገናኝ ብዬ ላኩላት። 'የኔ እህት አሁን Class ሳላለኝ 10 ሰዓት ላይ እንገናኝ'ብላ መለሰችልኝ። 10 ስዓት ላይ ይችን ልጅ አገኘዋት። የምትነግረኝን ለማንም እንዳትናገር ቃል አስገብታኝ ሁኔታውን ትነግረኝ ጀመር። ' ያንቺና የዳኒ ፍቅር የግቢ ተማሪ ሁሉ የሚያውቀውና የሚቀናበት እንደሆነ አውቃለሁ። ኤልሳ ዳኒን ስለምትፈልገው ማርታ ከሌላ ወንድ ጋር ሆቴል ገብታ አድራለች ከዛም ድንግል ነኝ ብላ የምትዋሽህም ውሸቷን ነው ብላ ስለነገርችው ነው ዳኒ አንቺ ላይ የተቀየረው።' ብላኝ 'ከዚህ በላይ መቆየት አልችልም ብላኝ ሌላ የአዕምሮ ስራ ሰጥታኝ ትታኝ ሄደች።ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ። እኔ'ኮ አይደለም ከሌላ ወንድ ጋር ልተኛ ይቅርና ሌላ ወንድ ሊያቅፈኝ ሲሞክር እንኳን የምጣላ ሴት ነኝ። ሳላገባ አይደለም ድምግልናዬ ከንፈሬን እንኳን አላስነካም ብዬ ለራሴም ለእናቴም ጋር ቃል ገብቻለሁ።" በትካዜ ጭልጥ ብላ ሄደች ንግግሯም ለተወሰኑ ሰከንዶች ተቋረጠ። "ዳኒ አያምነኝም ነበር ማለት ነው። እንዴት ከእኔ ሌላ ሰው አመነ። ብለየው እንኳን እውነቱን ነግሬው መሆን አለበት ብዬ ስላመንኩኝ ደውዬለት ላገኘው እንደምፈልግ ነግሬው በቀጠሮውም ሰዓት ወደምንገናኝበት ቦታ አመራው። እሱም ቀድሞኝ ተገኝቷል።ሰኣት አክባሪነቱን እወድለታለሁ።ነገር ግን ሳየው የተደበላለቀ ስሜት ተፈጠረብኝ። ንዴት ፍቅር ናፍቆት ጥላቻ...ብዙ ብዙ። ተጨባብጠን ተቀመጥን። ስለ እኔ ማንነት ከመጀመሪያው ጀምሮ ከነገርኩት በኋላ አስደንጋጭ ቃል ከአንደበቱ አወጣ። 'አሁንም ትዋሻለሽ እኔ'ኮ ከራሴ ይልቅ ነበር ያመንኩሽም የወደድኩሽም። አንቺ ግን አሁንም ድንግል ነኝ ስትዪ አታፍሪም? ውሸታም ነሽ' ብሎኝ ከደብተሩ ውስጥ አንድ ፎቶ አውጥቶ አሳየኝ። ደነገጥኩኝ...እኔ ነኝ ፎቶው ላይ ያለሁት። የሆነ ወንድ እኔን ሲስመኝ የሚያሳይ። ከሆነ ወንድ ጋር ተቀምጬ የሚያሳይ። ይህ ወንድ ደግሞ ግቢ ውስጥ እኔን የሚፈልገኝና ከዚህ በፊት ከዳኒ ጋር የተጣለ ልጅ ነው። አዕምሮዬ ማሰብ እንዲሁም ይህ መች እንደሆነ ሊያውቅ አቃተው። ዳኒም ጥሎኝ ሄደ።
@Biblicalmarriage
እኔና ፎቶው ተፋጠጥ። እኔ ነኝ ልጁም እራሱ ነው። ነገር ግን ይህንን ነገር አላደረኩትም። ከዚህም ልጅ ጋር እንዲህ ባለ አስነዋሪ ድርጊት የትም አልተገናኘንም። ዞረብኝ። መሳቅ ጀመርኩኝ። ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ በሚያሳምን ሁኔታ በPhotoshop የተሰራ ፎቶ ነው! አልጋው ላይ ተቀምጫለሁ። እዛ አልጋ ላይ የተቀመጠው ግን እኔን ሊጠይቀኝ የ መጣው ወንድሜ ነበር። እንዴት እንዱህ እንደተደረገ ለማወቅ የሴት ጓደኛዬ ጋር ደውዬ ማግኘት እንዳለብኝ አመንኩ። ልጅቷንም አገኘዋት። እንዴት እንደሆነም በዘርዝር ነገረችኝ። ዳኒዬ አሳዘነኝ። ፎቶው ተሰርቆ ተወስዶ ነው እንዲህ የተሰራው። ይህንን ተንኮል ያሰራው ከምወዳት ጓደኛዬ ጋር ተመሳጥሮ ያ ይፈልገኝ የነበረው ልጅ ነው። ይህ ቀላል ስለሆነ ለዳኒብትክክለኛውን ፎቶ አሳይቼው አሳምነዋለሁ! ብዬ አሰብኩኝ። በፍጥነት ወደቤት ሄጄ ስፈልገው ፎቶው የለም። ኤልሳ ጋር ደውዬ እባክሽ እኔ ከአንቺ ምንም አልፈልግም ተንኮል የተሰራበትን ትክክለኛውን ፎቶዬ ስጪኝ አልኳት። ይቅርታ አድርጊልኝ ማርቲ ፎቶውን ልጁ ቀዳዶ ጥሎታል አለችኝ።"
ታሪኩ ይቀጥላል......ነገ ከምሽቱ 3:00 ላይ ይቀጥላል
እራሶን በማርታ ቦታ ያድርጉና በቀጣይ ምን ያደርጋሉ? መልስዎትን በ @Biblicalmarriage_bot በኩል ይላኩልን!