#HPR
👉 የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን የተመለከተው የአዋጁ አንቀጽ የመኖሪያ ቤት አከራዮች በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ እንዳይጨምሩ ይከለክላል።
👉 አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪው አካል በዓመት አንድ ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።
👉 በአዋጁ መሠረት የሚደረገው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ አንድ ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።
👉 የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።
👉 አከራዮች ከሁለት ወር የቤቱ ኪራይ በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ አይችሉም።
👉 የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው የመያዝ ግዴታ አለባቸው።
👉 ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት። ሁለቱም ወገኖች የቤት ኪራይ ውሉ በተፈረመ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ውሉን አቅርበው እንዲረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። አዋጁን ተከትሎ የሚደረግ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም።
✅ በአዋጁ መሠረት ተቆጣጣሪ አካል ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡
@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆 Join
የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቤት ኪራይን የተመለከተ አዲስ ውሳኔ አሳለፈ።