Postlar filtri


crypto price  prediction (ዋጋቸውን የሚገምት)  ምርጥ Bot ነው። 👇👇
https://t.me/Amlcryptocheckbot?start=_tgr_UXvvVAViNjRk
https://t.me/Amlcryptocheckbot?start=_tgr_UXvvVAViNjRk




የመኖሪያ ህንፃ ተደርምሶ 7ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ጠሮ መስኪድ አካባቢ
የመኖሪያ ህንፃ ተደርምሶ የ 7ሰዎች ህይወት አልፏል ።

የወረዳው አስተዳደር አይዳ አወል እንደተናገሩት ፤ ምሽት 5ሰዓት ባጋጠመው አደጋው ህይወታቸውን ያጡት ቤቶቹ የመፍረስ አደጋ ሲጋረጥባቸው ከጀርባ የነበሩ ቤቶች ላይ ወድቀው ነው ተብሏል።

በአደጋው ህይወታቸውን ስላጡ ፣ ስለ ወደመ ንብረት እና ሌሎች ጉዳቶች ተጨማሪ መረጃ አልተሰጠም ።

https://t.me/Ankuar_news
https://t.me/Ankuar_news
👆👆ለበለጠ  መረጃ ይቀላቀላሉን👆👆


ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሲዘዋወር የተመለከትነው በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ውስጥ በምትገኘው ገጠራማ ቀበሌ ውስጥ ለ7 አመታት በ8.7 ሚሊዮን በመገንባት ላይ የነበረው ህንፃ ቤተክርስቲያን መመረቁን ተከትሎ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ደስታውን በጥይት ተኩስ መግለፁ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ልጁ ትጥቁን አውርዶ እንዲታሰር ተደርጓል።

👉የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ካሰራጨዉ መግለጫ  እንደተመለከተነው ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ  ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን  በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው ወቅሷል።

አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ   በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል።


አርቲስት #አማኑኤል #ሀብታሙ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከኤርፖርት በፖሊስ ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እንደታሰረ እስካሁን አልተለቀቀም።

አርቲስት አማኑኤል የአንድ ሰው ትያትር የሆነውን “ ዕብደት በህብረትን “ቲያትር ለማሳያት ከአዲስ አበባ ወደ እስራኤል ሀገር ሊሄድ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ለጥያቄ ትፈለጋለህ ብለው ፖሊሶች ይዘውት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ታስሯል።


#update

ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው - #ህወሓት


ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድር እያደረገ ነው " የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ህወሓት ግን " ይህ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው " ብሏል።

ህወሓት ፥ " ከብልጽግና ጋር በተከታያይ እየተካሄደ ያለው ውይይት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው " ሲል ገልጿል።

ከብልጽግና ፓርቲ ጋር #መሰረታዊ የሆነ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳለው የገለጸው ህወሓት ፤ " ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች አሉ " ብሏል።

" ህወሓት ከብልጽግና ጋር ሊቀላቀል / ሊዋሃድ ንግግሮች ተጀምረዋል " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው ሲል አሳውቋል።

https://t.me/Ankuar_news
https://t.me/Ankuar_news
👆👆ለበለጠ  መረጃ ይቀላቀላሉን👆👆




ከየመን ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ 16 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው አለፈ
***


ላንት ምሽት ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ አራ ከሚባል ስፍራ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጎዶሪያ በሚባል አካባቢ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት አልፏል፡፡

በጀልባ መገልበጥ አደጋው የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት ሲጠፋ አብረው የተሳፈሩ 28 ዜጎችን እስካሁን ማግኘት አለመቻሉ ተጠቅሷል፡፡

በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች መካከል 5ቱ ሕፃናት መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፤ 1 ሴትን ጨምሮ 33 ፍልሰተኞች በሕይወት ተርፈው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል። 

ኤምባሲው በደረሰው አሳዛኝ ክስተት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ፤ ከጅቡቲ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ህገ ወጥ ጉዞ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው የዜጎቻችንን ሕይወት እያሳጠ እንደሚገኝ አስገንዝቧል። 

ዜጎች በህገ ወጥ ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ኤምባሲው፤ የፍትህ አካላትም ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ከገጠራማ የአገሪቱ አካባቢዎች ዜጎችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጓቸው ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪውን አስተላልፏል።

ከ2 ሳምንት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በደረሰ አደጋ የ38 ፍልሰተኛ ዜጎቻችን ሕይወት ማለፉ የሚታወስ ነው።

https://t.me/Ankuar_news
https://t.me/Ankuar_news
👆👆ለበለጠ  መረጃ ይቀላቀላሉን👆👆


#update

ከአላማጣ እና የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን #ተመድ አስታወቀ።

ግጭት ከተነሳባቸው የአላማጣ ከተማ፣ ዛታ እና ኦፍላ የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ተፈናቃዮቹ የተጠለሉባቸውን የዞን ባለሥልጣናት ዋቢ አድርጎ ጽህፈት ቤቱ ሰኞ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት መሠረት ከተፈናቃዮቹ መካከል 42 ሺህ የሚሆኑ በሰሜን ወሎ በምትገኘው ቆቦ ከተማ እንዲሁም 8300 የሚሆኑት ደግሞ በሰቆጣ እና ዋግ ኽምራ ዞኖች ተጠልለዋል ብሏል።

በአብዛኛው ሴቶች፣ ህጻናት፣ ታዳጊዎች እና አረጋውያንን ያሉበት ተፈናቃዮች በማኅበረሰቡ ባሉ ቤቶች ለመጠለል እየሞከሩ እንደሆነ ገልጾ፣ ሌሎች ደግሞ ከቆቦ ከተማ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኝ ጋራ ሌንጫ በተሰኘው የኢንዱስትሪ መንደር ክፍት ቦታ ላይ ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል።

በዚህ ስፍራ የተጠለሉ ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ለበልግ ዝናብ መጋለጣቸውን የጠቀሰው የመንግሥታቱ ድርጅት መግለጫ የተወሰኑትን ተፈናቃዮች ወደ ሌላ ስፍራ ለማዘዋወር እየተሞከረ እንደሆነ መሬት ላይ ያሉ አጋሮቹን ዋቢ አድርጓል ጠቅሷል።

https://t.me/Ankuar_news
https://t.me/Ankuar_news
👆👆ለበለጠ  መረጃ ይቀላቀላሉን👆👆


ጋዜጠኛ ፍላጎት አብርሃም (የልጅ ማኛ) በድጋሚ ታስራለች።


https://t.me/Ankuar_news
https://t.me/Ankuar_news
👆👆ለበለጠ  መረጃ ይቀላቀላሉን👆👆


የፈረሱት ሰፈሮች ለጨረታ ቀረቡ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ለኮሪደር ልማት ሲል ያፈረሳቸውን ሠፈሮች ጨምሮ በ250 በላይ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ተሰምቷል።

የሊዝ ጨረታው የወጣባቸው ቦታዎች በአስር ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው። በፈረሰው ፒያሳ አካባቢ 2 ሺህ 179 ካሬ ሜትር ስፋት ካለው ቦታ ጀምሮ እስከ ዝቅተኛው 650 ካሬ ሜትር ድረስ የሚገኙ 22 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጥቶባቸዋል።

አስተዳደሩ ለ22ቱም ቦታዎች ያቀረበው የሊዝ መነሻ ዋጋ በካሬ 2 ሺህ 213 ብር ከ25 ሳንቲም ነው። የአኹኑ የሊዝ ጨረታ፣ የከተማ አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ካወጣው የሊዝ ጨረታ በኋላ ለኹለተኛ ጊዜ የወጣ ነው።

https://t.me/Ankuar_news
https://t.me/Ankuar_news
👆👆ለበለጠ  መረጃ ይቀላቀላሉን👆👆


#ሕወሓት

ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ መሆኑ
ተሰማ

ሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ–ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል።

ከኹለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረመው ሕወሓት፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልፅግናን በመቀላቀል በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት መስማማቱን ቢገልፅም፣ ፓርቲውን ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰብኩት መረጃ ያመለክታል ስትል ዘግባለች።

ከብልፅግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን፤ ብልፅግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልፅግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም።

አሁን እየተደረገ ባለው ድርድር ሕወሓት የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ ተሻሽሎ በፓርቲ ውስጥ አባል ድርጅቶች እኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የሥራ አስፈፃሚ ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋል።

ብልፅግና ግን ሕወሓት የተናጠል ህልውናውን አክስሞ ብልፅግናን እንዲቀላቀልና ውክልናውም በትግራይ ህዝብ ቁጥር ልክ የሚወሰን መሆኑን ይገልፃል።

የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር የጀመሩት ሲሆን፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው በጉዳዩ ላይ በስፋት መነጋገራቸው ተገልጿል።

በሕወኋት በኩል ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው …አስፈላጊም አይደለም” ብለው የሚያምኑ አመራሮች ቢኖሩም፤ "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው፣ በተለይም የትግራይን ፀጥታና ደህንነት ለመስጠበቅ ከብልፅግና ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑ መኖራቸውንም ዘገባው አመላክቷል።

https://t.me/Ankuar_news
https://t.me/Ankuar_news
👆👆ለበለጠ  መረጃ ይቀላቀላሉን👆👆


በ ASTU የ Civil Engineering 5ተኛ አመት ተማሪ የነበረችው እና አኒውሪዝም በሚባል በሽታ ተጠቅታ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ የነበረችው ቤዛዊት ገ/ዮሐንስ በትላንትናው ዕለት ህይወቷ ማለፉን ዩኒቨርስቲው አሳውቋል።

ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ፣ ለጓደኞቿና ለቤተሰቦቿ መፅናናትን እንመኛለን🙏🙏

@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆join


በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ጥብቅ ጥበቃ ከሚደረግበት አዳራሽ ውስጥ 30 ሚሊዮን ዶላር ተዘረፈ

አዳራሹ የደህንነት ካሜራን ጨምሮ በርካታ ጥብቅ ጥበቃ ማድረግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂ የተገዘጠሙለት ቢሆንም አንድም መረጃ እንዳልተገኘ ተገልጿል።

በሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ ባለ አንድ የገንዘብ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ የተፈጸመው ስርቆት የብዙዎችን ትኩረትን ስቧል፡፡

የሎስ አንጀለስ ፖሊስ እና ኤፍቢአይ ጉዳዩን በጋራ እየገመገሙ ነው የተባለ ሲሆን ካሽ ገንዘቡ በተቀመጠበት አዳራሽ ውስጥ ያሉት ደህንነት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂዎች ለምን እንዳልሰሩ እየመረመሩ እንደሆነ ኤፒ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ ስርቆቱ የተፈጸመው በፈረንጆቹ ፋሲካ ዕለት ማለትም ባሳለፍነው ዕሁድ ዕለት እንደተከናወነ ተገልጿል፡፡

በሎስ አንጀለስ ታክ እንዲህ አይነት ዘረፋ ተፈጽሞ አይውቅም የተባለ ሲሆን ዘረፋው አስደንጋጭ ሆኖ አልፏል ተብሏል፡፡

ገንዘቡ የተቀመጠበት አዳራሽ ንብረትነቱ መሰረቱን በካናዳ ያደረገ ታዋቂ እና ታማኝ የጥበቃ እና ደህንነት አገልግሎት የሚሰጠው ጋርዳ ወርልድ የተሰኘው ኩባንያ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

እንደ ድርጅቱ የደህንነት ቁጥጥር ከሆነ አይደለም ገንዘብ መዝረፍ በአካባቢው ቀስ ብሎ መንቀሳቀስ እንኳን አይቻልም ነበር የተባለ ሲሆን ይህ ሁሉ ገንዘብ ሲዘረፍ አለመታወቁ አግራሞትን ጭሯል፡፡

ይሁንና እስካሁን ዘራፊዎቹን በሚመለከት የወጣ መረጃ የሌለ ሲሆን ፖሊስ ጉዳዩን መመርመር ከጀመረ አንድ ሳምንት ቢያልፈውም እስካሁን ፍንጭ ስለማድረጉ የወጣ መረጃ የለም፡፡


@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆join


ጁምዓና ከተራን ጨምሮ አራት ቀናት ሥራ ዝግ ሆኖ እንዲከበሩ ጥያቄ ቀረበ

ጁምዓ፣ ከተራና ቃና ዘገሊላ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ እንዲሁም የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በዓላት ሥራ ዝግ ሆነው እንዲከበሩ በፓርላማ ጥያቄ መቅረቡን ሪፖርተር አስነብቧል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጤና፣ የሕዝብ በዓላትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የሕዝብ ውይይት የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ምሁራንና ሌሎች ተቋማት ተሳትፈዋል።

ተሳታፊዎቹ ምን ጥያቄ አቀረቡ?

👉 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በመወከል የተገኙት ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ በእስልምና አንድ ሰው 3 ተከታታይ ጁምዓ ካልተገኘ በመናፍቅነት የሚያስፈርጅ ከባድ ጉዳይ በመሆኑ፣ ዓርብ (ጁምዓ) ቀን ሥራ ዝግ እንዲሆን፣ ወይም ደግሞ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ከአምስት ሰዓት ተኩል እስከ ሰባት ሰዓት ተኩል በአዋጁ መካተት አለበት ብለዋል።

👉 ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያሪክ የሕግ መምርያ ኃላፊ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት፣ እየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ባህረ ዮርዳኖስ ሄዶ መጠመቁን የሚያሳየው የቃል ኪዳኑን ታቦት በመያዝ ጥር 10 ቀን የሚከበረው ከተራና ከጥምቀት በኋላ ጥር 12 ቀን የሚከበረው ቃና ዘገሊላ ክብረ በዓላት ከሥራ ዝግ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

👉 በተጨማሪም የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ታስቦ ከመዋል ይልቅ ከሥራ ዝግ ሆኖ መከበር ይገባዋል ያሉት ደግሞ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር) ናቸው፡፡

የተሰጡ አስተያየቶች ረቂቅ አዋጁን ለማጎልበት እንደሚያግዝ ሲገለፅ፣ አዋጁ ኢትዮጵያውያንን እንዲመስል ዘላቂነት ያለው ውይይት እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆join


#Meta
ትላንትና ምሽት በሜታ ኩባንያ ስር የሚተዳደሩት ፌስቡክ፣ ዋትሳፕ  እና ኢንስታግራም የሚባሉት ማህበራዊ ሚዲያዎች በአለም ዙሪያ አገልግሎታቸው ለተወሰነ ሰዓት ተቋርጦ ነበር።

      እነዚህ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከ 1ወር በፊት የመቆራረጥ እክል ገጥሟቸው እንደነበር አይዘነጋም።

@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆join


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ህንጻ በቅጽበት ሲደረመስ


በታይዋን ሁዋሊን በተባለ አካባቢ በርካታ ፎቆች ያሉት ህንጻ በቅጽበት ከመሬት ጋር ተቀላቅሏል።

ህንጻው በራስ ገዝ ደሴቷ በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ ነው የፈራረሰው።

በመንገድ ላይ የነበሩ ሰዎችም ከአደጋው ራሳቸውን ለማትረፍ ሲሯሯጡ በደህንነት ካሜራ ተቀርጿል።

በታይዋን ከ25 አመት በኋላ ከባድ ነው በተባለው ርዕደ መሬት ዘጠኝ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ የተነገረ ሲሆን፥ ከ800 በላይ ሰዎችን አቁስሏል።


@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆join


#ይሳተፉ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ "የክብር ዶክትሬት ሽልማት እና የዶክትሬት ትምህርት በኢትዮጵያ" በሚል ጭብጥ ላይ የገለጻና የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

መድረኩ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ አቅራቢነት እንዲሁም በፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ አወያይነት ይካሔዳል።

መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ነገ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይካሔዳል፡፡ ውይይቱን በዙም መሳተፍም ይቻላል፡፡

Join Zoom Meeting:
https://us06web.zoom.us/j/83253374239...
Meeting ID: 832 5337 4239
Passcode: 921303

@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆join


#HPR

የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቤት ኪራይን የተመለከተ አዲስ ውሳኔ አሳለፈ።


👉 የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን የተመለከተው የአዋጁ አንቀጽ የመኖሪያ ቤት አከራዮች በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ እንዳይጨምሩ ይከለክላል።

👉 አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪው አካል በዓመት አንድ ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።

👉 በአዋጁ መሠረት የሚደረገው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ አንድ ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።

👉 የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።

👉 አከራዮች ከሁለት ወር የቤቱ ኪራይ በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ አይችሉም።

👉 የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው የመያዝ ግዴታ አለባቸው።

👉 ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት። ሁለቱም ወገኖች የቤት ኪራይ ውሉ በተፈረመ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ውሉን አቅርበው እንዲረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። አዋጁን ተከትሎ የሚደረግ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም።

✅ በአዋጁ መሠረት ተቆጣጣሪ አካል ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡

@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆 Join


በታላቁ የ'#ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ [#GERD] ዙሪያ በሚኖረው ሰው ሰራሽ ሀይቅ 70 ደሴቶች እንደሚፈጠሩ ተነገረ፡፡

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሀይቅ፤ የተለያዩ የኢንቨስትመንት እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን እድል የሚፈጥር ነው ተብሏል፡፡

በግድቡ ዙሪያ የተንጣለለው ዉሃ 246 ኪሎ ሜትር የሚሆን ቦታ የሚሸፍን ሰው ሰራሽ ሀይቅ እንደሚፈጥርም ተጠቅሷል፡፡

ይህም የ'#ጣና ሀይቅን በ 3 እጥፍ እንደሚበልጥ መገመቱን ተነግሯል።

© SHEGER FM

@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆 Join

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.