በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ጥብቅ ጥበቃ ከሚደረግበት አዳራሽ ውስጥ 30 ሚሊዮን ዶላር ተዘረፈ
አዳራሹ የደህንነት ካሜራን ጨምሮ በርካታ ጥብቅ ጥበቃ ማድረግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂ የተገዘጠሙለት ቢሆንም አንድም መረጃ እንዳልተገኘ ተገልጿል።
በሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ ባለ አንድ የገንዘብ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ የተፈጸመው ስርቆት የብዙዎችን ትኩረትን ስቧል፡፡
የሎስ አንጀለስ ፖሊስ እና ኤፍቢአይ ጉዳዩን በጋራ እየገመገሙ ነው የተባለ ሲሆን ካሽ ገንዘቡ በተቀመጠበት አዳራሽ ውስጥ ያሉት ደህንነት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂዎች ለምን እንዳልሰሩ እየመረመሩ እንደሆነ ኤፒ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ስርቆቱ የተፈጸመው በፈረንጆቹ ፋሲካ ዕለት ማለትም ባሳለፍነው ዕሁድ ዕለት እንደተከናወነ ተገልጿል፡፡
በሎስ አንጀለስ ታክ እንዲህ አይነት ዘረፋ ተፈጽሞ አይውቅም የተባለ ሲሆን ዘረፋው አስደንጋጭ ሆኖ አልፏል ተብሏል፡፡
ገንዘቡ የተቀመጠበት አዳራሽ ንብረትነቱ መሰረቱን በካናዳ ያደረገ ታዋቂ እና ታማኝ የጥበቃ እና ደህንነት አገልግሎት የሚሰጠው ጋርዳ ወርልድ የተሰኘው ኩባንያ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
እንደ ድርጅቱ የደህንነት ቁጥጥር ከሆነ አይደለም ገንዘብ መዝረፍ በአካባቢው ቀስ ብሎ መንቀሳቀስ እንኳን አይቻልም ነበር የተባለ ሲሆን ይህ ሁሉ ገንዘብ ሲዘረፍ አለመታወቁ አግራሞትን ጭሯል፡፡
ይሁንና እስካሁን ዘራፊዎቹን በሚመለከት የወጣ መረጃ የሌለ ሲሆን ፖሊስ ጉዳዩን መመርመር ከጀመረ አንድ ሳምንት ቢያልፈውም እስካሁን ፍንጭ ስለማድረጉ የወጣ መረጃ የለም፡፡
@Ankuar_news
@Ankuar_news
ለተጨማሪ መረጃ 👆join