ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሲዘዋወር የተመለከትነው በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ውስጥ በምትገኘው ገጠራማ ቀበሌ ውስጥ ለ7 አመታት በ8.7 ሚሊዮን በመገንባት ላይ የነበረው ህንፃ ቤተክርስቲያን መመረቁን ተከትሎ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ደስታውን በጥይት ተኩስ መግለፁ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ልጁ ትጥቁን አውርዶ እንዲታሰር ተደርጓል።
👉የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ካሰራጨዉ መግለጫ እንደተመለከተነው ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው ወቅሷል።
አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል።