መጽሐፉን ሳታነቡ በትረካ ያዳመጣችሁት
እና የወደዳችሁትን መጽሐፍ የቱ ነው?
አምስት በድምጽ የተዘጋጁ መጻሕፍትን የማዳመጥ ጥቅሞች
በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ያደረጉ የበርክሌይ ዩኒቨርሰቲ ባለሞያዎች እንደሚሉን አዕምሯችን በየትኛውም መንገድ መረጃን ተቀብሎ መመዘግብ ስለሚችል መጻሕፍትን ማዳመጥ ከማንበብ እኩል ባይሆንም እንኳ በየትኛውም ቦታ ለመደመጥ ምቹ ስለሆነ አድማጮቹ መፅሐፉን ያነበቡት ያህል እንዲሰማቸው ያረጋል፡፡ በመቀጠል መጻሕፍትን ማድመጥ ዐይናችንን ያሳርፍልናል፤ እንደምናውቀው በዚህ ዲጂታል ዓለም ውስጥ በስራ፣ በትምህርት፣ በመዝናናት እና በሌሎችም ጉዳዮች ምክንያት ዐይናችን ሲለፋ ይውላል ስለዚህ ኦዲዮ መጻሕፍትን በመስማት ያለ ዓይናችን ድካም ማንበብ እንችላለን፡፡
ሌላኛውን ጥቅም ደግሞ እንይ፤ ጥሩ እንቅልፍ እንዲኖረን ያደርጋል፤ ከመኝታ በፊት ትረካዎችን መስማት ተፈጥሯዊ የእንቅልፍ ስርዓታችንን ያግዘዋል፡፡ ብሎም ተጨማሪ ስራዎችን እንድንሰራ ይፈቅዱልናል፤ እንደ ጠረጴዛ መወልወል፣ ልብስ መተኮስ እና መሰል ነገሮችን ስናደርግ የድምጽ መጻሕፍትን መስማት እንችላለን ይሄም ጊዜያችንን ይቆጥብልናል፡፡
በመጨረሻም፤ መጽሐፉ የተጻፈበትን ቋንቋ እንድንለምድ ይረዳናል ፤ አፍ መፍቻችን ባልሆነ ቋንቋ የተጻፉ ትረካዎቹን ስንሰማ ቃላት እና አረፍተ ነገር እንዴት እንደሚሰካካ እንዲሁም የቋንቋው ትክክለኛ አነጋጋር እንዲገባን ይሆናል
መጽሐፉን ሳታነቡ በትረካ ያዳመጣችሁት እና የወደዳችሁትን መጽሐፍ አጋሩን…