NeBeb ንበብ: Reading Platform


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


እናንብብ፣ እንወያይ፣ ነፃ እንውጣ።

APP'ችንን ያውርዱ፣ ወይም NeBeb.com ላይ ገብተው ማንበብ ይጀምሩ።
Download our APP. or visit our website and start reading.

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ፍቅር ዕውር ነው።
አንድ ሰው ቆንጆ ልጃገረድ አገባ፡፡ እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡ አንድ ቀን የቆዳ በሽታ ያዛት፡፡ ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች፣ ያሰጨንቃትም ጀመር፡፡ አንደ ቀን ባልዋ ለጉብኝት ራቅ ወደላ ስፍራ ሄደ፡፡ በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጠመውና እና ማየት አቃተው፡፡ ሆኖም የጋብቻ ህይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ፡፡ ቀናት እያለፉ ውበቷን ደረጃ በደረጃ እየባሰ፣ ሙሉ ወበቷን አጣች፡፡ ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳራቸው ሕይወት ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡ እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡ አንድ ቀን በድንገት ሞተች፡፡ ድንገት መሞቷ ታላቅ ሀዘን አመጣበት፣ ሀዘኑም ሲበረታበት ከዚያች ከተማ ለመልቀቅ ፈለገ፡፡ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች “አሁን እንዴት ብቻውን መሄድ ይችላል? ሚስቱ ነበር የምትረዳው፡፡” ብለው ይወያዩ ነበር፡፡ ሰውየውም “አይነስውር አይደለሁም ብሎ መለሰ፡፡ ይህን ያህል ጊዜ የማላይ መስዬ ነበር የቆየሁት፣ ምክንያቱም የቆዳ በሽታ እንዳለባት አውቅ ስለነበር የሷን ስሜት እንዳይጎዳ ብዬ ነው፡፡ ውበቷ ሲጠፋ መጨነቅ ስለጀመረች ምንም እንዳልሆነ እንዲሰማት ነበር፡፡ ስለዚህ እንደማላይ ነገርከት፡፡ እሷ ለኔ በጣም ጥሩ ሚስት ነበረች፡፡ እሷን ደስተኛ ማድረግ ብቻ ነበር የምፈልገው፡፡
አንዳንድ ጊዜ አውቀን አይተን ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዮች ስናልፋቸው፤ በዙሪያችን ካሉ ሰዎችን ጋር ያለን መልካም ግንኙነት እንዲጠነክር ይረዳል፡፡
https://nebeb.com/article/6045a09e09458e768b6186db

24.7k 1 317 19 31

በጎች እና ተኩላወች
ከተረት አባት፣ ኤዞፕ [aesop] የተውሰደ፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላዎች ተመካከሩና መልዕክተኞች ወደ በጐች ላኩ፡፡ የተኩላዎቹ ልዑካን በጐች መንደር ደረሱ፡፡ በጐች ተኩሎች መጡብን ብለው ተሸሸጉ፡፡ አድፍጠው ጋጣቸው ውስጥ ተደብቀው ተቀመጡ፡፡ ተኩሎቹ ግን ረጋ ብለው፣ አደብ ገዝተው፤
“በጐች አትደናገጡ፣ እንደምና ዋላችሁ” አሉ፡፡
“ለድርድር ነው የመጣነው” አሉ ተኩሎቹ፡፡
በጐቹ ቀስ በቀስ ከተደበቁበት ወጡ፡፡
በጐቹም “እኛ በድርድር እናምናለን፡፡ እህስ፣ ምን እግር ጣላችሁ? ምን የድርድር ሃሳብ ይዛችሁ መጣችሁ?” አሉ ፡፡
“አንድ የቸገረ ነገር ገጥሞን ነበርና ልናዋያችሁ ፈልገን ነው” አሉ የተላኩት ተኩላዎች።
በጎቹም ዞር ዞር በለው ተያዩና፣ “ምንድነው? ከተመካከርን የማይፈታ ምንም ነገር አይኖርም፡፡ ዋናው ተቀራርቦ መነጋገር ነው ንገሩን፡፡” አሉ።
ተኩሎችም፤ “እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ የቸገረን ነገር ምን መሰላችሁ? ይኸው ከተፈጠርን ጀምሮ ከውሾች ጋር ነጋ-ጠባ እንታገላለን፡፡ የችግራችን መነሻም መድረሻም ውሾች ናቸው፡፡ እርኩስ ውሾች እኛን ባዩ ቁጥር ይጮሃሉ፣ ይተነኩሱናል፣ ሠፈር ይረበሻሉ!፣ ለእኛና ለእናንተ ወዳጅነትና ሰላም ዋና እንቅፋቶች ውሾች ናቸው፡፡” አሉ
በጐችም፤ “ታዲያ ምን እናድርግ? ምን ዘዴ ብንፈጥር እንቅፋቶቹን ማስወገድ እንችላለን?” ሲሉ፣
ተኩሎችም፤ “እናንተ እሺ ካላችሁማ ዘዴ አይጠፋም ነበር”
“እኮ ዘዴ ካለ ንገሩና?”
“ለጌታችሁ ንገሩ፡፡ ውሾች እንዳልተመቿችሁ፣ ሰላምም እንደነሷችሁ አስረዱ፡፡ ይባረሩልን በሉ!፣ እኛም ለእናተም ከጩሀታችው ሰላም ታገኛላችሁ” ይሉዋቸዋል።
“ይሄማ ቀላል ነው፡፡ እንነግራቸዋለን፡፡”
በዚህ ተስማሙና ተኩሎቹ ሄዱ፡፡
በጐቹ፤ ውሾቹ እንዲባረሩ ለጌታቸው አመለከቱ፡፡ ጌታቸውም ስንት ዘመን ቤት - ደጁን ይጠብቁ የነበሩትን ውሾች ከቤት አስወጥቶ አባረራቸው፡፡
ከዚያን ቀን በኋላ፣ የዋሆቹ በጐች የዘመናት ጠባቂዎቻቸውን አጡ፡፡ ተንኮለኞቹ ተኩሎች እየተዝናኑና በጐቹን አንድ በአንድ እየለቀሙ፤ በሏቸው፡፡

የድርድርን ትርጉም አለማወቅ እርግማን ነው፡፡

በርቱላን፣ አንብቡ። ሌሎችም እንዲያነቡ እሲቲ ከስቅሱዋችው።
እናንብብ፣ ከአይምሮ ባርነትም እራሳችንን ነጻ እናውታ። ቡሀላ እንድበጎቹ ድርድር ላይ ኩማር እንዳንበላ።

***********************
ከውደዳችሁት፣ ላይክ እና ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩት፡፡
👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽
***********************
https://nebeb.com/article/604301ce09458e768b616b6c

Nebeb.com
ንበብ ለንባብ
እናንብብ፣ እንወያይ፣ ነጻ እንውጣ!
#Ethiopia #Nebeb #ንበብ ለ #ንባብ


ሁለት ጡረታ የወጡ ጎረቤታማች ሽማግሌዎች ነበሩ። አንድ ፓይለት ሌላው መምህር፡፡ ሁለቱም አንድ ወቅት ላይ ተመሳሳይ አትክልት በጓሯቸው ተከሉ፡፡
ፓይለቱ ለአታክልቶችው ያለው ፍቅር ይገርማል። ወሃ ከመጠን በላይ ይሰታቸዋል፣ የተለያየ ማዳበሪያ እየገዛ ያደርግላቸዋል፣ ከመጠን በላይ ይንከባከባቸዋል፡፡
መምህሩ ደሞ ጠዋት ይነሳና ዉሃ ያጠጣል፡፡ እንደፓይለቱ ግን ብዙ እንክብካቤ የለውም፡፡
አንድ ቀን ማታ ከባድ ዝናብ ጣለ ሌሊቱን ሙሉ ዘነበ፡፡
ጠዋት አትክልታቸውን ለማየት ሁለቱም ወደ ጉዋሯቸው ሄድ፡፡የፓይለቱ መሉ በመሉ ወድሟል፡፡ ተነቃቅሎ ወድቋል፡
የመምህሩ ደሞ ምንም አልሆነም፣ በዝናብ ከመሙላት ውጪ፡፡
ፓይለቱ ገረመው፡፡ እንደዛ እየተንከባከበው ምክንያቱን ለማወቅ ጉዋጉዋና ወደ መምህሩ ሄዶ "አንድ አይነት እፅዋት በተመሳሳይ ግዜ ተክለን አታክልቶቹን ከአንተ በላይ እየተንከባከብኩት፣ ግን የኔ በዚህ ዝናብ ወደሙ፡፡ ያንተ ደሞ ምንም አልሆነም፡፡ እንዴት??? ለምን???" ብሎ እየተገረመ ጠየቀው፡፡ መምህሩም "አንተ ለእፅዋቶቹ የተለየ እንክብካቤ ብዙ ውሃ እና አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ትሰጥ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት እፅዋቶቹ ውሃና mineral ለማግኘት ስራ አለሰሩም፡፡ ሁሉንም አንተ ታቀርብላቸዋለህ፡፡ እኔ ደሞ የተወሰነ እንዳይደርቁ የሚሆን ውሃ እሰጣቸዋለሁ፡፡ ከዚያ በላይ ከፈለጉ ራሳቸው ስራቸውን በመጠቀም እንዲፈልጉ እተዋቸዋለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት ስራቸው ተጨማሪ ውሃና ሚንራል ፍለጋ ወደ ውስጥ እድጉዋል፡፡ ለዚህም ነው የዳኑት፡፡ ወደመሬት ስራቸው በደንብ ስለተቀበረ፡፡"

እፅዋቱን ልጅ ያላችሁ እንደልጃችሁ፣ ትንሺ እህትና ወንድም ያላችሁ ደሞ እንደነሱ አርጋችሁ ቁጠሩዋቸው። በምታሳድጓቸው ግዜ እንደፓይለቱ ሁሉን ነገር እየሰጣችሁ በራሳቸው እንዳይቆሙ ካደረጋችሁዋቸው በችግር ግዜ ወድቀው ታገኛቸዋላችሁ።










”በድንጋዩም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ትችላለክ። ላንተ ሁለቱም ያው ናቸው” አሉት፡፡ ጳውሎስ በጥሞና አዳመጠና ፣ ለትንሽ ጊዜ አሰብ አድርጎ እንደ መባነን ቀና አለና “አዎ ፣ ልክ ኖት አባት ፡፡ እኔ በጣም ሞኝ ነበርኩ፣ ደስተኛ ለመሆን የወርቅ ክምር አያስፈልገኝም፣ አልጠቀመኝ! ስንቖጥቖጥ ሁሉንም አጣሁት” በማለት እጃችን ላይ ባለው ነገር ደስተኛ ለመሆን ለራሱ ቃል ገባ፡፡

እጃችን ላይ ያለንን ነገር ሳንጠቀም ደስታን ፍለጋ ከምንባክን ያለንን ነገር ለደስታችን ምንጭ ማድረግ እንችላለን፡፡

***************************
ሼር በማድራግ ለሎሎች ያጋሩት፡፡
👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽
*****************************

https://www.nebeb.com/article/603c8115ea0a9c0760b290b9

Nebeb.com
#Ethiopia #Nebeb #ንበብ ለ #ንባብ


ሀብትና ደስታ

ጳውሎስ የሚባል በጣም ሀብታም ነጋዴ ነበር። ለቤተሰቦቹንም ሆን ለራሱ ገንዘቡ ማውጣት አይወድም። ሰው እንዳይሰርቀውም ሁሌም ፈራቶ፣ ድሃ መስሎ ነው የሚኖረው፡፡ ያረጁ እና ጊዜው ያለፈባቸውን ልብሶችን ነው የሚለብሰው፡፡ ሰዎችም “እዩት እይሄን ቖጥቓጣ” እያሉ ይስቁበት ነበር፣ ነገር ግን እሱ ግድ የለውም፡፡ እሱ የሚያስበው ሰለ ገንዘቡ መጠን ብቻ ነው። ደስታውም ከገንዘብ ጋር ብቻ ይመስለዋል፡፡ አንድ ቀን፣ አንድ ትልቅ ወርቅ ገዛ። ከጭንቀቱም የተነሳ እቤቱ ጋር ከነበራው አንዱ ዛፍ አጠገብ ባለው ጉድጓድ ውስጥ ወርቁን የደብቀዋል፡፡ እይተኛም ወርቁን ሲጠብቅ፣ በየምሽቱ ወርቁ መኖርን ለማረጋገጥ እና ለማየት ወደ ጉድጓዱ ይሄድል፡፡ “መቼም ወርቔን ማንም አያገኝውም!” እያለ በፈገግታ ያጉረመርማል።
እንደ ልማዱ በሌሊት ከቤቱ ሰወጣ አንድ ሌባ ያየዋል። ዛፉ ጋር ካለው ጉድጎዱ ወርቁን አውጥቶ ሲመለከት ያየዋል፡፡ እናም ጳውሎስ ወደ ቤቱ ሲሄድ ሌባው የወርቅ ጥቅሉን ከጉድጎዱ ውስጥ አውጥቶ እየሳቀ ይሮጣል። በሚቀጥለው ቀንም እንድ ልማዱ ወርቁን ለመመልከት ሲሄደ ፣ ወርቁ አልነበረም። “ተሰርኩ… ተሰረኩ፣ ኡ..ኡ..ኡ” እይለ ጳውሎስም እየጮህ ማልቀስ ጀመረ፡፡ ለቅሶውን አንድ ብልህ ሽማግሌ ይሰሙና ለመርዳትም የመጣሉ። ጳውሎስም የተሰረቀውን የወርቅ መጠን እና አሳዛኝ የሂወት ታሪኩንም ነገራቸው።
“አትጨነቅ” አሉት ፡፡
“አንድ ትልቅ ድንጋይ በጨርቅ ጠቅልለክ ወርቁ ከነበረበት ቀዳዳ ውስጥ አስገባው ፡፡” አሉት ጳውሎስም “ምን?” አላቸው። ከዛም “ለምን?”፣ እርሳቸውም ቀበል አድረገው “በጥቅል ወርቅክ ምን አደረግክ፣ ምን ተጠቀምክበት?” በለው ጠየቁጥ ጳውሎስም “በየቀኑ እየመጣው ቁጭ ብዬ እመለከተው ነበር፣ እንጂ ምንም አልተጠቀምኩበትም” አላቸው፡፡ ጠቢቡ ሽማግሌ “በትክክል!” አሉት።


“በመተሳሰብ የተሞላ ማሕበራዊ ሕይወት እንዲኖረን ሕልሜ ነው”
ኢቫን ፈርናንዴዝ

የኬኒያ ሯጭ አቤል ሙታይ እና ስፔኒያው ሯጭ ኢቫን ፈርናንዴዝ በአንድ የአትሌቲክስ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሆነው ይገናኛሉ። ኬንያዊው አቤል ሙታይ ውድድሩን በአንደኝንት እየመራ ለማጠናቀቅ እርምጃዎች ቢቀሩትም፣ የማጠናቀቂያው መስመር ጋር ከመድረሱ በፊት ያሉት ምልክቶች ግራ አጋብተውት ውድድሩን የጨረሰ መስሎት ቆመ። ውድድሩንም ያሸንፈ መስሎት ቆመ እንጂ መጨረሻው መስመር ጋር ለመድራስ በቂ ጉልብት ነበርው። ስፔናዊው አትሌት ኢቫን ፌርናንዴዝ በሁለተኝነት እየተከተለው ያለ ተፎካካሪው ነበር። “Vamos, Vamos’ እያለ መጮህም ጀመረ። አቤልም የስፓኒሽኛ ቋንቋ ስለማይሰማ መልእክቱ አልገባውም፣ ተደናገጠም። ኢቫን ፌርናንዴዝ በሁለተኝነት እየተከተልውም ቢሆንም አልፎት ሔዶ ሩጫውን ለማሸንፍ ሕሊናው አልፈቀደለትም። አቤልንም ሩጫውን እንዲቀጥል እየጮኸ ቢነግረው ሊግባቡ አልቻሉም።ያኔ ነው ኢቫን ከኋላው ሄዶ እየገፋው ወደ ፍጻሜው መስመር በማድረስ እንዲያሸንፍ ያደረገው።

በመጨረሻም፤ አንድ ጋዜጠኛ ወደ ስፔናዊው ኢቫን ተጠግቶ "ለምን እንዲህ አደረግክ?" ሲል ጠየቀው። ስፔናዊውም "እንዲህ ዓይነት ማኅበራዊ ሕይወት የሆነ ቀን እንዲኖረን ሕልሜ ነው" ሲል መለሰ።
ጋዜጠኛው ቀጠለና፤ "ግን ለምን ኬኒያዊውን እንዲያሸንፍ አደረግከው?" አለው።
ኢቫንም: "እኔ እንዲያሸንፍ አላደረግኩትም። እርሱ ያሸንፍ ነበርኮ" ሲል መለሰ።
ጋዜጠኛው አለቀቀውም፤ "አንተ ማሸነፍ ትችል ነበርኮ" አለው።
ኢቫን ትኩር ብሎ አየውና:- "ግን በዚህ መልኩ ባሸንፍ ማሸነፌ ምን ትርጉም ይኖረው ነበር? የሜዳልያውስ ክብር ምን ይሆን ነበር? እናቴስ ስለዚህ ድል ምን ታስብ ነበር?" ብሎ መለሰለት።


ምን ታስባላችሁ?? …. Share በማረግ፣ ለሌሎች ያጋሩ


ይቅር መባባል ያስፈልገናል!
በአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ታሪክ አብርሃም ሊንከን የጎላው ለምንድነው? በዘመኑ ያሳለፋቸው ጠንካራ አሻራዎቹ፤ በክፉና ደግ ቀን የወሰናቸው ጠንካራ ውሳኔዎች ይሄንን ገናናነት እንዲሰጡት እድርጓል፡፡
ሊንከን በአሜሪካ ታሪክ ስመ-ጥር ይሁን እንጂ አሜሪካንን አላገኛትም ወይም አላቋቋማትም፡፡ በዋናነት እነ ጆርጅ ዋሽንግተን፣ ቶማስ ጀፈርሰን፣ ቤንጃሚን ፍራንክሊን እና የመሳሰሉት ናቸው ከእንግሊዝ እጅ መንጭቀው አሁን አሜሪካ ብለን የምንጠራው አገር ያቋቋሙት። ሊንከን ግን …አሜሪካ በእርስበርስ ጦርነቱ በፈራረሰች ጊዜ የነበረ ፕሬዚዳንት ነው፡፡
አገር የካዱ ጀነራሎች ተማርከው ለመጨረሻ ጊዜ በተገኙበት የካቢኔ ጉባኤ ላይ ሊንከን የተናገረው የሰለጠነ ሀሳብ ሁሉንም ያስደንቃል፣ ያረካል፣ ሁሌም ይታወሳል፡፡
“የገደለ ይገደል!” "ዐይን ያጠፋ ዐይኑ ይጥፋ!"… ብለው የምያምኑ ብዙ የዓለም መሪዎች ነበሩ፣ ሊንከን ልብ ግን እንደዚያ አልነበረም። ይቅርታ ማድረግ ይቻላል ብሎ የሚያምን መሪ ነው፡፡ ይህንን ያንፀባረቀው ደግሞ የመጨረሻው የካቢኔ ጉባኤ ላይ ነበር፡፡ “ሀገሪቱን አምሰዋል፣ ለመገንጠል መክረዋል፣ ጦር አንስተዋል ፣ ለብዙዎች ህይወት መጥፋት መንስዔ ሆነዋል" …የተባሉ “አሸባሪዎች” ቅጣት ምንድነው?” ተብሎ ሲጠየቅ፡- “እስከ ዛሬ ድረስ የፈሰሰው ደም በቂ ነው፣ ከእንግዲህ በኋላ የማንም ደም እንዲፈስ አልፋቅድም” ነበር ያለው፡፡ ታዲያ ይህ የይቅርታ ቃል በአሜሪካውያን የፈጠረው ስሜት ቀላል አልነበረም፡፡ በቁስል ላይ ቁስል፣ በቂም ላይ ቂም ከመፍጠር ይልቅ፣ በይቅርታ ዘይት ቁስልን ማድረቅ ይሻላል፡፡ ይሄንንም በማድረጉ በዓለም ካርታ ላይ በደማቅ የተሳለች አገር ለመምራት በቃ።
እኛስ በሊንከን ቦታ ብንሆን ምን እንዲወስን እናደርግ ነበር ወይም ምን እንወስን ነበር? ይሄ ለሁላችንም ጥያቄ ሊ


‹‹ ሰዎች ሁሉ እኩል ናቸው፡፡ ፆታ የሚያበላልጥና የሚያተናንስ ነገር የለውም፡፡ ›› አውራምባ

አውራምባ በዙምራ ኑሩ በ1964 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን የራሱ የሆነ ስርዓትና ባሕሎች ያሉት ማህበረሰብ ነው፡፡ ነዋሪዎቹ አውራምባን ሲገልጹት የእኩልነት፣ የመከባበር፣ የመደማመጥና የመቻቻል አካባቢ ነው ይሉታል።

አውራምባን ከሌሎች የማህበረሰብ ስርዓቶች ምን ልዩ ያደርገዋል?

• 'የሴቶች ሥራ' እንዲሁም 'የወንዶች ሥራ' ብሎ ነገር አለመኖሩ፡፡ አንዱን ፆታ አሳንሶ ሌላውን የሚያስበልጥ የሥራ ክፍፍልን የማይደግፍ ፤ ችሎታን መሰረት ያደረገ የስራ ባሕል ያለው ማህበረሰብ መሆኑ፡፡

• ጋብቻን በተመለከተ የተጋቢዎች ፈቃድ ላይ መሰረት ያደረገ እንዲሆን ያስተምራል፡፡

• ‹‹ የሀሳብ ልውውጥ ሲኖር አንድ የተሻለ ሀሳብ ይወለዳል ›› ብለው ስለሚያምኑ አውራምባዎች ለውይይት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፡፡

• አውራምባ ስርቆትን ፤ ውሸት መናገርን ፤ ልመናንና ስንፍናን እንደ ነውር ይመለከታል፡፡

• ፆታ ያልገደበው የሀሳብና የውይይት መድረክ እንዲኖር ይፈቅዳል፡፡

• ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በፅኑ ይቃወማል፡፡

• ሁሉም ቤተሰብ በየ15 ቀን ውይይት ያደረጋል። ይህም የውይይት ባህል የእድሜ ልዩነት የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው ውስጥ አንዳች ጠቃሚ ሀሳብ አለ ‹‹ ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር ተወያይተው ችግር የመፍታትና አዲስ ሀሳብ የማፍለቅ መብት አላቸው ›› ብሎ ያምናል፡፡

• እኔን አይመለከተኝም የሚባል ነገር የለም፤ ሁሉም ይሠራል። አንድ ሰው የሚያገኘውን እውቀት 'የኔ ብቻ' አይልም፤ ለሁሉም ያካፍላል።

• የመጨረሻውና ዋነኛው የአውራምባ ማህበረሰብ የሚታወቅበት እሴት ፡- ገንዘብና ጊዜ የሚባክንባቸውን የተንዛዙና አላስፈላጊ ወጪ የሚወጣባቸው የሰርግና የሀዘን ድግሶችን በልክ እንዲሆኑ የሚያስተምሩበት መርሃቸው ነው፡፡


የንበብ የዕለቱ ቃል - ባለቅኔ ወንድም እህቶቻችን፣ እስቲ 'ውጣኝ'ን ግጠሙበት ወይም ውበት ስጡት። ካልሆነም ዓረፍተ-ነገር አበጁለት።

ቋንቋችንን እንወቅ፣ እናጎልብት፣ እናሳድግ።


መጽሐፉን ሳታነቡ በትረካ ያዳመጣችሁት
እና የወደዳችሁትን መጽሐፍ የቱ ነው?

አምስት በድምጽ የተዘጋጁ መጻሕፍትን የማዳመጥ ጥቅሞች

በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ያደረጉ የበርክሌይ ዩኒቨርሰቲ ባለሞያዎች እንደሚሉን አዕምሯችን በየትኛውም መንገድ መረጃን ተቀብሎ መመዘግብ ስለሚችል መጻሕፍትን ማዳመጥ ከማንበብ እኩል ባይሆንም እንኳ በየትኛውም ቦታ ለመደመጥ ምቹ ስለሆነ አድማጮቹ መፅሐፉን ያነበቡት ያህል እንዲሰማቸው ያረጋል፡፡ በመቀጠል መጻሕፍትን ማድመጥ ዐይናችንን ያሳርፍልናል፤ እንደምናውቀው በዚህ ዲጂታል ዓለም ውስጥ በስራ፣ በትምህርት፣ በመዝናናት እና በሌሎችም ጉዳዮች ምክንያት ዐይናችን ሲለፋ ይውላል ስለዚህ ኦዲዮ መጻሕፍትን በመስማት ያለ ዓይናችን ድካም ማንበብ እንችላለን፡፡
ሌላኛውን ጥቅም ደግሞ እንይ፤ ጥሩ እንቅልፍ እንዲኖረን ያደርጋል፤ ከመኝታ በፊት ትረካዎችን መስማት ተፈጥሯዊ የእንቅልፍ ስርዓታችንን ያግዘዋል፡፡ ብሎም ተጨማሪ ስራዎችን እንድንሰራ ይፈቅዱልናል፤ እንደ ጠረጴዛ መወልወል፣ ልብስ መተኮስ እና መሰል ነገሮችን ስናደርግ የድምጽ መጻሕፍትን መስማት እንችላለን ይሄም ጊዜያችንን ይቆጥብልናል፡፡
በመጨረሻም፤ መጽሐፉ የተጻፈበትን ቋንቋ እንድንለምድ ይረዳናል ፤ አፍ መፍቻችን ባልሆነ ቋንቋ የተጻፉ ትረካዎቹን ስንሰማ ቃላት እና አረፍተ ነገር እንዴት እንደሚሰካካ እንዲሁም የቋንቋው ትክክለኛ አነጋጋር እንዲገባን ይሆናል
መጽሐፉን ሳታነቡ በትረካ ያዳመጣችሁት እና የወደዳችሁትን መጽሐፍ አጋሩን…


አንባቢዋ ንግሥት
ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚሉት ቀዳማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ከአስተዳደር ሥራ ጎን ለጎን ከመጻሕፍት ጋር ጊዜዋን በማሳለፍ ደስታን ታገኝ ነበር። ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ በላቲንና በፈረንሳይኛ የተዘጋጁ ጽሑፎችን የምታነበው ንግሥት፤ ይህን በቋንቋ ችሎታዋ ያገኘችውን ድንቅ ነገር ሌሎችም ጋር ደርሶ እንዲደሰቱ በማለት “ክላሲክ“ ሥራዎችን ወደ እንግሊዝኛ መልሳለች፡፡ ከሁኔታው መረዳት እንደሚቻለው ንግሥቲቱ መጽሐፍ በል (ቡክ ነርድ) ከሚባት ውስጥ የምትመደብ ናት…
የእኛስ የንባብ ልምድ እንዴት ያለ ነው?


የጋዜጠኛ መአዛ ብሩ የንባብ ልምድ
‹‹ አባቴ ትጉህ አንባቢ ነበር፡፡ ዘወትር ወደ ቤት ፤ ብዙ መፅሐፍትና ጋዜጦች ገዝቶ ያመጣል፡፡ ይዞ የመጣቸው ጋዜጦች አንብቤ ስጨርስ በእጄ እንድገለብጥ ያደርጋል፡፡ ይህን የሚያደርገው … ማንበቤን ለአዕምሮዬ ፤ መጻፌን ለእጅ ጽሑፌ ማማር ከማሰብ ነበር፡፡
ዘጠኝ አመት ሲሆነኝ ከሂርና አዲስ አበባ መጥቼ ሴንት ሜሪ አዳሪ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡ ትምህርት ቤት በነበርኩበት ጊዜ ለከተማውና ለተማሪዎቹ እንግዳ ስለሆንኩኝ ብቸኝነት ይሰማኝ ነበር፡፡ ለዚህም ስል ጋዜጦችና መጻሕፍት በየቀኑ አነብብ ነበር፡፡ አነብባቸው ከነበሩት መሃል …የዛሬይቱ ና አዲስ ዘመን ጋዜጦች ይጠቀሳሉ ›› የምትለን መአዛ ብሩ ናት…
የሸገር ሬዲዮ ጣቢያ መስራችና ባለቤት ጋዜጠኛ የሆነችው መአዛ ብሩ ቅዳሜን በጨዋታ ፤ እሁድን በሸገር ካፌ የምታስናፍቅ ድንቅ ጋዜጠኛ ናት፡፡ መአዛ ግሩም በሆኑ የጥያቄ ለዛዎቿና ስለእንግዳዎቿ የምታውቅበት ልክ በአድማጮቿ ዘንድ ከሚያስወድዷት ነገሮች መሃል ናቸው፡፡ ስለ እንግዶቿ መረጃ ልታገኝ ከምትችልባቸው መንገዶች እና ከእንግዶቿ ጋር የምታወራበትን የቋንቋ ውበት ለመፍጠር እንግዶቿ ከሆኑት ነገር በጥቂቱም ማወቅ ይጠበቅባት ነበር፡፡ ለዚህ ቀዳሚ መፍትሄው ደግሞ ማንበብ ነው፡፡ የግል የንባብ ልምዷ እንዳለ ሆኖ ከደራሲ ጋር ለማውራት የድርሰትን ውጤቶች በጥቂቱም ቢሆን ማንበብ ይፈልጋል …
ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ ከማን ጋር ያደረገችው ቃለ መጠይቅ ይበልጥ ደስ ይላችኋል?… ኮሜንት አድርጉልን


የንበብ የዕለቱ ቃል - Word of the day

~ ለውይይት እና ለጥያቄ እዚህ ⬇️ ግሩፕ ላይ ተቀላቀሉ!

https://t.me/Nebeb_Discussions

@nebeb_ethiopia




ቲክቶክ እና ንበብ!
ከዚህ በፊት በአማካይ በ1 ደቂቃ 250 ቃላትን ማንበብ እንደሚቻል እና በ 10 ደቂቃ ደግሞ አንድ አጠር ያለ ሙሉ ጽሑፍ አንብበን መጨረስ እንደመንችል ጽፈንላችሁ ነበር፡፡ አሁንም ይህንን ደግመን ልናስታውሳችሁ ወደድን
በዘመናችን ከረጃጅም ጽሑፎችና ቪዲዮዎች ይልቅ አጠር አጠር ያሉ ነገሮች ይወደዳሉ። ሜሞች፣ የፌስቡክ ፖስቶችማ በጣም ተመራጭ ናቸው እና ለረጅም ሰዓት ቪድዮዎች እና ፎቶዎችን ያለ መሰልቸት እያየን ለንባብ ሲሆን የምንሰንፈው ለምንድን ነው?

አንዴ ፌስቡክ፣ ዩቱዩብ ወይም ቲክቶክ ከፍተን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ቪድዮ ማየታችን አይቀርም። በዚህ ግዜ ውስጥ ግን ሶስት መካከለኛ ርዝመት ያላቸው ጽሁፎችን ልናደምጥ ወይም ልናነብ እንችላለን።
የት ነው የምናነበው ማህበራዊ ሚድያው በጥላቻ ጽሁፎች ተሞልቷል የምትሉ ከሆነ ደግሞ ሁሉንም አይነት መዝናኛ እና መረጃ እንዲሁም እውቀት የያዙ ጽሁፎችን የያዘ የሞባይል አፕሊኬሽን አለ nebeb ይባላል፡፡ እስቲ በብዙ ለማትረፍ አንድ ጊዜ ንበብን ተመልከቱ፡፡
በመጨረሻም ይህንን እንጠይቃችሁ...
በ10 ደቂቃ ውስጥ 10 የቲክቶክ ቪድዮ ከምታዩና አንድ አጭር ታሪክ ከምታነቡ የትኛው ይበልጥባችኋል? እንነጋገርበት …. አስተያየቶቻችሁን በኮሜንት አካፍሉን።


*ችካል እና እርምጃ*
“ሀገር ማለት የኔ ልጅ” በሚለው ድንቅ ግጥም የወደድናቸው እውቁ ገጣሚና ደራሲ በድሉ ዋቅጀራ (ዶ/ር) አስረኛ ሥራ የሆነው “ችካል እና እርምጃ” የተሰኘ የረዥም ልቦለድ መፅሐፍ ከሰሞኑ በገበያ ላይ ውሏል። ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሰው ልቦለዱ፤ በ312 ገፆች ተዘጋጅቶ በ180 ብር እየተሸጠ ነው፡፡
“... የእናንተ ሞት ምን አፈራ? ትእቢት? ግትርነት? አእምሯዊ የማሰብ ነጻነትን ቀይሮ ላራምድ ያለ ችካል፣ ሞታችሁ ያፈራው ያንን ነው። እና ስማኝ ወጣትነታቸውን ከቼጉቬራ፣ መስዋእትነታቸውን ከእየሱስ ለሚያወዳድሩት ጓደኞችህም ንገራቸው። እኔ መስዋዕትነት የከፈልኩት “ያ ትውልድ” “ተራራ ያንቀጠቀጠ ትውልድ፣ ምናምን በሚሉ ድርሳናት ጠርዤ፣ ገዳይና ሟችነቴን ለልጆቼ ለማውረስ አይደለም። " ከመጽሐፉ የተወሰደ፤
መልካም ንባብ እየተመኘን ይህን እንጠይቃችሁ፤ ከዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የስራዎች የትኛውን ትወዳላችሁ?

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

6 714

obunachilar
Kanal statistikasi