ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ አገልግሎትን በድሬዳዋ አስተዋወቀ
አገልግሎቱን አስመልክቶ ለድሬዳዋ ኗሪዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አዘጋጅቷል።
መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በዳሸን ባንክ የድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ተንኮሉ ባንኩ ከወለድ ነጻ በሆነ መንገድ እያስተዋወቃቸው የሚገኙ አገልግሎቶች የማሕበረሰቡን ህይወት እንደሚያቀሉ ተናግረዋል ።
ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለድሬዳዋ ከተማ ኗሪዎች የሚተገብራቸውን ከወለድ ነጻ የብድርና ሌሎች አገልግሎቶችን እንደሚያቀርብም አስረድተዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ዳሸን ባንክ የዲጅታል ፋይናንስ ተደራሽነትን እያስፋፋ ይገኛል ብለዋል።
የከተማ አስተዳድሩ ዳሸን ባንክ ያስተዋወቀውን ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ አገልግሎት ማሕበረሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀምበት በጋራ እንደሚሰራም ገልጸዋል ።
ባንኩ ከወለድ ነጻ በሆነ መንገድ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም አመላክተዋል።
በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ስትራቴጂክ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ በበኩላቸው ባንኩ የማሕበረሰቡን እሴት የሚያበረታቱ ስራዎችን አጠናክሮ ያስቀጥላል ብለዋል።
በእለቱ አገልግሎቱን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ አገልግሎት ሴሚናር በሐረር እና ጅግጅጋ ከተሞች መካሄዱ ይታወሳል።