ዳሸን ባንክና ኖቫ ኮኔክሽንስ ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
ዳሸን ባንክና ኖቫ ኮኔክሽንስ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ ለማዘጋጀት እና ለተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ዕውቅና ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ዛሬ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡
ዳሸን ባንክን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ ኤልያስ ሁሴን እንደተናገሩት ዳሸን ባንክ ኖቫ ኮኔክሽንስ የሚያዘጋጃቸውን የነዚህ መርሃ-ግብሮች አጋር መሆኑን በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክር አመልክተዋል፡፡
የኖቫ ኮኔክሽንስ ኃላፊ አቶ ጋሻው አበዛ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ኖቫ ኮኔክሽንስ ባለፉት አራት ዓመታት ባዘጋጃቸው መርሃ-ግብሮች አጋር ሆኖ በመቆየቱና ይህን አጋርነቱንም በቀጣይ ሦስት ዓመታት ለማስቀጠል ፈቃደኛ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ስምምነቱ ዳሸን ባንክ ከኖቫ ኮኔክሽንስ ጋር በመተባበር በቀጣይ ሦስት ዓመታት በአሜሪካ ዋሺንግተን ከተማ ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማካሄድና ተፅዕኖ ፈጣሪ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን በየአመቱ ዕዉቅና ለመስጠት እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡
ስምምነቱ የተለያዩ የዳሸን ባንክ አገልግሎቶች በሰሜን አሜሪካ ለሚገኘው የዳያስፖራ ማህበረሰብ ዘንድ ይበልጥ ተደራሽ የሚሆኑበትን ዕድል እንደሚፈጥርና ዳሸን ባንክ ማኅበረሰቡ የሚሰባሰብባቸውን መርሃ-ግብሮች መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያሳየበት መሆኑ ተገልፃል፡፡
ዳሸን ባንክና ኖቫ ኮኔክሽንስ ባለፈው መስከረም ወር በዋሺንግተን የተካሄደውን ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ እና የታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ዕውቅና መስጠት መርሃ-ግብሮችን በጋራ ማዘጋጀታቸው ይታወሳል፡፡