ዳሸን ባንክ በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር ያደረገው ኤግዚቢሽን ተከፈተ
ዳሸን ባንክ ዋና አጋር የሆነበት የዲያስፖራ አውደ-ርዕይ በዛሬው ዕለት በግዮን ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።
አውደ-ርዕዩ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኀበር ከሮሆቦት ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው ።
በዳሸን ባንክ ዲያስፓራ ባንኪንግ መምሪያ ከፍተኛ ስራ አስኪያጅ አቶ ካሱ ጌታቸው በአውደ-ርዕዩ ላይ ባንኩ በቅርቡ ይፋ የሆነውን ዳሸን ሱፐር አፕን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን እያስተዋወቀ እንደሆነ ገልጸዋል።
ባንኩ ለዲያስፓራው ምቹ የሆኑና የተለያዩ አማራጮች ያሏቸውን የዲያስፓራ ተንቀሳቃሽ ሒሳብ፣በውጭ ሀገር ገንዘብ የሚከፈት የቁጠባ ሂሳብ፣ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትና ሌሎች ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ምቹ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
አውደ-ርዕዩን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ዲያስፓራ አገልግሎት ተወካይ አምባሳደር አንተነህ ታሪኩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ለበዓላት ወደ ሀገር ቤት የገቡ እንደመሆናቸው የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንዲመለከቱ ጋብዘዋል።
ማኀበሩ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎትና ሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።
ዲያስፖራው ማህበረሰብ የሀገር ቤት ቆይታውን ቀላል የሚያደርጉለት የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶችን መጠቀም እንደሚችልም አመላክተዋል።
ዛሬ የተጀመረው የዲያስፖራ ሳምንት በትብብር ለሀገር ለመስራት የምንመክርበት ነው ብለዋል።
አውደ-ርዕዩ በቀጣይ በካናዳ ቶሮንቶ እንደሚካሄድም ተጠቁሟል።
ኤግዚቢሽኑ እስከ ነገ ድረስ እንደሚቀጥል የተመላከተ ሲሆን የሀገር ውስጥ ምርትና አገልግሎቶች ይተዋወቁበታል።
#telegram #exibition #diaspora #Ethiopia #ኢትዮጵያ #DashenBank