#መልስ: ሰይጣን ሰዎችን ከሚጥልበት መሰናክሎች አንዱ ውዳሴ ከንቱ፣ ያልሆኑትን አድርጎ ማሳየት ነው።
በዚህም ብዙ መንፈሳውያን ተሰነካክለው ወድቀውበታል። አንድ ሰው ከሰዎች ሙገሳ ቢቀርብለት ''አቦ አቦ ካላንተ ሰው የለም" ቢባል ይህንን አመለካከት ለማቆም አይችል ይሆናል። ነገር ግን የራሱን ኃጢአት በማሰብ ሰዎች እንደገመቱት ጻድቅና ቅዱስ አለመሆኑን በመረዳት ራሱን ለንስሓ ማዘጋጀት ግን ትልቅ ጥበብ ነው።
ወንድማችን፦ የሰዎችን የውዳሴ ከንቱ ንግግር ለጆሮህ ስማው እንጂ ወደ ልብህ እንዲገባ አትፍቀድለት። ሰዎች ምንም ይበሉ ምን አንተ ቦታ ካልሰጠሃቸው በውዳሴ ከንቱ ተጠልፈህ ልትወድቅ ስለማትችል የምትሰማው ነገር ከልኩ ካለፈ ቦታ አትስጠው። በሌላ በኩልም ያልሆንከውን ነህ ብትባልም ለመሆን መጣር እንጂ ተስፋ ቆርጠህ መቀመጥ አይገባህም። ኃጢአትህ ባለመገለጡ ያልገለጠህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ለአለም ያልተገለጠውን በደልህን ለንስሓ አባትህ ተናዘዝ!
እግዚአብሔር ራሳችንን ወቅሰን እንጸጸት ዘንድ ይታገሰናል፤ በዚህ ትዕግስቱ ካልተመለስን ግን በደላችንን ለፍጥረታት ለፍጥረታት ሁሉ ይገልጥብናል። ኋላም የሚሸፍነው ማንም አይኖርም። የሆነው ሆኖ በአጉል ትኅትና አይገባኝም፣ እኔ ለዚህ አልበቃሁም እያልክ ራስህን ከቅድስና ሕይወት እንዳትለይ ተጠንቀቅ!
ሰይጣን ከንቱ እንደሆንክና ለምንም ነገር እንደማትበቃ አድርጎ በማሳየት የልብህን ሰላም ነሥቶ በውስጥህ ጭንቀት ፈጥሮ ከንሰሓና ከቅዱስ ቁርባን ሊያርቅህ ይችላልና። ስለዚህ "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ" የሚለው ስሜትህ ከገደብ አልፎ ከእግዚአብሔር ቤት እንዳይለይህ ትኅትናህን በልኩ አድርገህ በንስሓ ራስህን አስተካክል!
አቤቱ እኔስ እውነተኛውን እራሴን ሳውቀው ምንም ዋጋ በማያሰጠው ከንቱ ውዳሴ ለምን እጠለፋለሁ፤ አንተ የእውነት ጠራኸኝ እኔስ የእውነት መምጣት ለምን አቃተኝ፤ ሰዎች የደረቡብኝ የውዳሴ ካባ ጎተተኝ፤ እነሱስ ለክፋት አልነበረም ለኔ ግን ለጥፋት ሆነብኝ፥ ጌታ ሆይ አንተን ዘንግቼ ይጠቅሙኛል ብዬ በእጄ የያዝኳቸው፣ ያበረቱኛል ብዬ የተደገፍኳቸው፤ ለውበትም ያጌጥኩባቸው እንደ ባለማዕረግ በእራሴ የደፋኋቸው ለልቤ ስብራት መጠገኛ ለዕንባዬም ማባበሻ የማይጠቅሙ ከንቱ ናቸውና አቤቱ ከዚህ ክፉ ደዌ አድነኝ!
ከምሥጢሬን ላካፍላችሁ የተወሰደ
@Deaconchernet