Deacon Chernet


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤አሜን
2ኛ ጴጥ 3፡18
በተዋህዶ እምነታችን ፀንተን እንኑር !
ጥቆማ ወይም ጥያቄ ካላቹ በዚህ የተለግራም ቦት👉🏽https://t.me/Cher2112bot ይጠቀሙ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


#ምሥጢረ ጥምቀት

የማይታየውና የማይመረመረው እምላክ ከእመቤታችን ሰው ሆነ በሠላሳ ዓመቱ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ አዳምና ሔዋን ያጡትን ልጅነት ለመመለስ ስለሰው ልጆች ሁሉ የተጠመቀውን ጥምቀት የምናውቅና የምናምንበት ሦስተኛው አዕማድ ምሥጢረ ጥምቀት ነው።

“ወአሜሃ መጽአ አግዚአ ኢየሱስ ኀበ ዮርዳኖስ ከመ ይጠመቅ እምዮሐንሰ” ያንጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ በዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ማቴ. ፫፡፲፫ 3+13

በዚያን ጊዜም ዕድሜው የ3ዐ ዘመን ጎልማሳ ነበር። በ3ዐ ዘመኑ መጠመቁ አባታችን አዳምን ሲፈጥረው የ3ፀ ዘመን ጎልማሳ አድርጎ ነበር። አዳምም የ3ዐ ዘመን ሆኖ ተፈጥሮ የተሰጠውን ልጅነት በዲያብሎሰ አስነጥቆ ነበርና ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ የአዳምን ልጅነት ሊመልስለት በ3ዐ ዘመኑ በአደ ዮሐንስ በአፍላገ ዮርዳኖስ ተጠመቀ።

#በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቁም

ሀ. ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ ነው። “ምንተ ኮንኪ ባሕር ዘጎየይኪ ወአንተኒ ዮርዳኖስ ዘገባአከ ድኀሬክ“ አንቺ ባሕር የሸሽ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋካሽ የተመለሽ ምን ሆናችኋል ብሎ ቅዱስ ዳዊት ይጠይቃል

ለ. ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የዕዳ ደብዳቤ ጽፎ በዮርዳኖስ ቀብሮት ስለነበር ያንን ለመደምስስ። ጠላት ዲያብሎስ አዳምና ሔዋንን የዘላዓለም ባሮች አድርጎ በሁለት ዕብነ ሩካም ጽፎ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል ቀብሮት ነበር። በዮርዳኖስ የተቀበረውን፡ ከብር ይግባውና ጌታ ሲጠመቅ በሰውነቱ ረግጦ በአምላክነቱ አቅልጦ አጠፋው። በሲኦል የተቀበረውን በቀራንዮ ተሰቅሎ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ደመስሶታል። ቆላ- ፪:፲፬ 2፡14 ፩ጴጥ ፫፡፲፱ 3:19

ሐ. በብሉይ በዮርዳኖስ ወንዝ እየተጠመቁ ከሥጋ ደዌ ይፈወሱ አንደነበር የነፍሳችንን ደዌ ሊፈውስልን በዮርዳኖስ ተጠመቀ። ለምሳሌ ኢዮብ ንዕማን ፪ ነገ. ፭፡፲፬ (5:14)

#በውኃ መጠመቁ
ሀ. ትንቢት ስለአለ፡- “ጥሩ ውኃንም አረጭባችኋለሁ አናንተም ትጠራላችሁ“ ሕዝ. ፴፮፡፳፭ 36፥25
ለ. ጌታ ሲጠመቅ በማር ወይም በቅቤ ወይም በሌላ አላደረገውም በውኃ ተጠመቀ ምክንያቱም ውኃ ለድህው ለህብታሙ ለታላቅ ለታናሹ ሁሉ ይገኛልና። ይህን ያደረገው ለእኛ ነውና ስለዚህ የሰው ልጅ ሁሉ ለመዳን "በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም ሊጠመቅ ይገባዋል።”

አንድ ሰው አምኖ በሚጠመቅበት ጊዜ ካህናት በጸሎት ውኃውን ሲባርኩት ከጌታ ጎን የፈሰሰውን ማየ ገቦ ይሆናል። ዮሐ. ፲፱፡፴፬ 19፥34 በዚያን ጊዜም ከውኃና ከመንፈሰ ይወለዳል። ይህችም ሁለተኛ ልደት ትባላለች። አንደኛ ልደት ከእናት ከአባት አለና - ጌታም የነገረን ይህንን ነው፡፡ እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈሰ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው ከመንፈሰ የተወለደ መንፈሰ ነው። ዳግመኛ ልትወለዱ ያሰፈልጋችኋል ስላልሁ አታድንቅ ብሎ ለኒቆዲሞሰ እንደነገረው። ዮሐ.፩-፲፭ 3፥1-15

#በዮሐንስ መጠመቁ

ከብር ይግባውና ጌታችን የተጠመቀው በዘካርያሰና በኤልሳቤጥ ልጅ በቅዱሰ ዮሐንሰ እጅ ነው። የዚህም ምክንያት፡-

አንደኛ፡ ጌታችን ወደዚህ ዓለም መምጣቱ ለትሕትና ስለሆነ ነው ። “ዮሐንሰ ግን እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል እንጂ አንተም ወደኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር። ኢየሱስም መልሶ አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።” ማቴ ፫፡፲፬፡፲፭ (3፡ 14-15) ጽድቅም የተባከች ትሕትና ናት።

ሁለተኛ፡ ሰው ሁሉ ወደ ካህን ሄዶ መጠመቅ እንዳለበት ሲያሰረዳ ወደ ዮርዳኖስ መሄዱ በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈው “ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንሰ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ “ ማቴ ፫፥፲፫ 3:13 አምላክ ሆኖ ሳለ። ሰለምን ዮሐንሰን አንተ መጥተህ አጥምቀኝ አላለውም ለምን ጌታ እራሱ ሄደ? ይህም ለእኛ ትምህርት ነበር። ሰው ምንም ያህል የተከበረ ቢሆን ካህኑን ናና ቤቴ አጥምቀኝ እንዳይል ለአርአያና ለምሳሌ ነው። ማንም ቢሆን ወደ ቤተ ከርሰቲያን ሄዶ መጠመቅ እንዳለበት ሲያስተምረን ነው።

#ምሥጢር መባሉ፡-

አምላካችን በተጠመቀ ጊዜ ሰማይ ተከፍቶ አብ በደመና ወልድ በዮርዳኖስ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል መታየቱና *የምወደው ልጀ" ብሎ አብ የተናገረለት መንፈስ ቅዱስ የመሰከረለት ወልድ በተዋሕዶ አንድ መሆኑ ነው። ይህ አንዱ ወልድ ሁለት አይደለም አብ ልጄ ያለው ሌላ ከድንግል ማርያም የተወለደው ሌላ አይደለም። በበረት የተወለደው ሌላ ሰብአ ሰገል የሰገዱለት ሌላ አይደለም የተጠመቀው ሌላ አይደለም ጥምቀት የማያሻውም ሌላ አይደለም። አርሱ አንድ የሆነ አምላክ በፈጠረው በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ መጠመቁ ይህ ድንቅ ምሥጢር ነው።

በጸሎት ውኃው ተለውጦ ከጌታ ጎን የፈስስውን ውኃ ሲሆን በሥጋ ዓይን ስለማይታይ ምሥጢር ነበረ።
በመንፈሰ ቅዱስ የምንወለድበት ጊዜ ልክ ከእናታችን ከአባታችን ስንወለድ አንደማናውቅ በዚያን ስዓት ስለማንረዳ በመንፈስ የሚታወቅ በመሆኑ ምሥጢር ነው።

#በቀጣይ ምስጢረ ቊርባንን እናያለን


#ምሥጢረ ሥጋዌ

ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ያለአባት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆኖ ከወደቅንበት የኃጢአት ጉድጓድ (ሲዖል) አወጣን አዳነን ብለን ሰው መሆኑን የምንረዳበት እምነት ምሥጢረ ሥጋዌ ይባላል።

#ከማን ሰው ሆነ?

በነቢዩ ኢሳይያስ ፯፡፲፬ (7፥14) ሰለዚህ ጌታ ራሱ ምልከት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” ብሎ እንደተናገረ ሰው የሆነው ከድንግል ማርያም ነው። በሉቃስ 1፥27 "የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። ይላል።

ሰለዚህ እግዚአብሔር እምላክ የወደቀውን አዳምን ለማዳን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍሰን ነሥቶ ሰው ሆነ። ይህ ስው የሆነው አምላክ ነው። የሥጋን ባሕሪ ባሕርዩ ያደረገ የማይታየው የታየው የማይዳስሰው የተዳሰሰው ከእመቤታችን በተዋሐደው ሥጋ ነው ብሎ ማመን ምሥጢረ ሥጋዌን መረዳት ነው። መሠረታዊ ቃሉም በዮሐ.፩፡፩-፲፬ (1፥1-14) ያለው ነው። በመጀመሪያ ቃል ነበረ። ቃልም በእግዚብሔር ዘንድ ነበር። ቃልም እግዚእብሔር ነበር ብሎ “ቃል ሥጋ ሆነ” የሚሊውን የእግዚእብሔርን ከእመቤታችን መወለድ ይገልፃል።

#ሰው የሆነው ማነው?

አግዚአብሔር ነው፡- ዮሐ.፩፡፩-፫ (1፥1-3)
አምላክ ነው፡- ኢሳ. ፱፡፮ (9፥6)
ጌታ መድኃኒት ነው ፡- ሉቃስ ፪፥፰-፲፬ (2፥8-14)

ሰው የሆነው ከድንግል የተወለደው ሰማይና ምድርን የፈጠረ ብቻውን አምላክ የሆነ ጌታ መድኃኒት ኢየሱሰ ከርስቶስ ነው። ደገኛው ቅዱስ ጳውሎሰ እንዲህ ገልጾታል።

“ወእሙንቱ አበዊነ ወእምላዕሌሆሙ ተወለደ ከርስቶስ በሥጋ ሰብእ ዘውእቱ አምላከ ቡሩከ ለዓለመ ዓለም
“አባቶችም ከእነርሱ ናቸው፤ ከአነርሱም ከርሰቶሰ በሥጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው አሜን።" ሮሜ፱፡፭ (9:5)

#ለምን ሰው ሆነ?

አዳም በበደለው በደል የሰው ልጅ ሁሉ የሞት ሞት ተፈርዶበት ከአምላኩ ተለይቶ ገነት መንግሥተ ሰማያትን አጥቶ በኃጢአት ወድቆ ስለነበር ይህ የወደቀውን አዳምን ለማንሳት የሰው ልጅ ሁሉ ሕይወትን ያገኝ ዘንድ የዲያብሎስ ባርያ የነበረው ደካማው የሰው ልጅ ብርቱ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔርን ልጅነት ሥልጣን ያገኝ ዘንድ ወልድን ፍቅር ከሰማይ ሰቦት የመንግሥቱ ልጆች እንሆን ዘንድ ሰው ሆነልን።

“በእርሱ የሚያምን የዘላለም ሕይወት ኣንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እሰኪሰጥ ድረሰ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” ዮሐ ፫፡፲፮ (3:16)

“የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሐር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ለከ አንደ ልጆቹ እንሆን ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ” ገላ. ፬፥፬ (4፥4)

ስለዚህ የዘላለም ሕይወት እናገኝ ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ከኃጢአት በስተቀር የስውን ባሕርይ ባሕርዩ አድርጎ ያለመለወጥ ያለመቀላቀል ያለመከፋፈል ያለመለያየት በተዋሕዶ ሰው ሆነ።

ስለዚሀም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእመቤታችን ተወልዶ የሰው ልጅን ሁሉ አዳነ። ሰለዚህ አምላክ ሰው ሆነ ሰውም አምላክ ሆነ የሚለውን ምሥጢር በእምነት የተረዳ በጠንካራው ዐለት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

“በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃ አወጣን እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገናም በባርነት ቀንበር እትያዙ።”ገላ 5;1

ወልድ ሰው በመሆኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ያነሰ ወይም የበለጠ አይደለም። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ዘላለም ትክከል ነው። ብዙዎች የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስን ሰው መሆን ብቻ ያዩና ኃይሉንና እምላክነቱን ይክዳሉ ፪ጢሞ ፫፡፭ (3፥5) እርሱ ግን ዳኛ ፈራጅ ዘላለማዊ እምላክ ነው። በቸርነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን።

“ኢየሱስ ከርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘላለምም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ።” ዕብ.13+8

ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ የቅዱስ ባስልዮስ ወንድም፡ ከእመቤታችን ተወልዶ ስላዳነን የአብ ልጅ ወልድ ኢየሱስ ከርስቶስ እንዲህ አስተምሮናል፡-
በምድራዊ ልደቱ አባት አለው፡ በስማያዊ ልደቱም እናት አለችው አትበሉ፡ እርሱ በምድር አባት የሌለው ነው በሰማይም እናት የሌለችው ነው።

የከርስቶስን አካል ሁለት አታድርጉ ወደ ሁለት አካል ወደ ሁለት ባሕርይ ፈጽማችሁ አትለዩት ወልድን አንድ ወገን የተዋሐደውን ሥጋም አንድ ወገን አታድርጉ።

የማይለየውን ተዋሕዶውም ሊፈርስ የማይቻለውን አንዱን ትለዩ ዘንድ አትድፈሩ ሰው በሆነ በእግዚአብሔር ከመለኮቱ የተለየ ዕሩቅ ብእሲ (ለስም አጠራሩ ከብር ይግባውና እንዲሁ እንደ አንድ ሰው አምላክነት የሌለው) አንደሆነ አታስቡ አርሱ አንድ ብቻ እንደሆነ እመኑ እንጂ እርሱ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ ነው።

ከዘመን አስቀድሞ በቅድምና የነበረ ዛሬ ሰው የሆነ አምላክ ይህ ነው። አርሱም መለኮቱ ከትስብእቱ ትሰብአቱ ከመለኮቱ ሳይለይ ለዘለዓhም ይኖራል።

#በቀጣይ ምስጢረ ጥምቀትን እናያለን


ምሥጢረ ሥላሴ

ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢር አንደኛው ይህ ምሥጢረ ሥላሴ ሲሆን ይህም የአግዚአብሔር የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የሚገለጽበት ነው።

* አንድነቱ፡- በመለኮት በባሕርይ በህልውና በፈቃድ በአገዛዝ ይህን ዓለም በመፍጠርና በማሳለፍ አንድ ነው።

*ሦስትነት፡- በስም በግብር በአካል በኩነት

#በስም፡-አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ ፡፡ ማቴ 28:19

#በግብር፡- አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ ነው። ዮሐ. ፩፡፳፭ (1፥25)

#በአካል፡- ለአብ ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክ አለው። ለወልድም እንዲሁ ለመንፈስ ቅዱስም አንዲሁ

#በኩነት፡-አብ ልብ ነው። ወልድ ቃል ነው፣ መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር በስም በአካል በግብር በኩነት ሦስት ነው ብንልም በመስኮት በህልውና በባሕርይ በአገዛዝና በመሳሰሉት አንድ ስለሆነ አንድ አምላክ ተብሎ ይታመናል ይጠራል እንጂ ሦስት አማልክት አይባልም። ከዚህም የተነሣ ሥካሴ ሦስት ሲሆኑ አንድ አንድ ሲሆኑ ሦስት በመሆናቸው ይህ ምሥጢር ተባለ ለሚያምን ብቻ የሚገለጽ ምስጢር።

#ለምሳሌ:-
- አዳም አንድ ነው ሦስት ሊሆን አይችልም።

- ኣብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ደግሞ ሦስት ናቸው አንድ ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚሀም ቅድስት ሥካሴ ሰንል “ቅድስት” ልዩ -ሥላሴ" ሦስትነት ሲሆን ልዩ የሆነች ሦስትነት ብለን እናምናለን።

* በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች

#አንድነት ፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ የሚለው ቃል አንድነቱን ያሳያል ዘፍ. ፩፡፩(1:1)

#ሦስትነት፡- “የጌታችን የኢየሱስ (ወልድ) ከርስቶሰ ጸጋ የአግዚአብሔርም (አብ) ፍቅር የመንፈስ ቅዱሰም ኅብረት ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን።” 2ቆሮ 13:14 ይህ ቃል ሐዋርያት ሕዝቡን የሚባርኩበት ቃል ነው ይህም ሰመ ሥካሴ ነው።

#አንድነትና ሦስትነት፡- እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር።” ዘፍ1፥26 “እግዚአብሔር አለ” ሲል አንድነቱን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር የሚሉት ቃላት ሦስትነቱን በግልጽ ያመለክታሉ።

#ሌሎች ምሳሌዎችን እንመልክት
1. ፀሐይ ፡-
ሀ/ ከበብ (ቅርፅ) አላት
ለ/ ብርሃን አላት
ሐ/ ሙቀት አላት

አንድ የሆነችው ፀሐይ ክበብ ብርሃን ሙቀት ስላላት ሦሰት ፀሐዮች አትባልም እንድ ፀሐይ እንጂ። በክበቡ አብ ይመስላል በብርሃኑ ወልድ ይመሰላል በሙቀቱ ደግሞ መንፈሰ ቅዱስ ይመሰላል። ኣብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ቢባሉም እርሱ ግን አንድ ፈጣሪ አምላከ ነው።

“ኣብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ ወመንፈስ ቅዱስ ፀሐይ ፩ዱ ውእቱ ፀሐየ ጽድቅ ዘላዕለ ኩሉ

“አብ ፀሐይ ነው። ወልድ ፀሐይ ነው። መንፈስ ቅዱስም ፀሐይ ነው፡ ከሁሉ በላይ የሚሆን አንድ የእውነት ፀሐይ ነው“ ቅዳሴ ማርያም

2. ነፍሰ፡- ሦስትነት አላት
ሀ/ ለባዊነት
ለ/ ነባቢነት
ሐ/ ሕያዊነት

ይህ ማለት ነፍስ ለባዊት ናት (ልብ) ነባቢት ናት (ቃል) ሕያዊት ናት (እስትንፋስ) አሁን አንደምታዩት ልብ የምታደርግ የምትናገር ሕያው የሆነች ብለን ብንመለከትም ሦስት ነፍሳት ሳይሆን አንድ ነፍስ ብቻ ነች። በለባዊነት አብ ይመስላል። በነባቢት ወልድ ይመስላል በሕያዊነት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ይመስላል።አብ ልብ ነው፡ ወልድ ቃል ነው፡ መንፈስ ቅዱስ አስትንፋስ ነው። ልክ ነፍስ ሦስትነት ሲኖራት አንድ ነፍስ አንደምንል ሥላሴም ሦስት ሲሆን አንድ ነውና አንድ እምላክ ብለን እናምናለን።

#በቀጣይ ምስጢረ ሥጋዌን አጠር አጠር አድርገን እናያለን

ለሌሎች በማጋራት{share} ክርስትያናዊ ግደታዎን ይወጡ!




አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን እምነቷን የምትገልጽበት ለሰዎችም የምታስተምርበትና የምትመስከርበት አምስት እዕማደ ምሥጢራት አሏት።

"ናሁ ኅቡዓ ነገረ እነግረከሙ” እነሆ ኅቡዕ (ምሥጢር) እነግራችኋለሁ ፩ ቆሮ: ፲፭: ፶፩ (15፡51) እንዳለ እነዚህ አምስቱ ምሥጢራት አምስቱ ኅቡዓት ተብለውም ይነገራሉ፡፡ አምሰቱም ነገረ መለኮት ናቸው።

#አምስት፡- ቁጥራቸውን ይገልፃል

#አዕማድ፡- ማለት ምስሶዎች ማለት ነው። አንድ ቤት ሲሠራ ሊቆምና ጠንካራ ሊሆን የሚችለው በአዕማድ (ምሰሶዎች) ነውና። ለሃይማኖታችንም መሠረታዊ ምስሶዎች አሏት።

#ምሥጢር፡- ለወዳጅ የሚገለጽ ነገር ሲሆን ለሚያምኑ ሁሉ የሚገለጽና በእምነት ብቻ የሚረዱት በመሆኑ ምሥጢር ይባላል።

አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የሚባሉትም፡-

1.ምሥጢረ ሥላሴ
2.ምሥጢረ ሥጋዌ
3.ምሥጢረ ጥምቀት
4.ምሥጢረ ቊርባን
5.ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው።

አንድ ክርስቲያን እነዚህን ጠንቅቆ ከተረዳ መሠረቱ ጠንካራ ዐለት ይሆናል። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ.፲፬:፲፱ (14፥19) ላይ "ወባሕቱ በቤተ ከርስቲያን እፈቅድ ኀምስቲ ቃላተ እንግር በልብየ ከመ ለባዕዳንሂ እምሃር እስመ ይኄይስ እምእእላፍ ቃል በነገረ በሐውርት” “አምስት ቃላት በእእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ"ብሎ የአምስቱን አዕማደ ምሥጢር በአውነት ለምአመናን ያስተምር የነበረው።

#በቀጣይ ግልጽ በሆነ መንገድ አጠር አጠር አድርገን ምሥጢረ ሥላሴን እናያለን


#አስተርዮ_ማርያም

የማይታየው የታየበት፣ የራቀው የቀረበበት፣ የረቀቀው መለኮት በገዘፈ ሥጋ ማርያም የተገለጠበት፣ የወልድ ልጅነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ የተመሰከረበት፣ በልደቱ፣ በጥምቀቱ አንድነት በሦስትነት እንዲሁም መለኮት በሥጋ ሥጋም በመለኮት በተዋሕዶ ተገልጦ ምሥጢሩ ገሃድ የሆነበት የመገለጥ የመታየት ጊዜ የሆነው ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ዘመነ አስተርዮ እየተባለ ይጠራል፡፡

በዚሁ በዘመነ አስተርዮ መካከል የሚገኝ ስለሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “በዓለ ዕረፍት አስተርዮ ማርያም” እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ አስተርዮ ማርያም የምንለው ታላቅ በዓል እናታችን እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችበት መታሰቢያ ሲሆን ቀኑም ጥር ፳፩ ነው፡፡

ሰማይና ምድር የማይወስኑትን የወሰነች፣ ሞትን በሞቱ የመሻር ሥልጣን ያለውን፣ ዓለምን በመዳፉ የጨበጠውን የወለደች ክብርት ቅድስት እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም የምታርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ይኸውም ጥር ፳፩ ቀን በዕለተ እሑድ በ፷፬ ዓመቷ፣ በ፵፱ ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ነግሯት በልጇ መቃብር ሆና ጸሎት ታድርስ ነበር፡፡

እንዲህም ብላ ጸለየች፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሐዋርያትን ሁሉንም፣ ነፍሳቸውንም የለየሃቸውን አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋንና የሙታን አምላክ ነህና›› አለች፡፡ (የጥር ፳፩ ስንክሳር)

በዚህ ጊዜ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ከኤፌሶን አመጣችው፤ ምስጋናም አቀረበላት፤ ሁሉም ሐዋርያት የሞቱትም ከመቃብር ተነሥተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ እንዲህም ስትል ጠየቀቻቸው፤ ‹‹ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፤ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ሰማችሁ?›› አለቻቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ‹‹ወደ አንቺ እንድንመጣ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፤ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወደ አንቺ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አላት፡፡

በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደ እርሷ መጣ፡፡ (ጥር ፳፩ ስንክሳር)
እንዲህም አላት ‹‹እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጥቻለሁ›› አላት፡፡ እርሷ ግን ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜህ፤ በድንግልና ወልጀህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡

በዚህ ጊዜ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ አሳያትና ‹‹እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ሁሉ ነፍሳት መዳን ምክንያት (ቤዛ) ይሆናቸዋል›› አላት፡፡ ‹‹እነዚህን ሁሉ ከማርክልኝስ ይሁን›› አለች፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥጋዋን ከክብርት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በይባቤ መላእክት በክብር ነፍሷን ዐሳረጋት፡፡ (መዝገበ ታሪክ ቁጥር አንድ ገጽ ፻፶፭፣ ጥር ፳፩ ስንክሳር)

የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!!!

#ማህበረ_ቅዱሳን


ኢትዮጵያና ሕገ ኦሪት

አሞጽ ፱፡፯ (9፡7) "የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለአኔ እንደ
ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር" ይህም ምን ይገልጽልናል ብሎ
ለሚጠይቅ ነገሩ እንዲህ ነው ዛሬ አሰራኤል ታቦቱ የላትም።
የዚህ ምሥጢር ባለቤት ግን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ናት።

በአጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍጥረት ጀምሮ የብሉይ ኪዳንን እምነትና ሥርዓት ጠብቃ አስጠብቃ እግዚአብሔርን በማምለክ የጸናች አገር ናት፡- ቅድመ ክርስትና ይህ የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት እየተሠዋባት የነበረች አገር እንደነበረች በሁሉም የአገሪቷ ከፍል ያለ የሃይማኖት መገለጫ የታሪከ ማስረጃ የባህልም ምስከርነት አለ።

ለምሳሌ፡- በመላው ኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት ይቀርብባቸው የነበሩ የንዋየ ቅድሳት ምስክሮች አሉ። ኢትዮጵያ በዚያ ዘመን ለአምላኳ መሥዋዕተ ቁርባን ታቀርብ ነበር። ነቢዩ ሶፎንያስ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ “ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱልኝ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ ቁርባኔን ያመጡልኛል” በግእዙ እንዲህ ይለዋል። “እምነ ማዕዶተ ፈለገ ኢትዮጵያ ያመጽኡ ሊተ መሥዋዕተ” የዚህም ትርጓሜ “ከኢትዮጵያ ወንዝ ጀምሮ መሥዋዕቱን ያመጡልኛል።“ ሶፎ ፫፡፲ (3:10)

እንዲህ ባለ ሁኔታ ኢትዮጵያ ለአንድ አምላከ እየሰገደች እርሱን ብቻ እያመለከች ሀገረ እግዚአብሔር ሆና አምላክ ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ተጠምቆ፣ በመሰቀል ተስቅሎ፣ ደሙን እፍስሶ፣ ሥጋውን ቆርሶ፣ ዓለምን ሁሉ ያድናል እያለች የተቆጠረው ሱባዔ የተነገረው ትንቢት ይፈጸማል አምስት ሺህ አምስት መቶ የኃጢአት የጨለማ ዘመን ያበቃል እያለች የነቢያትን ትንቢት በመጋራት በእምነት ፀንታ ስትኖር ዘመኑ ሲፈፀም በትንቢቱ መሠረት ጌታችን አኛን ለማዳን ሰው ሆነ ተዋሕዶ ሃይማኖት በዚህ ተጀመረች ኢትዮጵያም የመጀመሪያዋ ከርስቲያን ሀገር ፤ለመሆን በቃች።

#ከላይ ኢትዮጵያና ሕገ ወንጌል (ክርስትናን) አለ

ለተፈጠረው ቅደምተከተል ይቅርታ እንጠይቃለን




ኢትዮጵያና ሕገ ወንጌል (ክርስትና)

ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪት ሰለማመኗ የነገረን መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ስለከርስትናውም መጽሐፍ ቅዱሰ አንዲህ ይላል። የሐዋርያት ሥራ ፰፡፳፮ (8፥ 26) የጌታም መልአከ ፊሊጶስን ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ አለው። ተነሥቶም ሄደ።

እነሆም ሕንደኬ በመጠሪያ ስሟ ጌርሳሞት የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥች አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘቧም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳኬም መጥቶ ነበር። ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያሰን መጽሐፍ ያነብ ነበር። ፊሊጶሰም አፉን ከፈተ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ሰለ ኢየሱስ ወንጌል ሰበከለት ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ አጠመቀውም።

እንግዲህ ልብ እንበል
* ጃንደረባው አማኝ ነበር
* ወደ ኢየሩሳሌም የሄደው ሊሰግድ ነበር
* የኢሳይያስን ትንቢት ያነብ ነበር
እነዚህ ከላይ ያየናቸው ማሰረጃዎች ኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳን እምነት አማኝ የነበረች ሀገር መሆኗን የሚገልጽ ነው።

ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ሰንመለከት
ፊልጶስ ስለ ኢየሱሰ ወንጌል ሰበከለት ጃንደረባው ኢየሱስ የአግዚአብሔር ልጅ አንደሆነ አመነ ተጠመቀ እነዚህ ማሰረጃዎች ደግሞ የክርስትናን እምነት የሚገልጹ ናቸውና ኢትዮጵያ ከ33 ዓ.ም ጌታ ከሞት ተነሥቶ ካረገ በኋካ ወዲያው ክርሰትናን_እንዳመነች የሚያሳይ የእግዚእብሔር ቃል ነው።

ጃንደረባው በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀዋል ይልቁንም ለመላው አፍሪካም ሐዋርያ ሆኗል። “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” መዝ. ፷፯፡፴፩ (67፥31) ተብሎ የተነገረው የነቢዩ ዳዊት ትንቢታዊ መዝሙር በዚህ እንደተፈጸመ እንገነዘባለን። ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ከርስትና በኢትዮጵያ እየተስፋፋች የወለደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ይሰበክባት ጀመር።

ይልቁንም ደግሞ በ33ዐ ዓ.ም ክርስትና የመላው የኢትዮጵያ እምነት በመሆን ብሔራዊ እምነት ሆነ፡፡ ከዛም በዓለም ላይ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ከርስቲያን ሀገር ሆነች።

ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!

#በቀጣይ አምስቱን አዕማደ ምሥጥራት አጠር አድርገን ተራ በተራ እናያለን




ወይንኬ አልቦሙ
የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም

በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤

ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።

የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፡— የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም፡ አለችው።

ኢየሱስም፡— አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም፡ አላት።

እናቱም ለአገልጋዮቹ፡— የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፡ አለቻቸው።

አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።

ኢየሱስም፡— ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው፡ አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው፡ አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።

አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።

አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፡—

ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል፡ አለው።

ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ። (ዮሐ 2፥1- 11)

የሰውን ችግር ተረድታ ለልጇ የምታሳስብ፣ ልመናን የምታቀርብ፣ መልስ የምታሰጥን እናት የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁንልን።

ልጆቿ እንድንሆን የረዳን፣ ፍቅሯንም በዕድሜ ዘመናችን ያበዛልን፣ ምስጢሩንም የገለጸልን መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ለዘለዓለም የከበረ፣ የተመሰገነ ይሁንልን።

አማላጅነቷ፣ ጸሎቷ፣ ፍቅሯ፣ በረከቷ ከሁላችንም ጋር ጸንቶ ይኑር!

አሜን!


ከተራ_ምንድን_ነው?

እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ!

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡


ኢትዮጵያና ሕገ ልቡና

ሕገ ልቡና ማለት ሕገ ኦሪት በሙሴ አማካኝነት እግዚአብሔር ለሕዝቡ እሰከሰጠበት ጊዜ ድረስ ያለው የሰው ልጅ ይጠቀምበት የነበረ ዛሬም የሚሠራ ያልተፃፈ ሕግ ወይም የአእምሮ (ጠባይዕ) ነው።

ይህ የአእምሮ ጠባይዕ ለሰው ልጆች በእግዚአብሔር አምላክ የተሰጠው ታካቅ ፀጋ ስለሆነ ከፉንና ደጉን ጽድቅና ኩነኔውን ይለዩበት ዘንድ የሚያስችላቸው የኅሊና ሕግ ነው።
ለኅሊና መገዛት መልካም ነው።

ይህን የልቡና ሕግ በኛ ውስጥ የቀረፀው ገና ሲፈጥረን እንደሆነ ማስተዋል ይገባናል። ”እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እሰትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍሰ ያለው ሆነ” ዘፍ፡ ፪፡፯ (2¹7)

“እንግዲህ ይህች ሕያዊት የሆነች ነፍሳችን ናት የፈጠራትን የእግዚእብሔርን ትእዛዝ ሰለምትረዳ እኛም በእውነተኛ መንገድ እንድንሄድ የምትጠራን ይህም ሕገ ልቡና ነው።
ከብር ምስጋና ይግባውና አምላካችን ኢየሱሰ ክርስቶሰ በኦሪትም በወንጌልም የነገረን ይሀንን ነው።

“አፍቅሮ ለእግዚአብሔር አምላክከ በኵሉ ልብከ፡ ወበኵሉ ነፍሰከ ወበኵሉ ሐይለከ፡ ወበኵሉ ሕሊናከ"
“እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፡ በፍጹም
ሰውነትህ፡ በፍጹም ኃይልህም፡ በሐሳብህም ሁሉ ውደደው ዘዳ (6:10) ሉቃ ፲:፳፯(10:27)

እንግዲህ ይህንን ያሀል ስለ ሕገ ልቡና ካየን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ ሕግ መሠረት እንደ ተጠቀመበትና አምላኩን እንዳመለከበት ብዙ ግልፅ ማሰረጃዎች አሉ ሰለዚህ ኢትዮጵያ እግዚእብሔርን የምታውቀው በኦሪት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በፊት ከፍጥረት ጀምሮ ነው፡፡

ምሳሌ ፡-
ሕገ ኦሪት የተሰጠው በሙሴ ነው ሙሴ ሕግን ከመቀበሉ በፊት እግዚአብሔርን አማኝ ነው የፈርዖንን ቤት ሹመት የናቀው በእምነት ነው። ዕብ. ፲፩፥፳፫-፳፰ (11፥23-28)

ይህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያገባት ሚሰቱ ኢትዮጵያዊት እንደሆነች መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘኁልቍ ፲፪፡፩ (12*1) ይገልፃል። ይህች የሙሴ ሚሰት ሲፓራ እግዚአብሔርን ከሚያምን ቤተሰብ የተወለደች ነበረች። ይልቁንም አባቷ የእግዚአብሔር ካህን ነበረ።

ይህ የሙሴ አማት የሲፓራ አባት ዮቶር በሌላ ስሙ ራጉኤል የተባለው ኢትዮጵያዊ የእግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ እንዲህ ይላል ዘጻ ፲፰፡፲፪ (18፡12) እግዚአብሔርንም እንዲህ እያለ ያመሰግን ነበር ዘጸ ፲፰፡፲ (18፡10) እንግዲህ ይሀ የሚገልጽልን ኢትዮጵያ ከሕገ ኦሪት በፊት በሕገ ልቡና ለአምላኳ እንደ አቤል እንደ ኢዮብ መሥዋዕት የምታቀርብ የእግዚአብሔር ሀገር መሆኗን ነው፡፡ ታላቁን ሊቀ ነቢያት ሙሴን የማታምን የካሀነ ጣዖት ልጅ ያገባ ብሎ ማሰብ አላዋቂነት ከመሆኑም በላይ የሙሴን ክብር ዝቅ ማድረግ ነው።

ንግሥተ ሳባ ወይም ንግሥት አዜብ ተብላ የምትጠራው ኢትዮጵያዊት ንግሥት ማክዳን ብንመለክት እግዚአብሔርን ማመን የጀመረችው ኢየሩሳለም ሄዳ ከመጣች በኋላ ሳይሆን ከመሄዷ በፊት አስቀድሞ በሕገ ልቡና ፈጣሪዋን የምታውቅ መሆኗን የእግዚአብሔር ቃል ይመሰከርልናል። ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና ሀገረ እግዚአብሔር ሰለሆነች ንግሥስቲቷም ወደ ኢየሩሳለም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን የሄደችበት ምክንያት በተመሳሳይ እምነት ያለች እሰራኤልን በሰሎሞን ምከንያት ያገኘችውን በረከት ለመመልከትና አግዚአብሔርን ለማመሰገን ነበር።

“አንተን የወደደ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠሀ
አምላክህ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን“ ፩ነገ ፲፡፱ (10፡9) በማለት ምስክርነቷን ገልጻለች። ይህን ማለቷ ንግሥቲቷ ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን ታውቀውና ታመልከው ስለነበር ነው። ለዚህም ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ለእምነት ምሳሌ አድርጎ በወንጌል ያስተማረን አንዲህ ብሎ

“ንግሥተ እዜብ ትትነሣእ አመ ዕለተ ደይን ወትትፋታሕ ምስለ ዛ ትውልድ ወታስተኀፍራ እስመ መጽአት እምአጽናፈ ምድር ትስማዕ ጥበቢሁ ለሰሎሞን“

“ንግሥተ እዜብ በፍርድ ቀን ተነሥታ ከዚህ ትውልድ ጋር ትፋረዳለች፡ ታሳፍራታለች፡ የሰሎሞንን ጥበብ ትሰማ ዘንድ ከምድር ዳርቻ መጥታለችና ሲል መሰከሮላታል።” ማቴ ፲፪፡፵፪ (12፡42) ሉቃ ፲፩፡ ፴፩ (11:31)

ንግሥተ አዜብ ወደሀገሯ በተመለሰች ጊዜ ሀገራችን ያን ጊዜ ሕገ ኦሪትን ተቀብላ ሃይማኖተ ኦሪትን ብሔራዊ እምነት አድርጋለች፤ ቀድሞ ያለውንም አጽንታለች። ይህም የሚፈጸመው በቃል ኪዳኑ ታቦት ነውና ከንጉሥ ሰሎሞን በወለደችው በቀዳማዊ ምኒልከ ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ ገባች።

#በቀጣይ ኢትዮጵያና ሕገ ኦሪትን - ከሙሴ አስከ ዮሐንስ መጥምቅ ያለውን እንመለከታለን!




ሦስቱ ሕግጋት

ሕገ ልቡና - ከአዳም እስከ ሙሴ

ሕገ ኦሪት - ከሙሴ አስከ ዮሐንስ መጥምቅ

ሕገ ወንጌል - ከዮሐንስ መጥምቅ እስከ ምጽአት

”ኦሪትኒ ወነቢያትኒ አሰከ መጥምቁ ዮሐንስ እምትካት ስበኩ በእንተ መንግሥተ አግዚአብሔር”

“ኦሪትም (ሕግ) ነቢያትም ከጥንት ጀምሮ አስከ ዮሐንስ ድረስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አሰተማሩ።” ሉቃ፡፲፮፡፲፮(16:16)

እግዚአብሔር አምላካችን የፈጠረውን የሰውን ልጅ ወደ ሕይወት ይመልስ ዘንድ በተለያዩ ዘመናት አርሱን የሚያውቁበት ለአርሱም የሚገዙበትን መንገድ ሰጥቶታል። አነዚሀም ሕገ-ልቡና፣ ሕገ-ኦሪት እና ሕገ ወንጌል ናቸው፡፡

የሰው ልጅ ፍጥረት ሁሉ አምላኩን ለማወቅ እነዚህ ሕግጋት ይገልጹለታል ከአነዚህ የወጣ የለም። ያለ ሕግ የሚሠራ ሁሉ ያለ ሕግ ይቀጣልና፡፡ የሚገርመው ነገር እነዚህን እሟልታ በዓለም ላይ ያለች ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡

በሦስቱም ሕግጋት አግዚአብሔርን እያመለከች በመኖሯ አምልኮተ እግዚአብሔርም ስላልተቋረጠባት ቅዱስ ዳዊት ስለዚህም ነበር
“ኢትዮጵያ ታበጽሕ አደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር”
“ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች “ መዝ- ፮፯፡፴፩ (67፡ 31) ያለው!


#በቀጣይ ኢትዮጵያና ሕገ ልቡናን እያለን ሦስቱንም ሕግጋት ተራ በተራ ግልጽ በሆነ መንገድ እንመለከታለን


ተዋሕዶ

ተዋሕዶ የቃሉ ትርጉም ግእዝ ሲሆን የሚያበሥረንም የአምላካችን የአግዚአብሔርን ሰው የመሆን ምሥጢር ነው። ይህም ገና ያኔ በኦሪት ዘፍጥረት ፫፡፳፪ (3:22) “አግዚብሔር አምላክም አለ አነሆ አዳም መልካምንና ከፉን ለማወቅ ከአኛ አንደ አንዱ ሆነ” የሚለው አምላካዊ ቃል የተፈጸመበት የሰው ልጅ የመዳን ዜና ነው።

ተዋሕዶ ስንል ማን ከማን ተዋሐደ?

በዮሐንስ ወንጌል ፩፡ ፲፬ (1፥14) ላይ "ውአቱ ቃል ሥጋ ኮነ”
ያ ቃል ሥጋ ሆነ ይለናል ያ ቃል የተባለው አግዚአብሔር ነው።

“ሥጋ” የተባለው ደግሞ ሰው ነው።ከዚህ የወንጌል ምሰጢር የተነሣ ተዋሕዶ ማለት አካላዊ ቃል የተባለ አግዚአብሔር ወልድ ሥጋ ከተባለ ሰው ያለመለየት፣ ያለመቀላቀል፣ ያለድማሬ አንድ ሆነ። በተዋሕዶ ከበረ ስለዚህ አምካካችን እግዚብሔር እኛን ለማዳን ሲል ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ።

ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ ስንል የአሷን ባሕርይዋን ባሕርይ አደረገ። ሥጋም የአምላክን ባሕርይ ባሕርዩ አደረገ።

ይህ ምን ማለት ነው?

አካላዊ ቃል አግዚአብሔር፡- አይዳበሰም፣ አይታይም፣ አይጨበጥም፣ አይዳስስም፣ አይበላም፣ አይጠጣም፣ አያንቀላፋም፣ አይሞትም እነዚህ ሁሉ የሚሰማሙት ለሰው (ለሥጋ) ነው። አምላካችን ከድንግል በተወለደ ጊዜ ግን በተዋሕዶ የስውን ባህርይ የራሱ አደረገ።

በአጭሩ የሠራዊት ጌታ አግዚአብሔር ካለ አባት ከአመቤታችን ተወልዶ ሥጋን ተዋሕዶ (3ዐ) በሠላሳ ዘመኑ ተጠምቆ በቀራኒዮ ተሰቅሎ በጐልጐታ ተቀብሮ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ዐረገ በተዋሐደው ሥጋ ዳግም ለፍርድ ይመጣል “ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ አንዳያችሁት አንዲሁ ይመጣል“ ሥራ. ፩:፲፩ (1:11) ሥጋን ለብሶ አንዳረገ አንዲሁ ይመለሳል በመንግሥተ ሰማያት ለዘላለም ይኖራል ብሎ ማመን እውነተኛ የተዋሕዶ እምነታችን ነው።

የማይመረመር የማይለወጥ ቃል የሚለወጥ ሥጋን ተዋሐደ መለወጥ ይሰማማው የነበረ ሥጋን የማይለወጥ አደረገው። ሰለዚህም በተዋሐደው በመዋቲ አዳም ሥጋ ተገለጠ የማይለወጥ ባሕርይ ያለው ቃል የሚለወጥ ባሕርይ ባለው ሥጋ ሞተ በፍዳ የተያዙትን በወንጌሉ አዳናቸው

ሃይማኖተ አበው።

ስለዚህም ወገኖች ሆይ:- አምላካችን በደሙ የመሠረተልንን የነጻች እምነታችንን እሰከ መጨረሻ ካፀናን የከብሩ ወራሾች የስሙ ቀዳሾች አድርጎ በከብር ያኖረናል። ”ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያሰብ _ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከለች ፍሬዋን በየጊዜው አንደምትሰጥ ዛፍ ይሆናል።” መዝ.፩፡ ፪ (1፥2)

የመጀመሪያ አምነታችንን አሰከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ የከርሰቶሰ ተካፋዮች እንሆናለን" ዕብ ፫፥፲፬(3:14)

ይህ የቅዱሰ ጳውሎሰ ቃል በአምላካችን ስው መሆን (ተዋሕዶ) ያገኘነውን የልጅነት ፀጋ ያሳያል።ከፅንሰታችን እሰከ ዕለተ ሞትታችን ኋላም እሰከ ዕለተ ምጽእት በዚች ተዋሕዶ ሃይማኖት ጸንተን የቀደመች ልጅነታችንን ብንጠብቅ ከከርሰቶሰ ጋር አንድ እንሆናለንና።

ተዋሕዶ የአግዚአብሔር ሰው የመሆን ምሥጢር ነው። ከድንግል ሰው የሆነው ቃል የተባለ እግዚአብሔር ወልድ እርሱ አምካክ ነው። ሰው በመሆኑ ከእምላክነቱ እንዳች አልጎደለውም።

ተዋሕዶ የቃለ እግዚአብሔር ከአመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ የመንሣት (የመዋሐድ) ምሥጢር ታላቅ ነው። እርሱ የዳዊት ልጅ አንደሆነ አንዲሁ የዳዊት ፈጣሪ ነው። ከአብርሃም ዘር እንደተገኘ እንዲሁ ከእብርሃም በፊት ነበረ።

ማቴ. ፩፡፩ ፳፪፡፵፩: ፵፭ (22፡41-45) ዮሐ ፰:፶፰(8:58)

@Deaconchernet


ኦርቶዶክስ

ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል የግሪከ ቃል ሲሆን “ኦርቶ“ (ኦርቶስ) ማለት ቀጥ ያለ ማለት ሲሆን “ዶከስ” ማለት ደግሞ እምነት ማለት ነው። ስከዚህ ኦርቶዶክስ ማለት ቀጥ ያለ፣ የጸና፣ የቀና እምነት ማለት ነው።በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን እንደተገለጸልን ቀጥ ያለ እምነት ወይም እውነተኛ ሃይማኖት ተብላ በእምላካችን የተመሠረተችው ኦርቶዶከስ ተዋሀዶ ናት። ቀድሞ በነቢዩ በኤርምያስ የቀደመችው መንገድ ብሎ ያናገረ ጌታ በመዋዕለ ሥጋዌው ባስተማረን ወንጌል ጠባቢቱ በር ጠባቢቱ መንገድ ብሎ ኦርቶዶከስ የሕይወት መንገድ መሆኗን እስተምሮናል። መሥርቷታልም።

“እግዚእብሔር እንዲህ ይላል ። በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፡ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፡ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእስዋም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡ እነርሱ ግን እንሄድባትም አሉ።” ኤር ፮፡፲፮ (6፡16)

“በጠበበው ደጅ ገቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው። ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና። የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው ማቲ ፯:፰፫-፰፬ (7:13-14)

ከሁለቱ ጥቅስ ልብ የምትሉት ነገር ብዙዎች ይህችን አውነተኛ መንገድ አንደማይቀበሏት ነው። ከሐድያን መናፍቃን የተበረዘና የነቀዘ እምነት እንዲሁም ከወንጌል ውጪ የሆነ የፍልስፍናን ትምህርት ወደ ቤተ ከርስቲያን ለማስገባት በሚጥሩበትም ጊዜ ቅዱሳን አባቶች 318ቱ ሊቃውንት አርዮስንና መሰሎቹን አውግዘው እኛ እሱ ጌታችን የመሠረተልንን ነቢያት ትንቢት የተናገሩላትን፣ ሐዋርያት የስበኩላትን ፣ሰማዕታት የሞቱላትን ቀጥ ያለች እምነት ይዘን እንሄዳለን ብለው ሥርዓት ስለደነገጉ እምነታችንም ኦርቶዶከስ ተብላ ትጠራለች።

“የአግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምስሉአቸው። ኢየሱስ ከርስቶስ ትናንትና ዛሬ አስከ ዘላለም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ” ዕብ.፲፫፡፯ (13፥7)

@Deaconchernet


የመመኪያችን ዘውድና የንጽሕናችን መሠረት

ክርስቶስ ተጸነሰ - ተወለደ ስንል ለዚህ ሁሉ ምሥጢር ማካተቻና የድኅነታችን መጀመሪያ : የመመኪያችን ዘውድና የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናትና ከፈጣሪ ቀጥሎ ታላቅ ክብር : ምስጋና : ስግደትና ውዳሴ ለእርሷ ይገባታል። መድኅናችን ክርስቶስ ያዳነን በእርሷ ምክንያት ነውና።

ሠለስቱ ምዕት ይህንን ምሥጢር ሲያደንቁ እንዲህ ብለዋል፦

• በሥጋ ማርያም ጌታ ተጸነሰ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ተወለደ
• በሥጋ ማርያም ጌታ አደገ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ተጠመቀ።
• በሥጋ ማርያም ጌታ አስተማረ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ተሰቀለ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ሞተ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ተነሳ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ዐረገ
• በሥጋ ማርያም ጌታ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ዳግመኛ በሕያዋንና ሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድ ከመለኮቱ ኃይል ጋር ይመጣል። (መጽሐፈ ቅዳሴ)

በዚያውም ላይ ለዘለዓለም ድኅነት የምንመገበው የጌታ ሥጋና ደም መለኮት የተዋሐደው የድንግል ማርያም ሥጋና ደም ነው።

ለድንግል ማርያም ክብርና ውዳሴ ከስግደት ጋር ይሁን!

የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ክርስቶስ በርሕራሔው ይማረን። ከበረከተ ልደቱም ያሳትፈን።

"እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህ ሲል "የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።" ይህም ሁሉ የሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ በነቢይ የተነገረው ይፈፀም ዘንድ ነው ፤ እንዲህ ሲል፦ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።ማቴ. ፩፥፳-፳፫

ከዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ


#ቅዱስ_አግናጥዮስ      

"ክርስትያን ተብዬ ብቻ መጠራት የምፈልግ አይደለሁም ፤ ይልቁንም መሆንን እፈልጋለሁ ... ስጋዬን ለአውሬዎች ይስጡት በአውሬዎቹም ጥርስ ልፈጭ ፤ ንጹህ የክርስቶስ ህብስት ሆኜ ልገኝ ፤ ከአካሌም ምንም አያስቀሩ ፣ ምናልባት ለእናንተ ሥራ እንዳልሆንባችሁ፡፡

[ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾክያ ለአራዊት ሊሰጥ ለሰማእትነት እየሄደ ሳለ ለሮሜ ሰዎች ከላከው መልእክት]

"በቅዱስ መስቀል አምሳያ ዘወትር ያለ ድካም ለጸሎት ለሚዘረጉትና በአሥር ጨካኝ ወታደሮች በብረት ሰንሰለት ታስረው ለተጎተቱት እጆችህ ሰላምታ ይገባል። ጵጵስናን ከቅዱስ ጴጥሮስ የተቀበልክ ሰማዕተ ክርስቶስ ቅዱስ አግናጥዮስ ሆይ ፣ ከታሰርኩበት የኃጢአት ሰንሰለት በተሰጠህ ሰማያዊ ሥልጣን ፍታኝ በብርሃን እጆችህም በፍጹም በረከት ባርከኝ።"
                                  
"ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል ፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።"
~|ኤፌ.፫፥፲፰

የአባታችን የቅዱስ አግናጥዮስ የከበረች ጸሎቱና ምልጃው አይለየን። ከበረከቱ ይክፈለን።

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ያከናወንክ፣ የሁሉ ፈጣሪ፥ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፣ እልፍ አእላፋት መላእክት የሚያመሰግንህ፣ ትእልፊተ አእላፋት ሊቃነ መላእክት የሚገዙልህ ዐይኖቻቸው ብዙ የሆኑ ኪሩቤል የሚቀድሱህ ክንፋቸው ስድስት የሆኑ ሱራፌል ያለማቋረጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅድስናን የሚቀድስ፣ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ፣ የነገስታት ንጉሥ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፣ ብርሃናትን የተጎናጸፈ እያሉ የሚያመሰግኑህ፤ አንተ ወደህ ፈቅደህ ልጅህን ከአተ ዘንድ ወደ እኛ ላክኸው፤ እርሱም ቃልህ ነው።

የጠፉትን የሚናገሩ በጎች የሚባሉ የሰው ልጆችን ወደ አንተ ይመልሳቸው ዘንድ። እንደ ፈቀደ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ከሰማያት ወረደ። ከቅድስት ድንግል ማርያምም ሰው ሆነ። ይህንን ሁሉ ያደረግኸው ለሰው ልጆች መድኀኒት ይሆን ዘንድ ነው። ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣኸን፤ አንተን ወደማወቅም መራኸን፤ አቤቱ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ መድኀኒታችን ለመሆን ሰው በሆነ በዋህድ ልጅህ፤ እነሆ ጌታ ይህ ዐመፀኛ ከሐዲ በሙሽራህ  ላይ ያደረገውን ተመልክተሃል።

የቤተ ክርስቲያንህን ልጆች እንደያዛቸውና እንደ በግና ፍየል እንዳረዳቸው። የሕዝብህንና የርስትህን ልጆችም እንዳጠፋቸው። ስለ ወንድሞቼ ስለ ምእመናን ቀንቻለሁና በመሲሕ መስቀል ኀይል ይህን የእኛንና የአንተን ጠላት እወጋው ዘንድ እወጣለሁ። እነሆ እኔ በአንተ እና በዋህድ ልጅህ፣ አመንኩ በመሠዊያው ቀንድም ተማጸንኩ በሃይማኖትህም ጸናሁ።

ስለዚህም ስምህን የሚያውቁ አምላካቸው ወዴት አለ እንዳይሉኝ ከተስፋዬ አታሳፍረኝ። በብዙ አበሳየና ኃጢአት ምክንያት ጸሎቴን ባትሰማኝ ስእለቴንም ብትተዋት እንኳን አቤቱ በዚህች ሀገር ግደለኝ እንጂ ስምህን ለማያውቁ ከሐዲ ጠላቶችህ ርስትህን አታሳልፋት። እኛ ሕዝቦችህ የመንጋህም በጎች ነንና። እስከ አለምም እናመሰግንሃለን።

#እኛም አለማዊ ጌጣችንን፣ የኃጢአት ልብሳችንን አውልቀን፤ ትህትናን ተላብሰን በተሰበረ ልብ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንግባ። ዲያቢሎስ የከፈተብንን ጦርነት ድል እንነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው። ዋናችን ይህን አስተምሮናልና። የእግዚአብሔር ሀይል እንጂ ንግሥናው ይህን እንደማያደርግ አውቋልና፤ ለኛም ባለጸጋነታችን ድልን አያደርግም።

#ኢትዮጵያንም እንደ ጥንቱ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍበትን ዘመን ያምጣልን። አሜን።


   
     ምንጭ: የናግራን ሰማዕታት

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.