#አስተርዮ_ማርያም
የማይታየው የታየበት፣ የራቀው የቀረበበት፣ የረቀቀው መለኮት በገዘፈ ሥጋ ማርያም የተገለጠበት፣ የወልድ ልጅነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ የተመሰከረበት፣ በልደቱ፣ በጥምቀቱ አንድነት በሦስትነት እንዲሁም መለኮት በሥጋ ሥጋም በመለኮት በተዋሕዶ ተገልጦ ምሥጢሩ ገሃድ የሆነበት የመገለጥ የመታየት ጊዜ የሆነው ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ዘመነ አስተርዮ እየተባለ ይጠራል፡፡
በዚሁ በዘመነ አስተርዮ መካከል የሚገኝ ስለሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “በዓለ ዕረፍት አስተርዮ ማርያም” እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ አስተርዮ ማርያም የምንለው ታላቅ በዓል እናታችን እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችበት መታሰቢያ ሲሆን ቀኑም ጥር ፳፩ ነው፡፡
ሰማይና ምድር የማይወስኑትን የወሰነች፣ ሞትን በሞቱ የመሻር ሥልጣን ያለውን፣ ዓለምን በመዳፉ የጨበጠውን የወለደች ክብርት ቅድስት እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም የምታርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ይኸውም ጥር ፳፩ ቀን በዕለተ እሑድ በ፷፬ ዓመቷ፣ በ፵፱ ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ነግሯት በልጇ መቃብር ሆና ጸሎት ታድርስ ነበር፡፡
እንዲህም ብላ ጸለየች፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሐዋርያትን ሁሉንም፣ ነፍሳቸውንም የለየሃቸውን አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋንና የሙታን አምላክ ነህና›› አለች፡፡ (የጥር ፳፩ ስንክሳር)
በዚህ ጊዜ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ከኤፌሶን አመጣችው፤ ምስጋናም አቀረበላት፤ ሁሉም ሐዋርያት የሞቱትም ከመቃብር ተነሥተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ እንዲህም ስትል ጠየቀቻቸው፤ ‹‹ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፤ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ሰማችሁ?›› አለቻቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ‹‹ወደ አንቺ እንድንመጣ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፤ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወደ አንቺ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አላት፡፡
በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደ እርሷ መጣ፡፡ (ጥር ፳፩ ስንክሳር)
እንዲህም አላት ‹‹እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጥቻለሁ›› አላት፡፡ እርሷ ግን ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜህ፤ በድንግልና ወልጀህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡
በዚህ ጊዜ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ አሳያትና ‹‹እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ሁሉ ነፍሳት መዳን ምክንያት (ቤዛ) ይሆናቸዋል›› አላት፡፡ ‹‹እነዚህን ሁሉ ከማርክልኝስ ይሁን›› አለች፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥጋዋን ከክብርት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በይባቤ መላእክት በክብር ነፍሷን ዐሳረጋት፡፡ (መዝገበ ታሪክ ቁጥር አንድ ገጽ ፻፶፭፣ ጥር ፳፩ ስንክሳር)
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!!!
#ማህበረ_ቅዱሳን