#ምሥጢረ ሥጋዌ
ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ያለአባት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆኖ ከወደቅንበት የኃጢአት ጉድጓድ (ሲዖል) አወጣን አዳነን ብለን ሰው መሆኑን የምንረዳበት እምነት ምሥጢረ ሥጋዌ ይባላል።
#ከማን ሰው ሆነ?
በነቢዩ ኢሳይያስ ፯፡፲፬ (7፥14) ሰለዚህ ጌታ ራሱ ምልከት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” ብሎ እንደተናገረ ሰው የሆነው ከድንግል ማርያም ነው። በሉቃስ 1፥27 "የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። ይላል።
ሰለዚህ እግዚአብሔር እምላክ የወደቀውን አዳምን ለማዳን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍሰን ነሥቶ ሰው ሆነ። ይህ ስው የሆነው አምላክ ነው። የሥጋን ባሕሪ ባሕርዩ ያደረገ የማይታየው የታየው የማይዳስሰው የተዳሰሰው ከእመቤታችን በተዋሐደው ሥጋ ነው ብሎ ማመን ምሥጢረ ሥጋዌን መረዳት ነው። መሠረታዊ ቃሉም በዮሐ.፩፡፩-፲፬ (1፥1-14) ያለው ነው። በመጀመሪያ ቃል ነበረ። ቃልም በእግዚብሔር ዘንድ ነበር። ቃልም እግዚእብሔር ነበር ብሎ “ቃል ሥጋ ሆነ” የሚሊውን የእግዚእብሔርን ከእመቤታችን መወለድ ይገልፃል።
#ሰው የሆነው ማነው?
አግዚአብሔር ነው፡- ዮሐ.፩፡፩-፫ (1፥1-3)
አምላክ ነው፡- ኢሳ. ፱፡፮ (9፥6)
ጌታ መድኃኒት ነው ፡- ሉቃስ ፪፥፰-፲፬ (2፥8-14)
ሰው የሆነው ከድንግል የተወለደው ሰማይና ምድርን የፈጠረ ብቻውን አምላክ የሆነ ጌታ መድኃኒት ኢየሱሰ ከርስቶስ ነው። ደገኛው ቅዱስ ጳውሎሰ እንዲህ ገልጾታል።
“ወእሙንቱ አበዊነ ወእምላዕሌሆሙ ተወለደ ከርስቶስ በሥጋ ሰብእ ዘውእቱ አምላከ ቡሩከ ለዓለመ ዓለም
“አባቶችም ከእነርሱ ናቸው፤ ከአነርሱም ከርሰቶሰ በሥጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው አሜን።" ሮሜ፱፡፭ (9:5)
#ለምን ሰው ሆነ?
አዳም በበደለው በደል የሰው ልጅ ሁሉ የሞት ሞት ተፈርዶበት ከአምላኩ ተለይቶ ገነት መንግሥተ ሰማያትን አጥቶ በኃጢአት ወድቆ ስለነበር ይህ የወደቀውን አዳምን ለማንሳት የሰው ልጅ ሁሉ ሕይወትን ያገኝ ዘንድ የዲያብሎስ ባርያ የነበረው ደካማው የሰው ልጅ ብርቱ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔርን ልጅነት ሥልጣን ያገኝ ዘንድ ወልድን ፍቅር ከሰማይ ሰቦት የመንግሥቱ ልጆች እንሆን ዘንድ ሰው ሆነልን።
“በእርሱ የሚያምን የዘላለም ሕይወት ኣንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እሰኪሰጥ ድረሰ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” ዮሐ ፫፡፲፮ (3:16)
“የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሐር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ለከ አንደ ልጆቹ እንሆን ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ” ገላ. ፬፥፬ (4፥4)
ስለዚህ የዘላለም ሕይወት እናገኝ ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ከኃጢአት በስተቀር የስውን ባሕርይ ባሕርዩ አድርጎ ያለመለወጥ ያለመቀላቀል ያለመከፋፈል ያለመለያየት በተዋሕዶ ሰው ሆነ።
ስለዚሀም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእመቤታችን ተወልዶ የሰው ልጅን ሁሉ አዳነ። ሰለዚህ አምላክ ሰው ሆነ ሰውም አምላክ ሆነ የሚለውን ምሥጢር በእምነት የተረዳ በጠንካራው ዐለት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
“በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃ አወጣን እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገናም በባርነት ቀንበር እትያዙ።”ገላ 5;1
ወልድ ሰው በመሆኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ያነሰ ወይም የበለጠ አይደለም። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ዘላለም ትክከል ነው። ብዙዎች የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስን ሰው መሆን ብቻ ያዩና ኃይሉንና እምላክነቱን ይክዳሉ ፪ጢሞ ፫፡፭ (3፥5) እርሱ ግን ዳኛ ፈራጅ ዘላለማዊ እምላክ ነው። በቸርነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን።
“ኢየሱስ ከርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘላለምም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ።” ዕብ.13+8
ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ የቅዱስ ባስልዮስ ወንድም፡ ከእመቤታችን ተወልዶ ስላዳነን የአብ ልጅ ወልድ ኢየሱስ ከርስቶስ እንዲህ አስተምሮናል፡-
በምድራዊ ልደቱ አባት አለው፡ በስማያዊ ልደቱም እናት አለችው አትበሉ፡ እርሱ በምድር አባት የሌለው ነው በሰማይም እናት የሌለችው ነው።
የከርስቶስን አካል ሁለት አታድርጉ ወደ ሁለት አካል ወደ ሁለት ባሕርይ ፈጽማችሁ አትለዩት ወልድን አንድ ወገን የተዋሐደውን ሥጋም አንድ ወገን አታድርጉ።
የማይለየውን ተዋሕዶውም ሊፈርስ የማይቻለውን አንዱን ትለዩ ዘንድ አትድፈሩ ሰው በሆነ በእግዚአብሔር ከመለኮቱ የተለየ ዕሩቅ ብእሲ (ለስም አጠራሩ ከብር ይግባውና እንዲሁ እንደ አንድ ሰው አምላክነት የሌለው) አንደሆነ አታስቡ አርሱ አንድ ብቻ እንደሆነ እመኑ እንጂ እርሱ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ ነው።
ከዘመን አስቀድሞ በቅድምና የነበረ ዛሬ ሰው የሆነ አምላክ ይህ ነው። አርሱም መለኮቱ ከትስብእቱ ትሰብአቱ ከመለኮቱ ሳይለይ ለዘለዓhም ይኖራል።
#በቀጣይ ምስጢረ ጥምቀትን እናያለን